Skip to main content
x

ብሔራዊ ባንክና ፓርላማው የማያውቋቸው የውጭ ምንዛሪ ቋቶች?

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር)፣ መነጋገሪያ ሆነው የሰነበቱበትን ንግግር አሰምተው ነበር። ገዥው አገሪቱ ከመድኃኒትና ከነዳጅ በቀር ለሌላ ሸቀጥ ግዥ ሊውል የሚችል በቂ የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንደሌላትና ያለውም ቢሆን አሳሳቢ እንደሆነ አመላክተዋል።

የውጭ  ምንዛሪ  ተመን  በገበያ  እንዲወሰን  መንግሥት  ማቀዱ ተሰማ

የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ የሚወሰንበት አሠራር ተግባራዊ እንዲሆን መንግሥት ዘላቂ ወይም የረዥም ጊዜ ዕቅድ መያዙ ተሰማ። አንድ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቁጥጥር ከሚደረግበት የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት እንዲያበቃ፣ በፍላጎትና አቅርቦት የገበያ መርህ የብር የውጭ ምንዛሪ ተመን እንዲወሰን መንግሥት አቅጣጫ አስቀምጧል።

የአገሪቱ ባንኮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የአምስት ሚሊዮን ብር እራት እንዲያዋጡ ብሔራዊ ባንክ ጠየቀ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በመጪው ግንቦት ወር ለሚያዘጋጁትና በሳህን አምስት ሚሊዮን ብር ለሚያስከፍለው እራት፣ ሁሉም የአገሪቱ ባንኮች እንዲያዋጡ ብሔራዊ ባንክ ጥያቄ አቀረበ፡፡

በአዲሱ አስተዳደር የኢኮኖሚው የአንድ ዓመት  ቆይታ  

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ኃላፊነት ተረክበው ኢትዮጵያን መምራት ከጀመሩ ከነገ በስቲያ ድፍን አንድ ዓመት ይሆናቸዋል፡፡ ከፖለቲካው አንፃር በርካታ ለውጦች በታዩበትና ጠቅላይ ሚኒስትሩም ያልተለመዱ አካሄዶችን ያሳዩበትና ጉልህ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች የተላለፉበት የአንድ ዓመት የሥልጣን ቆይታ እንደነበር ይታመናል፡፡

ለውጭ ምንዛሪ ክምችት የተለየ መፍትሔ ካልተገኘ ከነዳጅና ከመድኃኒት ግዥ በስተቀር ሌላ ጥያቄ ማስተናገድ እንደማይቻል ታወቀ

በቀጣዮቹ ወራት በተለየ ሁኔታ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ካልተገኘ በስተቀር፣ ከነዳጅና ከመድኃኒት ግዥ በዘለለ የኢኮኖሚውን ፍላጎት ማስተናገድ እንደማይቻል የብሔራዊ ባንክ ገዥ አስታወቁ። የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) የ2011 በጀት ዓመት የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐሙስ መጋቢት 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ባቀረቡበት ወቅት ነው ይህንን የተናገሩት።

የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን ኩባንያ የቦርድ ሊቀመንበር ሹመት ውድቅ ተደረገ

የጥቅም ግጭት አለው የተባለውና በድጋሚ ተመርጠው የነበሩትን የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን ኩባንያ የቦርድ ሊቀመንበር ሹመት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንዲያፀድቅ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ፡፡ የቀሪዎቹን ተመራጭ የቦርድ አባላት ሹመት አፀደቀ፡፡

ተንቀሳቃሽ ንብረት እንደ ብድር ዋስትና መያዣነት

በአገሪቱ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ በተበላሸ ብድር ክምችቱ ስሙ የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በቀደመው ዘመን የብድር አሰጣጡ በርካታ አማራጮችን የያዘና ታች ገበሬውና አርብቶ አደሩ ዘንድ ድረስ የሚሻገር እንደነበር የኋላ ታሪኩ ይመሰክራል፡፡

ብሔራዊ ባንክ የአዲሱን የንብ ባንክ ፕሬዚዳንት ሹመት አፀደቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ የሌሎች ኃላፊዎችንም ሹመት አፀደቀ፡፡ የንብ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ሹመታቸው ከፀደቀላቸው ውስጥ የባንኩ ፕሬዚዳንት በመሆን የተሾሙት አቶ ገነነ ሩጋ ናቸው፡፡ አቶ ገነነ የንብ ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ የሚያበቃ ሁኔታ ስለማሟላታቸው ባደረገው ማጣራት ገዥው ባንክ ማረጋገጡን አስታውቆ፣ ሹመታቸውን ያፀደቀበትን ደብዳቤ በሳምንቱ አጋማሽ ለባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ መላኩ ታውቋል፡፡

ኅብረት ባንክ በትውልደ ኢትዮጵያዊያን የተያዙ አክሲዮኖችን በከፍተኛ ዋጋ አገበያየ

በተለያዩ ባንኮችና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ውስጥ የአክሲዮን ባለድርሻ በመሆን የቆዩ የውጭ ዜጎች ኢትዮጵያዊያን ይዞታ ሥር የነበሩ አክሲዮኖች እንዲመለሱላቸው ቢወሰንም፣ አሁንም ግን ድርሻዎቻቸው ለጨረታ እየቀረቡ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡