Skip to main content
x

‘ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ . . . ይህንን ሁሉ ጉድ ትሰሚያለሽ ወይ?’

እነሆ ዛሬ ደግሞ ከመገናኛ ወደ ገርጂ ልንሳፈር ነው። ፀሐይን ሰሞነኛው ደመና ሸፍኗታል። ልክ አንዳንዱን እውነታ ሰሞነኛ ማስተባበያ እንደሸፈነው። የዘመኑ ኑሮ ሰውን ወዝውዞ ወዝውዞ የሆነ የሕይወት ቱቦ ውስጥ ጥሎ የረሳው ይመሳለል። መንገዱ ላይ ቆሜ በትርምሱና በጫጫታው መሀል የማሰላስለው፣ ከአድማስ ወዲህ ማዶ ስላለው ስለእኛ ስለሰው ልጆች ትግል ነው።

ግራ ተጋብተው ግራ የሚያጋቡን ምነው በዙ?

እነሆ መንገድ! ከቄራ ወደ ሜክሲኮ ልንጓዝ ነው። ከፊሉ በተንቧቸንበት ጎዳና ላይ ሲሮጥ፣ ከፊሉ ጉልበት ሳይከዳው ኑሮ ከብልኃቱ አልገናኝ ብሎት በጉብዝናው ወራት እያዘገመ ይጓዛል። ሩቅ ማሰብ፣ ነገን ማብሰልሰል፣ የዛሬን ሰላምና እርጋታ ያውካል። መንገድ ነውና ሰው መሆን በዘመናት ሒደት ሊፈታ ያልቻለ ታላቅ ሚስጥር ነውና ሕፃን አዋቂው ‘የዛሬ መንገዴ የት ያደርሰኝ ይሆን?’ ብሎ ሲርበተበት ገጹ ላይ ይነበባል።

በደመነፍስ ጉዞ የት ይደረስ ይሆን?

እነሆ መንገድ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። በላብህ ወዝ ትበላለህ ሆኖ በለቅሶ የተቀላቀልናት ዓለም ላይ የኑሮ ትግሉን ተያይዘነዋል። የሕይወትን ትርጉም፣ የመኖርን ጣዕም አጣርተን ሳናውቅ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ነገን እንጓጓለን። መነሻውን ባልደረስንበት የጉጉት ሰቀቀን ጎዳናው ላይ ወዲያ ወዲህ እንመላለሳለን።

ያልተገራ ሥልጣን የደሃ ጠላት ነው!

እነሆ መንገድ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ። አጀማመራችን በፀጥታ የተጠነሰሰ ነው። ተሳፋሪው በሙሉ የሚተነፍስ አይመስልም። በውጥረት የታፈነው ጎዳና መንገደኛውን አየር የነሳው ይመስላል። ጩኸት ኑሮው የሆነው ወያላ ዕድሜው በለቅሶ ተጀምሮ በጩኸት በሚገባደድ ሕዝብ መሀል ያለ ዕረፍት ይጮኻል። እንደ ንጋት ጎርናና ድምፁ ሁሉ ጎርበጥባጣ ኑሮው የሚቀጥል ይመስል እሪ ሲል አይታክትም።

ኑሮአችን የውሸት ሞታችን የእውነት እየሆነ ተቸገርን!

እነሆ ዛሬ የምንጓዘው ከቦሌ ወደ ካዛንቺስ ነው። ሁሉም አካባቢ አቋራጭ እንጂ አገር አቋራጭ ባለመሆኑ፣ ከአንድ ራሱ በቀር ተጎታች ሳይኖረው ይሳፈራል። ወያላው ራቅ ብሎ ቆሟል። ‹‹የት ነው?›› እያለ እርስ በርሱ ተጠያይቆ የሚሳፈረው መንገደኛ ብዙ ነው።

ወሬና ንፋስ ምንና ምን ይሆኑ?

እነሆ መንገድ! እነሆ ጉዞ! ከመገናኛ ወደ ስድስት ኪሎ። የጎዳናው ጭብጥ ተደጋጋሚ ነው። ሕይወት ቀለም ያለቀባት ትመስላለች። በመንጋ ቅርፅ አሠልፋ የምትነዳው ሕዝብ እልፍ ነው። ሲቃችን ተያያዥ ነው።

ወይ ጭቅጭቅና ብሽሽቅ?

እነሆ ጉዞ ከኮተቤ ወደ መገናኛ። ምን እንደገጠማቸው ያልታወቀ ሁለት ሴቶች ፊት ለፊት ተላተሙ። “አንችዬ!ምነው ዓይንሽ ቢያይ?” ብላ ግንባሯን እያሸች አንደኛዋ ቆመች።

የድል አጥቢያ አርበኛው በዛሳ?

እነሆ መንገድ። ከጳውሎስ ወደ ፒያሳ ልንጓዝ ነው። አላፊ አግዳሚው ወጪ ወራጁ ከምትፋጀው ፀሐይ ለመጠለል ታዛ እየፈለገ ይሰባሰባል። ተራ አስከባሪዎቹ ‹‹አንድሽም ሳትሠለፊ አትሳፈሪም፤›› እያሉ ያስፈራሩናል። ‹‹እናንተ ሰዎች ለምን አትተውንም ግን? የት እንድረስላችሁ?›› ትላለች የመረራት መሳይ። ‹‹የት ይደረሳል ብለሽ ነው? በየደረሽበት ሁሉ መደብደብ ነው።

ዓሳ የሚጠመደው አፉን ሲከፍት ነው!

እነሆ መንገድ ከመገናኛ ወደ ስድስት ኪሎ። የጎዳናው ጭብጥ ተደጋጋሚ ነው። ሕይወት ቀለም ያለቀባት ትመስላለች። በመንጋ ቅርፅ አሠልፋ የምትነዳው እልፍ ነው። ሲቃችን ተያያዥ ነው። ውክቢያው ዓይን ያጥበረብራል። ደምቆ ካማረበት ይልቅ ገርጥቶ ያስቀየመው ልቋል።