Skip to main content
x

የአዲስ አበባ ከተማ ቁልፍ ቦታዎችን ይዘው የቆዩ ሁለት ባለሥልጣናት ተነሱ

ላለፉት አሥር ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቁልፍ ቦታዎችን ይዘው ሲመሩ የቆዩት አቶ ተወልደ ገብረ ፃድቃንና አቶ ኃይሌ ፍሰሐ ከሥልጣናቸው ተነሱ፡፡ አቶ ተወልደ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት ዋና አማካሪ፣ እንዲሁም በከተማው ሙሉ ሥልጣን ያለው የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ ሹም ሽር አካሄደ

ዓርብ ነሐሴ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. አስቸኳይ ስብሰባ የተጠራው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት፣ መሠረታዊ በሚባል ደረጃ የካቢኔ ሹም ሽር አካሄደ፡፡ በዕለቱ ሹመት ከተሰጣቸው 18 የቢሮ ኃላፊዎች መካከል አራቱ ብቻ ነባር ሲሆኑ፣ የተቀሩት በሙሉ አዳዲስ ተሿሚዎች ናቸው፡፡

አቶ ግርማ ብሩ የብሔራዊ ባንክ ቦርድ ሰብሳቢ ሆኑ

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አቶ ግርማ ብሩ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ብንክ ቦርድ ሊቀመንበር እንዲሆኑ ተሰየሙ፡፡ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥን ጨምሮ ሦስት የመንግሥት ኃላፊዎች፣ በቦርድ አባልነት እንዲያገለግሉ ተመድበዋል፡፡

በመንገዶች ባለሥልጣንና በትራንስፖርት ሚኒስቴር አዳዲስ ሹመቶች ተሰጡ

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ሀብታሙ ተገኝ (ኢንጂነር) የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው መሾማቸው ታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ አርዓያ ግርማይ ደግሞ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው እንዲያገለግሉ መሾማቸው ታውቋል፡፡

ለአቶ ሀብታሙ የተጻፈላቸው ደብዳቤ ከሐሙስ ሐምሌ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲሱ የኃላፊነት ቦታ እንዲያገግሉ የሚረጋግጥ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ በቀድሞ የተቋሙ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ተተኩ

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዷለም አድማሴ (ዶ/ር) ከኃላፊነታቸው ተነስተው በምትካቸው የቀድሞ የተቋሙ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ ተተክተዋል፡፡

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር የነበሩት አቶ ኢሳያስ ዳኘው ተነስተው፣ በምትካቸው ቺፍ ቴክኖሎጂ ኦፊሰር የነበሩት አቶ አማረ አሰፋ ተተክተዋል፡፡

የኦሮሚያ የቀድሞ ሹም አዲስ አበባን በምክትል ከንቲባነት ይመራሉ

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉት አቶ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር)፣ በምክትል ከንቲባነት አዲስ አበባን እንዲያስተዳድሩ ተሾሙ፡፡ በቅርቡ በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ ቻርተር መሠረት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል ያልሆነ ምክትል ከንቲባ መሆን ችለዋል፡፡

አዲስ አበባ በምክትል ከንቲባ ልትመራ ነው

በቅርቡ በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ ቻርተር መሠረት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል ያልሆኑ ምክትል ከንቲባ ተሾሙ፡፡ በምክትል ከንቲባነት የተሾሙት አቶ ታከለ ኩማ (ኢንጂነር) ሲሆኑ፣ እሳቸው የከተማውን ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማን በተመተካት ኃላፊነቱን ማክሰኞ ሐምሌ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ ተረክበዋል፡፡

አቶ ታከለ የኦሮሚያ ክልል ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ የነበሩ ሲሆን፣ ቀደም ሲል የሱሉልታ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅና የሆለታ ከተማ ከንቲባም ነበሩ፡፡ የሰበታ ከተማ ኢንዱስትሪና ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ የኦሮሚያ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ሠርተዋል፡፡

አሜሪካ የአፍሪካ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትሯን የሶማሊያ አምባሳደር አድርጋ ሾመች

በአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር የነበሩት አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶን፣ የሶማሊያ አምባሳደር ተደረጉ፡፡ አምባሳደር ያማሞቶ በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ አምባሳደር ሆነው ለተወሰኑ ዓመታት ማገልገላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ላለፉት አንድ ዓመት ከስድስት ወራት ደግሞ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ ነበር፡፡

በሥራ ላይ ለነበሩና ለተሰናበቱ ስምንት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የአምባሳደርነት ሹመት ተሰጠ

የአምባሳደርነት ሹመት የተሰጣቸው በቅርቡ ከደኢሕዴን ሊቀመንበርነታቸው በፈቃዳቸው የለቀቁት የግብርናና እንስሳት ሀብት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ዓለማየሁ ተገኑ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ ያለው አባተ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ፣ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አቶ ዮናስ ዮሴፍ፣ እንዲሁም አቶ እሸቱ ደሴና አቶ አዛናው ታደሰ ናቸው፡፡