Skip to main content
x

ኑሮ ከተባለ…

በአጭር የተከረከሙት ፀጉራቸው ብዙም ሽበት አይታይበትም፡፡ ጎስቋሏ ፊታቸው ግን እርጅና የተጫጫናቸው አስመስሏቸዋል፡፡ ከወለሉ የመስኮት ያህል ከፍታ ያለውን በር እንደተደገፉ ውጭ ውጭውን ያያሉ፡፡ ዕይታው የደከመው ዓይናቸው ግን ወዳጆቻቸውን እንኳን አይለይም፡፡ በስማቸው እየጠሯቸው ለሰላምታ እጃቸውን ለዘረጉላቸው ሰዎች አፀፋውን ቢመልሱም ማን መሆናቸውን አላወቁም፡፡

ሚሊዮኖች ሜዳ ላይ የሚፀዳዱባት ምድር

ትከሻ ለትከሻ ተደጋግፈው የቆሙት ደሳሳ ጎጆዎች የረባ ግድግዳ የላቸውም፡፡ አብዛኞቹም ባረጀ ቆርቆሮ የተሠሩ ሲሆን፣ በክረምት ወራት በላይና በታች ዝናብና ጎርፍ የሚያስገቡ ሰቆቃ የበዛባቸው ናቸው፡፡ የበጋው ሀሩር ሙቀቱ መድረሻ ሲያሳጣቸው፣ በክረምት ደግሞ ቆፈኑ ግራ ያጋባቸዋል፡፡

የስደተኞች ቁጥር ወደ 144 ሚሊዮን ከፍ ብሏል

ዓለም አቀፉ የፍልሰቶች ድርጅት (አይኦኤም) እ.ኤ.አ. በ2018 ብቻ 3,400 ስደተኞች ሕይወታቸውን እንዳጡ አስታውቋል፡፡ አብዛኞቹ ሕይወታቸውን ያጡት በጀልባ ተጭነው ወደ አውሮፓ አገሮች ለመግባት ሙከራ ሲያደርጉ ባህር ውስጥ ሰጥመው ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ጥቅጥቅ ደኖችንና በረሃ አቆራርጠው ድንበር ለመሻገር በሚያደርጉት አደገኛ ጉዞም ሕይወታቸው መጥፋቱን ድርጅቱ ይፋ ያደረገው ሪፖርት ያሳያል፡፡

አነጋጋሪው ጉዲፈቻ

ከሰውነት ተራ ያወጣት ሕመሟ ደጋግሞ ሲደቁሳት ቆይቷል፡፡ አንዴ በወጉ እንዳትራመድ እግሯን ሲሸመቅቅ፣ ሲለው ደግሞ ውስጥ አፏን እያቆሰለው እንዳትናገር እንዳትጋገር ሲያደርጋት አትደናገጥም፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመቄዶንያ ሕንፃ ሊገነባ ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፓይለቶች ለመቄዶኒያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል አሥር ሚሊዮን ብር ለመለገስ ቃል ገቡ፡፡ የአየር መንገዱን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያምን ጨምሮ ከአንድ ሺሕ በላይ ፓይለቶች እያንዳንዳቸው ከኪሳቸው አሥር ሺሕ ብር በማዋጣት ነው ድርጅቱ ለመርዳት ቃል የገቡት፡፡ ከቀናት በፊትም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለመቄዶኒያ ሁለት አምቡላንሶች መለገሱ የሚታወስ ነው፡፡

የቤተሰብ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

በሚቀጥለው ዓመት መጨረሻ አጠቃላይ ዓመታዊ የዋና ዋና ሰብሎች ምርታማነትን ወደ 406 ሚሊዮን ኩንታል ለማሳደግና የምግብ ዋስትናን በቤተሰብ ደረጃ በማረጋገጥ፣ ድህነትን ለማስወገድ እንደሚሠራ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ዴኤታ ካባ ኡርጌሳ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ 

አፍታ በዓይነ ሥውራኑ ዓለም

ፕሮግራሙ ወደተዘጋጀበት ቢርጋርደን የደረስኩት መገኘት ካለብኝ ሰዓት 40 ደቂቃ ያህል አርፍጄ ነበር፡፡  የእራት ግብዣውን አስመልክቶ በተደጋጋሚ ወደ ስልኬ ሲደወል ወደነበረው ቁጥር መታሁ፡፡ ‹‹አንደኛ ፎቅ ላይ ነን፣ ፕሮግራሙ ተጀምሯል ግቢ፤›› የሚል መልዕክት ከዚያኛው ጫፍ ሲደርሰኝ ወደ አሳንሰሩ ገባሁ፡፡  

ቀይ መስቀል ተፈናቃዮችን ለማቋቋም ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ያስፈልገኛል አለ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከምሥራቅ ወለጋ 75 ሺሕ፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከማሼ ዞን 15 ሺሕ፣ እንዲሁም ከጌድኦ የተፈናቀሉ በአጠቃላይ ከ90 ሺሕ በላይ ሰዎችን ለማቋቋም ከ523 ሚሊዮን ብር በላይ ያስፈልገኛል አለ፡፡