Skip to main content
x

የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ትብብርና ውጥረት ውስጥ ያለችው የኢትዮጵያ ሚና

የአፍሪካ ኅብረት ከተቋቋመበት ጊዜ ቀደም ብለው በነበሩ ዓመታት ከቅኝ ግዛት ነፃ የወጡ የአፍሪካ አገሮች ዋነኛ ትኩረት የነበረው፣ አኅጉራዊ ውህደትን ማምጣት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በወቅቱ ከኢኮኖሚያዊ ውህደትና ከፖለቲካ ውህደት የትኛው ይቅደም በሚለው አታካራ ወደ አንድ መምጣት አቅቷቸው፣ በጎራ በመከፋፈል ወደ ፉክክርና ክርክር ገብተው ነበር፡፡

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ሐውልት ግዘፍ የነሳበት የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ

ሰሞኑን የአፍሪካ ኅብረት 32ኛ የመሪዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ ሲካሄድ ለመወያያ አጀንዳ ሆኖ ከቀረበው ከስደተኞች፣ ከስደት ተመላሾችና ከአገር ውስጥ ተፈናቃዮች በላይ ከፍተኛ ትኩረት የሳበው፣ ከዛሬ 44 ዓመት በፊት በወታደራዊ የደርግ መንግሥት ከሥልጣናቸው የተወገዱት የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ሐውልት ነበር፡፡

ከሱዳን በብዛት የሚገቡ የጦር መሣሪያዎች የሁለቱን አገሮች ግንኙነት እንዳያበላሹ የመፍትሔ ምክክር መደረጉ ተገለጸ

በከፍተኛ መጠን ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው የቀጠለው ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎች የኢትዮጵያንና የሱዳን ግንኙነት እንዳያበላሹ፣ የሱዳን መንግሥት ጥንቃቄና ቁጥጥር እንዲያደርግ ውይይት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታወቁ።

የኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ተሻጋሪ ግንኙነት ሕግ እየተበጀለት ነው

ኢትዮጵያና ኤርትራ የሚጋሯቸውን ድንበሮች ለማቋረጥ ሕጋዊ ሰነድ መያዝ እንዲቻል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እየሠራ እንደሆነ ታወቀ፡፡ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ዕርቅ ከተደረገ በኋላ የሁለቱ አገሮች ዜጎች እንዳሻቸው ድንበር እየተሻገሩ ዘመድ ሲጠይቁ፣ ሲጎበኙና ሲነግዱ የነበረ ቢሆንም፣ ይኼንን ግንኙነት ፈር ለማስያዝ ሁለቱ አገሮች ለሚፈራረሟቸው ስምምነቶች በመዘጋጀት ላይ መሆናቸውን ሪፖርተር ከምንጮች ለማረጋገጥ ችሏል፡፡

ክብርና ዝናውን ለመመለስ የሰነቀው የመዲናዪቱ ብስክሌት ፌዴሬሽን

ኢትዮጵያ ኦሊምፒክን ጨምሮ በተለያዩ አኅጉራዊና ዓለማዊ ውድድሮች ከአትሌቲክስ ቀጥሎ ከምትወከልባቸው ስፖርቶች ብስክሌት ይጠቀሳል፡፡ ይሁንና ስፖርቱ  በፋይናንስ በተለይም በመወዳደሪያ ብስክሌቶች እጥረት ምክንያት ህልውናው ፈተና ውስጥ መግባቱ ውጤቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑ እንደተጠበቀ፣ በዲፕሎማሲው ረገድ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑ የሚገልጸው የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ነው፡፡

የኢትዮ ኤርትራ ድንበር ተዘጋ

ሐምሌ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በአስመራ ያደረጉትን ድንገተኛ ጉብኘት ካደረጉ በኋላ የሁለቱ አገሮች ግንኙነት በመሻሻሉ ተከፍቶ የነበረውና የኢትዮጵያና የኤርትራ ዜጎች ሲመላለሱበት የቆየው የኢትዮ ኤርትራ ድንበር፣ ከረቡዕ ታኅሳስ 17 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ መዘጋቱ ታወቀ፡፡

‹‹በኢትዮጵያ እየታዩ ላሉ ለውጦች በተቻለን መጠን ድጋፍ እናደርጋለን›› የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር

በኢትዮጵያ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደርና አሁን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቲበር ናዥ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በኢትዮጵያ ሲጀምሩ ከጎበኟቸው ተቋማት አንዱ የሰላም ሚኒስቴር ነበር፡፡ ከሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል ጋርም ውይይት አድርገዋል፡፡

የኤርትራ ወደቦችን ለመጠቀም ዝግጅት መደረጉ ተመለከተ

ከሁለት አሥርት ዓመታት በኋላ የኤርትራ ወደቦችን እንደ አዲስ ለመጠቀም እየተካሄደ ባለው ዝግጅት፣ አገራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ ዕቅድ መዘጋጀቱ ተመለከተ፡፡ የኤርትራ ወደቦች የሆኑትን አሰብና ምፅዋ ለመጠቀም የሚያስችል ዝግጅት እንዲያካሂድ ኃላፊነት የተሰጠው፣ ከዘርፍ መሥሪያ ቤቶች የተውጣጣ የቴክኒክ ኮሚቴና በከፍተኛ ባለሥልጣናት የተቋቋመው ዓብይ ኮሚቴ በቂ ዝግጅት ማድረጉ ተገልጿል፡፡

ኤርትራ የአፍሪካ ቀንድ የሠራተኞች ኮንፌደሬሽንን ለመመራት በፕሬዚዳንትነት ተመረጠች

ኤርትራ የፕሬዚዳንትነት ቦታ ያገኘችበት የአፍሪካ ቀንድ የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ምሥረታ በአዲስ አበባ ዕውን ተደረገ፡፡ የኮንፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት መቀመጫም አዲስ አበባ እንድትሆን ተወሰኗል፡፡