Skip to main content
x

የዳያስፖራ ኤጀንሲ ሥራ ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በይፋ ሥራ ሊጀምር መሆኑን የኤጀንሲው የሥራ ኃላፊዎች አስታወቁ፡፡ አዲስ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ አንድሪስና የኤጀንሲው የማኅበረሰብ ልማት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ወልዴ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ኤጅንሲው የሰው ኃይልና የአደረጃጀት ሥራዎችን ላለፉት ሁለት ወራት ሲያካሂድ ቆይቶ አሁን ሙሉ በሙሉ ሥራውን ማከናወን የሚችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል፡፡

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሐውልት በአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ወቅት ይመረቃል

በአፍሪካ ኅብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚቆመው የአፄ ኃይለ ሥላሴ ሐውልት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሌሎች አገሮች መሪዎች በሚገኙበት ተመርቆ ይፋ እንደሚሆን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስታወቁ፡፡

ዲፕሎማቶች ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምና ለዜጎች ጉዳይ ቅድሚያ እንዲሰጡ ማሳሰቢያ ተሰጠ

በቅርቡ ኢትዮጵያን በተለያዩ አገሮች እንዲወክሉ የተሾሙ 20 አምባሳደሮችና ሁለት ምክትል የሚሲዮን መሪዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና በተመደቡበት አገሮች ያሉ ኢትዮጵያውን ዜጎችን ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥተው ሊሠሩ እንደሚገባ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡

ከሱዳን በብዛት የሚገቡ የጦር መሣሪያዎች የሁለቱን አገሮች ግንኙነት እንዳያበላሹ የመፍትሔ ምክክር መደረጉ ተገለጸ

በከፍተኛ መጠን ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው የቀጠለው ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎች የኢትዮጵያንና የሱዳን ግንኙነት እንዳያበላሹ፣ የሱዳን መንግሥት ጥንቃቄና ቁጥጥር እንዲያደርግ ውይይት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታወቁ።

የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነትና ደኅንነት ፖሊሲ ማሻሻል ለምንና እንዴት?

ሁለት አሠርት ዓመታት ለመሙላት ጥቂት ጊዜ የቀረውንና በሥራ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና አገራዊ ደኅንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ለማሻሻል እየተሠራ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይና የአገራዊ ደኅንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር ከገባ 17 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ይኼንን ፖሊሲና ስትራቴጂ በፊታውራሪነት ያረቀቁት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ነበሩ፡፡

የኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ተሻጋሪ ግንኙነት ሕግ እየተበጀለት ነው

ኢትዮጵያና ኤርትራ የሚጋሯቸውን ድንበሮች ለማቋረጥ ሕጋዊ ሰነድ መያዝ እንዲቻል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እየሠራ እንደሆነ ታወቀ፡፡ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ዕርቅ ከተደረገ በኋላ የሁለቱ አገሮች ዜጎች እንዳሻቸው ድንበር እየተሻገሩ ዘመድ ሲጠይቁ፣ ሲጎበኙና ሲነግዱ የነበረ ቢሆንም፣ ይኼንን ግንኙነት ፈር ለማስያዝ ሁለቱ አገሮች ለሚፈራረሟቸው ስምምነቶች በመዘጋጀት ላይ መሆናቸውን ሪፖርተር ከምንጮች ለማረጋገጥ ችሏል፡፡

የኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ቆይታና ውጤቱ

ኢትዮጵያ የዛሬ ሁለት ዓመት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ተለዋጭ አባል በመሆን የተመረጠችው ታኅሳስ 23 ቀን 2009 ዓ.ም. ነበር፡፡ በወቅቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት አባልነት ድምፅ ከሰጡ 190 አባላት አገሮች መካከል የ185 አገሮችን ድምፅ በማግኘት የተለዋጭ አባልነት መንበሩን ስትቆናጠጥ የነበረው ጥያቄ፣ ይህ አባልነት ለአገሪቱም ሆነ ለቆመችለት ዓላማ ምን ፋይዳ ይኖረዋል የሚል ነበር፡፡

የኢትዮ ኤርትራ ድንበር ተዘጋ

ሐምሌ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በአስመራ ያደረጉትን ድንገተኛ ጉብኘት ካደረጉ በኋላ የሁለቱ አገሮች ግንኙነት በመሻሻሉ ተከፍቶ የነበረውና የኢትዮጵያና የኤርትራ ዜጎች ሲመላለሱበት የቆየው የኢትዮ ኤርትራ ድንበር፣ ከረቡዕ ታኅሳስ 17 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ መዘጋቱ ታወቀ፡፡

ኢትዮጵያዊው የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ሆነው ተመረጡ

ኢትዮጵያዊው የአቪዬሽን ባለሙያ አቶ ተፈራ መኮንን የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽን ዋና  ጸሐፊ ሆነው ተመረጡ፡፡ የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽን የአዲሱን ዋና ጸሐፊ ምርጫ ያካሄደው ሰኞ ኅዳር 24 ቀን 2011 ዓ.ም. በሊቪንግስተን ዛምቢያ ነበር፡፡ አቶ ተፈራ ከቻድ፣ ከቡርኪና ፋሶና ከዛምቢያ ዕጩዎች ብርቱ ፉክክር የገጠማቸው ቢሆንም፣ በሊቪንግስተን በተካሄደው ጉባዔ ማብራሪያ ካቀረቡ በኋላ በተካሄደው ምርጫ ተፎካካሪዎቻቸውን በከፍተኛ የድምፅ ልዩነት ማሸነፍ እንደቻሉ ታውቋል፡፡

ከታንዛኒያ 200 እስረኞችን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ የበጀት እጥረት አጋጥሟል

በታንዛያ እስር ቤቶች የሚገኙ 200 ኢትዮጵያውያንን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ የበጀት እጥረት ማጋጠሙ ተሰማ፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ከታንዛኒያ መንግሥት ጋር በመደራደር 96 ኢትዮጵያውያን እስረኞችን ወደ አገራቸው እንዲገቡ ማድረግ ቢቻልም፣ ቀሪዎቹን 200 እስረኞች ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ ግን እስካሁን አልተቻለም፡፡