Skip to main content
x

በደቡብ ክልል በተቀሰቀሰ ግጭት ከአሥር በላይ ሰዎች ሞቱ

በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት ከአሥር በላይ ሰዎች መሞታቸውን፣ ዘጠኝ ሰዎች ከባድ፣ ከ80 በላይ ሰዎች ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸውና ከ3,000 በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ኃይሉ ተናግረዋል፡፡

የሞት ቅጣት ተወስኖባቸው የነበሩ 40 ግለሰቦችን ጨምሮ ለ332 ፍርደኞች ይቅርታ ተደረገ

በነፍስ ግድያና በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች የሞት ቅጣት ውሳኔ ያረፈባቸውን 40 ግለሰቦች ጨምሮ፣ ለ332 ፍርደኞች ዓርብ ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ይቅርታ ተደርጎላቸው ከእስር ተፈቱ፡፡ መንግሥት በፖለቲካና በሌሎች የተለያዩ ወንጀሎች ተከሰውና ቅጣት ተጥሎባቸው የነበሩትን ፍርደኞችና ክሳቸው በመታየት ላይ የነበሩ ተከሳሾችን፣ ከግንቦት 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በይቅርታና ክስ በማቋረጥ እየፈታ መሆኑ ይታወሳል፡፡

የአማራ ብሔር ተፈናቃዮች ድጋፍ እየተደረገላቸው እንዳልሆነ ገለጹ

ከኦሮሚያና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተፈናቅለው ባህር ዳር ከተማ ውስጥ የሚገኙ የአማራ ብሔር ተወላጆች፣ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ ሕይወታቸውን እየገፉ እንደሚገኙ ተናገሩ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለፈው ዓመት ቢያንስ አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በአገር ውስጥ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች፣ በተለይም ከሶማሌና ከኦሮሚያ ክልሎች መፈናቀላቸውን ይፋ ባደረገ በወራት ልዩነት መፈናቀሉ እንደገና አገርሽቷል፡፡

በትግራይና በኦሮሚያ ክልሎች ታስረው የነበሩ ከዘጠኝ ሺሕ በላይ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገላቸው

ግድያና ኢሰብዓዊ የወንጀል ተግባር ከፈጸሙ ተከሳሾችና ፍርደኞች በስተቀር፣ በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተከሰውና ፍርድ አርፎባቸው ለነበሩ 9,817 ተከሳሾች የትግራይና ኦሮሚያ ክልሎች መንግሥታት ይቅርታ አደረጉ፡፡ በትግራይ ክልል መንግሥት ይቅርታ የተደረገላቸው 2,206 ታራሚዎች ሲሆኑ፣ 45 ሴቶች መሆናቸውን የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋና የክልሉ የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብረ መስቀል ታረቀ ተናግረዋል፡፡

በዳንጎቴ ሲሚንቶ ሠራተኞች ግድያ ሰባት ተጠርጣሪዎች ተያዙ

በቅርቡ በዳንጎቴ ሲሚንቶ ሠራተኞች ላይ ከተፈጸመው የግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ ሰባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ ታወቀ፡፡ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ በወንጀሉ የተጠረጠሩ ሰባት ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ ምንጮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ከተጠርጣሪዎቹ አንዱ የዳንጎቴ ሲሚንቶ የከባድ መኪና አሽከርካሪ እንደሆነ፣ የተቀሩት የአካባቢው ነዋሪዎች መሆናቸውን ምንጮች አክለዋል፡፡

ለገርቢ ግድብ ፕሮጀክት መሬት ማስረከብ ባለመቻሉ ከቻይና የተገኘ 146 ሚሊዮን ዶላር ጥቅም ላይ ሳይውል ቀረ

ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ ለታሰበው የገርቢ ወንዝ ግድብ ፕሮጀክት፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስፈላጊውን መሬት በወቅቱ ባለማቅረቡ ከቻይና መንግሥት የተገኘው ብድር መጠቀሚያ ጊዜ አለፈበት፡፡ ይህ ገንዘብ ከአንድ ዓመት በፊት ሥራ ላይ መዋል የነበረበት ቢሆንም፣ መሬቱን ማግኘት ባለመቻሉ ተመላሽ ሆኗል ተብሏል፡፡

የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች ግጭት ውድመት ሪፖርት እየተጠናቀቀ ነው

በመስከረም ወር 2010 ዓ.ም. በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ግጭት ምክንያት የደረሰውን ውድመት የሚያጣራው ቡድን ሪፖርት እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ከሁለቱም ክልሎች ከ900 ሺሕ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ መጠኑ የማይታወቅ ንብረት ወድሟል፡፡

የዳንጎቴ ሲሚንቶ ሥራ አስኪያጅና ሠራተኞች ገዳዮችን ለመያዝ ከፍተኛ አሰሳ እየተካሄደ ነው

ረቡዕ ግንቦት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀኑ አሥር ሰዓት ላይ በጥይት ተደብድበው የተገደሉት የዳንጎቴ ሲሚንቶ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ጸሐፊና ሾፌር ገዳዮችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት ከፍተኛ አሰሳ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

የዳንጎቴ ሲሚንቶ ማኔጀር ተገደሉ

የዳንጎቴ ሲሚንቶ የኢትዮጵያ ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዲፕ ካማራ ረቡዕ ግንቦት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. አሥር ሰዓት ላይ ከጸሐፊያቸውና ከሾፌራቸው ጋር ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ 85 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምዕራብ ሸዋ ዞን አዳበርጋ ወረዳ፣ ልዩ ስሙ ረጂ በተባለ አካባቢ በሚገኘው የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ አካባቢ መገደላቸው ተሰማ፡፡