Skip to main content
x

አንበሳ ባንክ ከ390 ሚሊዮን በላይ የተጣራ ትርፍ አስመዘገበ

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በ2010 ዓ.ም. ከታክስ በፊት 480.3 ሚሊዮን ብር ትርፍ በማስመዝገቡ የተጣራ ትርፉን 390.8 ሚሊዮን ብር እንዳደረሰው አስታወቀ፡፡ ባንኩ የ2010 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸሙን ቅዳሜ፣ ታኅሳስ 13 ቀን 2011 ዓ.ም. ይፋ ባደረገበት ወቅት እንዳስታወቀው፣ ከገቢ ግብር በፊት ያገኘው ትርፍ፣ ከካቻምናው በ54 በመቶ ወይም በ167.5 ሚሊዮን ብር ብልጫ አሳይቷል፡፡

አንበሳ ባንክ የወኪል ባንክ ተጠቃሚዎችን 100 ሺሕ አደረስኩ አለ

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የወኪል ባንክ አገልግሎት ተጠቃሚዎቹን ቁጥር ከ100 ሺሕ በላይ ማድረሱንና ከ25.6 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር መፈጸሙን ገለጸ፡፡ ባንኩ የወኪል ባንክ አገልግሎቱን ተጠቃሚዎች እዚህ ደረጃ ማድረስ የቻለው ከመደበኛ የባንክ አገልግሎት መስጫ ሲስተም ጋር በማስተሳሰር በጀመረው አሠራር መሆኑ ተገልጿል፡፡ ባንኩ ከ1,600 በላይ ወኪሎችና ክፍያ ከሚቀበሉ ከ300 በላይ ተቋማት ጋር አገልግሎቱን በማስተሳሰር የተሳካ ሥራ በመሥራቱ የተገኘ ውጤት መሆኑን አመልክቷል፡፡