Skip to main content
x

ከኦዳነቤ የተወጠነው የጅማ ጉዞ

በአሁኑ ወቅት ዱከም የሚባለው አካባቢ የቀድሞ ስያሜው ኦዳነቤ ይሰኛል፡፡ በኦዳነቤ መጫና ቱለማ የተባሉ የኦሮሞ ጎሳዎች ይኖሩበት ነበር፡፡ አፍሬና ሠዴቻ በሚል ለሁለት የተከፈሉት መጫወቻ ኦዳነቤን ትተው አምቦን ተሻግሮ በሚገኘው ጌዶ አካባቢ ሰፈሩ፡፡

የድል ደወል

ፋሺስት ጣሊያን አዲስ አበባን በያዘበት ማክሰኞ ሚያዝያ 27 ቀን (1928 ዓ.ም.) በሕዝቡና በአርበኞች ተጋድሎ የኢትዮጵያ የድልን ቀን ሰኞ ሚያዝያ 27 ቀን (1933 ዓ.ም.) ተበሰረ፡፡ 77ኛ ዓመቱንም ቅዳሜ ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ተዘከረ፡፡ ዘውዴ ረታ ‹‹የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት›› በሚለው መጽሐፋቸው ስለ ታሪካዊቷ ሚያዝያ 27 እንዲህ ጽፈዋል፡፡

የትምህርት ፕሮፌሰር ሚኒስትርና ዲፕሎማት ኃይለ ገብርኤል ዳኜ (1923-2010)

‹‹ባህልና ትምህርት ሁለት የሚደጋገፉ የሰውን ልጅ ሕይወት የሚወስኑ የማኅበረሰባችን አውታር ክስተቶች ናቸው፡፡ ባህል የማኅበረሰቡን አባላት በአስተሳሰብ እምነት፣ ምኞት ፍላጎት አኗኗር ወዘተ. ይወስናል፡፡ ያስተሳስራል፡፡ ዕውቀት፣ ጣዕም፣ ውበት፣ ብልህነት፣ ክህሎት፣ የመሳሰሉት ከባህል ይመነጫሉ፡፡ ትምህርት ግን ለባህል እንደመሣርያ ሆኖ፣ ባህልን ለአዲሱ ትውልድ በተግባርና በቀለም አማካይነት ያስተላልፋል፡፡

ልጅ እንዳልካቸው መኰንንን የዘከረው ዲቪዲ

ከሦስት ምታመት በፊት የነበረ አንድ ከመሳፍንት ወገን የሆነ ጸሐፊ (ራስ ስምዖን ዘሀገረ ማርያም) ‹‹መጽሐፈ ምዝጋና›› በሚለውና በግዕዝ በተጻፈው ድርሳኑ እንዲህ አስፍሮ ነበር፡፡፡ ‹‹ኢትዮጵያውያን ለምን ታሪካቸውን (ዜናቸውን) አይጽፉም? የውጭዎቹ ይጽፋሉ? የእኛስ? እኔ ግን እጽፋለሁ፤›› በማለት ታሪክን የመጻፍ አስፈላጊነት ያጎላበት ነበር፡፡

የታሪክና የቴዎሎጊያ ፕሮፌሰር ምክረሥላሴ ገብረአማኑኤል (1923 - 2010)

ከአራት ሺሕ ዓመታት የሚያልፈው የኢትዮጵያ ሥነ ጽሕፈት ታሪክ ከድንጋይ ላይ ጽሑፍ ወደ ብራና ላይ ጽሑፍ የተሸጋገረው ቅዱሳት መጻሕፍትን በዘመነ አክሱም ከመጀመርያው እስከ አራተኛው ምታመት መካከል ባሉት ዐረፍተ ዘመናት ውስጥ በመተርጐም ነው፡፡ መጻሕፍቱ ከግሪክና ከሶርያ ከሌሎችም ቋንቋዎች ወደ ግዕዝ ቋንቋ በመተርጐማቸው እስካሁን አገልግሎት እየሰጡ ናቸው፡፡

‹‹አሳቢው መንግሥቱ ለማ››

‹‹ድሃ፡- እባክዎ ጌታዬ ምፅዋት ያድርጉልኝ ችግር የበዛበት ፍፁም ድሃ ነኝ ጌታ፡- እኪሴ ያለውን የመቶ ብር ኖት እስክመነዝረው ታገሸኝ፤ ድሃ፡- ጌታዬ ይቅርታዎን ልድፈርዎትና ስንት እንደሚሰጡኝ ይንገሩኝ ለገና፤  ጌታ፡- እኔስ የምሰጥህ አንድ ብር ነው ምንዛሪ ታጣ ምን ይሁን ለዛው፤ ድሃ፡- 99 ብር አለኝ በምንቸቴ እዚሁ ይጠብቁኝ መጣሁ በፍጥነቴ ይኼው ይዤ ከተፍ አልኩ አሽከርዎ ኖቱን ይስጡኝና ምላሹን ልስጥዎ፤ ጌታ፡- የኔ ብልፅግና ካንተ ድህነት በአንድ ብር እኮ ነው የሚበልጥበት እንካ ምክር ልስጥህ ሥራ ሥራበት፡፡››

የልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም ግለ ታሪክ ዓርብ ይመረቃል

​​​​​​​በሃያኛው መቶ ዓመት የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በሚኒስትርነት፣ በአውራጃና ጠቅላይ ገዥነት የረዥም ዘመን አገልግሎት የሰጡት ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም ግለ ታሪክ ታተመ፡፡ ‹‹የትውልድ አደራ›› በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን የልዑል ራስ መንገሻ የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ ያሳተመው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ ነው፡፡

ዝክረ ዓድዋ

የዛሬ 122 ዓመት ጀግኖች የኢትዮጵያን መሬትና ሉዓላዊነት ለወራሪው የጣሊያን ጦር አሳልፈው ላለመስጠት ግንባራቸውን ለጥይት ሳይሰስቱ በታሪካዊው የዓድዋ ተራሮች የአገራቸውን ሰንደቅ ዓላማ ለማውለብለብ የቀራቸው ጥቂት ሰዓታት ብቻ ነበር፡፡ ከአምባላጌ ጀምሮ ጠላትን እየደመሰሱ የዓድዋ ተራራማ ሥፍራዎች በደረሱበት ወቅት አስቸጋሪውና ብዙ የሕይወት መስዋዕትነት ነበር ያስከፈላቸው፡፡

የዓድዋ ድል 122ኛ ዓመት

‹‹እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ፡፡ እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ፡፡ እንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉ ነውና ስለኔ ሞት አላዝንም፡፡ ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም ወደፊትም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ አሁንም አገር የሚያጠፉ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባህር አልፎ መጥቷል፡፡