Skip to main content
x

በበልግ አብቃይ አካባቢዎች የዝናብ እጥረት ሊያጋጥም እንደሚችል ተገለጸ

በበልግ አብቃይ የአገሪቱ ክፍሎች የዝናብ እጥረት ሊያጋጥም ስለሚችል ቅድመ ጥንቃቄ እንዲደረግ ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ኤጀንሲው ቀጣዩን የበልግ ወቅት አስመልክቶ ቅዳሜ ጥር 19 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ይፋ እንዳደረገው፣ ከአየር ንብረት ለውጡ ጋር ተያይዞ የውኃ እጥረትና በእንስሳት ላይ አደጋ ሊያስከትል የሚችል የአየር ንብረት ለውጥ ስለሚኖር፣ ከወዲሁ ይህንን ታሳቢ ያደረገ ዝግጅት እንዲደረግም አመልክቷል፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ በመጪው የበልግ ወቅት አካባቢዎቹ የአየር ፀባይን ግምት ውስጥ በማስገባት እንዲንቀሳቀሱ፣ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ያለባቸው አካላትም ይህንኑ የአየር ፀባይ አሉታዊ ተፅዕኖን ለመቋቋም መዘጋጀት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡