Skip to main content
x

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን እናት ባንክን በስድስት ሚሊዮን ብር ዕዳ ከሰሰ

እናት ባንክ አክሲዮን ማኅበር ሳትኮን ኮንስትራክሽን ለተባለ የሥራ ተቋራጭ የገባውን ዋስትና በተደጋጋሚ እንዲከፍል ሲጠየቅ ሊከፍል ባለመቻሉ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የስድስት ሚሊዮን ብር የፍትሐ ብሔር ክስ መሠረተበት፡፡ ባለሥልጣኑ በእናት ባንክ አክሲዮን ማኅበር ላይ ክሱን ሊመሠርት የቻለው፣ ከሰመራ-ዲዲግሳ ከሚያሠራው የመንገድ ግንባታ ጋር በተገናኘ በገባው ዋስትና ምክንያት ነው፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን 153.9 ሚሊዮን ብር እንዳይከፈለው ክስ ቀረበበት

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በኦሮሚያ ክልል የጌዶ-ፊንጫ-ለምለም በረሃ መንገድ ፕሮጀክት የጌዶ መናቤኛ መንገድ ሥራ ለማሠራት፣ ሀውክ ኢንተርናሽናል የፋይናንስና ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ጋር በነበረው የሥራ ውል ምክንያት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ቀረበበት፡፡ ባለሥልጣኑን የከሰሰው ሀውክ ኢንተርናሽናል ፋይናንስና ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በክሱ እንዳብራራው፣ ለመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ንብ ባንክ 153,957,947 ብር አስይዟል፡፡

መንገዶች ባለሥልጣን 1.8 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ መንገዶችን ለማስገንባት ስምምነት ፈጸመ

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቁ የሦስት መንገድ ግንባታዎችን ለማካሄድ ከሦስት የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች ተዋዋለ፡፡ በበጀት ዓመቱ የውል ስምምነት የተፈጸመባቸው ሦስቱ የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ የሚካሄደው በሶዶ-ድንቄ 86 ኪሎ ሜትር መንገድ፣ በወልድያ ከተማ 5.3 ኪሎ ሜትር መንገድና በድሬዳዋ ከተማ የሚገኘው የመልካ ጀብዱ-ድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ 7.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው መንገዶች ላይ ነው፡፡

የኮሪያ መንግሥት ለኢትዮጵያ የፍጥነት መንገዶች ግንባታ ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታወቀ

የደቡብ ኮሪያ መንግሥት በኢትዮጵያ እየተገነቡ ለሚገኙና ወደፊት እንደሚገነቡ ለሚታሰቡ የመንገድ መሠረተ ልማቶች ድጋፍ የመስጠት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ፡፡ በአዳዲስ መንገዶች ግንባታ ለመሳተፍ የኮሪያ መንግሥት ኩባንያ ከመንግሥት ጋር ድርድር ጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በበጀት ዓመቱ አንድ የመንገድ ግንባታ ውል አልፈጸመም

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ከዚህ ቀደም በየዓመቱ ሲያከናውነው ከነበረው በተለየ፣ በ2010 በጀት ዓመት አንድም የመንገድ ግንባታ ውል ሳይፈጽም የበጀት ዓመቱ ታጋመሰ፡፡ ባለሥልጣኑ በቀደሙ ዓመታት እስከ በጀት ዓመቱ አጋማሽ ድረስ የመንገድ ግንባታ ውላቸው ይፈጸማል ካላቸው ፕሮጀክቶች፣ ቢያንስ አንድ ሦስተኛውን የግንባታ ውላቸውን ይፈጽም ነበር፡፡ በ2010 በጀት ዓመት ግን እንደ ቀደሙት ዓመታት አዳዲስ የግንባታ ውሎችን ሳይፈጽም መዘግየቱ አዲስ ነገር ሆኗል፡፡

በሙስና የተከሰሱት የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች የእምነት ክህደት ቃል ሰጡ

የመንገዶች ባለሥልጣን ኃላፊዎች መቃወሚያቸውን እንዲያቀርቡ ተቀጠሩ በሙስናና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩትን ወ/ሮ ፀዳለ ማሞን ጨምሮ፣ 13 ተከሳሾች ዓርብ ጥቅምት 3 ቀን 2010 ዓ.ም. የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፡፡

የሁለት ሥራ ተቋራጭ ኩባንያዎች ኃላፊዎች ክስ ተቋረጠ

የአቶ ዛይድ ወልደ ገብርኤልን ክስ ለማሻሻል ቀጠሮ ተሰጠ በቀድሞ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር የመዝገብ ቁጥር 204154 ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት የሳትኮንና የሀዚአይአይ ኮንስትራክሽን ድርጅቶች ኃላፊዎችን ክስ ማቋረጡን፣ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት ዓርብ መስከረም 26 ቀን 2010 ዓ.ም. አስታወቀ፡፡

በሙስና የተከሰሱ አራት ደረጃ አንድ ተቋራጮችና መርማሪ ፖሊስ በንብረትና ገንዘብ አያያዝ ላይ ክርክር አደረጉ

ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ፖሊስ ገልጿል በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛይድ ወልደ ገብርኤል የክስ መዝገብ የተካተቱት ገምሹ በየነ ኮንስትራክሽን፣ ዲኤምሲ ኮንስትራክሽን፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የክስ መዝገብ የተካተቱት አሰር ኮንስትራክሽን፣ የማነ ግርማይ ጠቅላላ ተቋራጭና ኢሊሌ ዓለም አቀፍ ሆቴል በተጣለባቸው የንብረትና የገንዘብ ዕግድ ላይ፣ ከፌዴራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን ጋር መስከረም 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ክርክር አደረጉ፡፡

ለብይን ተቀጥረው ያለፍርድ ቤት ዕውቅና የተለቀቁት ተጠርጣሪ ጉዳይ ፍርድ ቤቱን አስቆጣ

ከቤተሰቦቻቸው ጋር አሜሪካ ዕረፍት ላይ ቆይተው ሲመለሱ በቁጥጥር ሥር ውለው በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ምርመራ ሲደረግባቸው የከረሙት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ፣ ለብይን ተቀጥረው ሳለ መለቀቃቸው ፍርድ ቤቱን አስቆጣ፡፡