Skip to main content
x

ተቃዋሚ ፓርቲዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ወደ ተግባር እንዲቀየር አሳሰቡ

ሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቃለ መሐላ የፈጸሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በፓርላማው ያደረጉት ንግግር ይዘት፣ በአብዛኞቹ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ዘንድ ተስፋን የጫረ እንደሆነና ወደ ተግባር እዲቀየርም ጠየቁ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ መንግሥትን ብቻ አነጋግረው በመመለሳቸው ሰማያዊ ፓርቲ ማዘኑን አስታወቀ

​​​​​​​ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያን የጎበኙ የአሜሪን፣ የሩሲያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ውስጥ በነበራቸው ቆይታ ከመንግሥት ጋር ብቻ ተነጋግረው መመለሳቸው፣ በእጅጉ እንዳሳዘነው ሰማያዊ ፓርቲ አስታወቀ፡፡፡

የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር በይቅርታ ተፈታ

የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው አቶ ዮናታን ተስፋዬ ሰኞ የካቲት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. በይቅርታ ተፈታ፡፡ አቶ ዮናታን በኦሮሚያ ክልል የተደረገን የሕዝብ ተቃውሞ በፌስቡክ አድራሻቸው ባሠራጨው መጣጥፍ እንዲባባስ አድርጓል ተብሎ፣ የሽብር ተግባር ወንጀል ክስ ተመሥርቶበት ሲከራከር መቆየቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ከእስር እንዲለቀቁ ተወሰነ

የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበሩት የአቶ ዮናታን ተስፋዬ ከእስር እንዲለቀቁ ተወሰነ፡፡

ሪፖርተር ያናገራቸው ምንጮች እንደገለጹት፣ የአቶ ዮናታን ከእስር እንዲለቀቁ ተወስኗል፡፡

አቶ ዮናታን በማኅበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ሁከትና ብጥብጥን የሚያበረታቱ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል በመባል ስድስት ዓመት ከስድስት ወር ተፈርዶባቸው የነበረ ቢሆንም፣ ይህ ፍርድ በሦስት ዓመታት እንዲቀነስላቸው ተወስኖላቸው ነበር፡፡

የቀድሞ የሰማያዊ አመራሮች አዲስ ፓርቲ ለመመሥረት ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ

የቀድሞ የሰማያዊ አመራሮች እነ አቶ ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) አዲስ ለሚመሠርቱት የሥነ መንግሥት ማኅበር (የፖለቲካ ፓርቲ)፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትብብር እንዲያደርግላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ ታወቀ፡፡

መኢአድና ሰማያዊ ፓርቲ አስቸኳይ የውይይት መድረክ እንዲፈጠር ጥሪ አቀረቡ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ሰማያዊ ፓርቲ የአገር ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ያካተተ የውይይት መድረክ እንዲዘጋጅና አገሪቱ ለገጠማት ወቅታዊ ችግርም መፍትሔ ከመድረኩ እንዲመነጭ ጥያቄ አቀረቡ፡፡

የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች አዲስ ፓርቲ ለማቋቋም ውሳኔ አሳለፉ

መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. በተደረገው የሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ ምክንያት አለመግባባት ተፈጥሮ ለሁለት ተከፍለው ከነበሩት አመራሮች፣ የእነ አቶ ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) ቡድን አዲስ ፓርቲ ለማቋቋም ውሳኔ ላይ መድረሱን አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ ተከትሎ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር መሆናቸው በተረጋገጠው ሊቀመንበሩ አቶ የሺዋስ አሰፋ የሚመራው ቡድን፣ በአገር ሽማግሌዎች የተደረገውን የማስማማት ጥረትና የውሳኔው ሐሳብ ተግባራዊ ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የችግሮችን ምንጭ ያለመረዳት እያስከፈለ ያለው ዋጋ

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከአንድ ወር በፊት ለአሥራ ሰባት ቀናት አድርጎት የነበረውን ዝግ ስብሰባ ሲያጠናቅቅ ባወጣው መግለጫ፣ በአገሪቱ ለተከሰቱ ግጭቶችና በግጭቶቹ ምክንያት ለጠፋው የሰው ሕይወትና ለወደመው ንብረት ሙሉ ኃላፊነት እንደሚወስድ መግለጹ ይታወሳል፡፡ በዚህም የአገሪቱን ሕዝብ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል፡፡ በአገሪቱ እየተከሰተ ያለውን ግጭት ለማስቆምና አገራዊ መግባባት ለመፍጠር ሲባልም፣ በወንጀል ተጠርጥረውና ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች ከእስር እንደሚፈቱ ቃል ተገብቷል፡፡ በተገባው ቃል መሠረት በፌዴራልና በክልል ደረጃ እስካሁን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከእስር መለቀቃቸውን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ዓርብ ጥር 25 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡

ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ዳኛው ከችሎት እንዲነሱ የቀረበው አቤቱታ ውድቅ ተደረገ

ጋዜጠኛው በፌስቡክ ገጹ ያሠራጨውን ዘገባ እንዲያርም ትዕዛዝ ተሰጠ የወልቃይት የማንነት ጥያቄን ምክንያት በማድረግ በአማራ ሕዝብ ላይ የዘረኝነት አስተሳሰብ አራምደዋል በማለት የሽብር ተግባር ወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው ተከሳሾች፣ ክሳቸውን ከሚመለከቱት ሦስት ዳኞች አንደኛው እንዲነሱላቸው ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ተደረገ፡፡