Skip to main content
x

የሰንደቅ ዓላማችን ኮከብ በኢትዮጵያ ካርታ ቢተካስ?

በዓለም ላይ የሚገኘው የሰንደቅ ዓላማ አጠቃቀም ታሪክ በእስያ አኅጉር የተጀመረ እንደሆነ አንዳንድ የታሪክ መረጃዎች ያሳዩናል፡፡ ይህ አጠቃቀም ወደተለያዩ አኅጉሮች ለመስፋፋት በቅቷል፡፡ ነፃ መንግሥታትም በሰንደቅ ዓላማቸው ቀለምና አቀማመጥ የሚለዩ ሲሆን፤ የአንድ መንግሥት ሰንደቅ ዓላማ ከሌላው መንግሥት ሰንደቅ ዓላማ ጋር አንድ ዓይነት መሆን አይችልም፡፡

ለውጡን ለማስቀጠል የባለድርሻ አካላት ሚናና ኃላፊነት

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች እየታዩ ያሉ ችግሮችን አስታኮ የብዙ ዜጎችና ሚዲያዎች የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆነው ከሰነበቱትና አሁንም በዚያው መልክ ከቀጠሉት ግንባር ቀደም ጉዳዮች መካከል፣ የሕግ የበላይነትን በማክበርና በማስከበር ረገድ የሚታዩ ችግሮች ዙሪያ የሚሽከረከሩ ነበሩ።

ነገርን ሁሉ በልክ እናድርግ

በህንድ የነፃነት ታጋይ አመራሮች መሀል ግጭት በመፈጠሩ ማሃተማ ጋንዲ ብርቱ ችግር አጋጠመው፡፡ መደማመጥ አልተቻለም፣ እንዳሻቸው መጓዝ ሆነ፡፡ የጋንዲ ዓላማ ሲጨናገፍ አመራሮቹን ጠርቶ መፍትሔ ፍለጋ ውይይት ይጀምራሉ፡፡ የችግሩ መንስዔና መፍትሔ ላይ አልተማመኑም፡፡ አንዱ ሌላውን ይከሳል፣ የፍቅር ባለ አርዓያው ጋንዲ ሁሉንም ሰምቶ በምሳሌ እንዲህ አለ፡፡

ሌባን ሌባ ለማለት እንድፈር!

አንድ በሥራው የማከብረውና የምወደው ነባር ጋዜጠኛና የትልቅ መሥሪያ ቤት የሕዝብ ግንኙነት መኮንን የነበረ፣ ባልሳሳት መንግሥት ለሲቪል ሰርቪሱ ደመወዝ በዓመት 18 ቢሊዮን ብር  እንደሚያወጣና ሲቪል ሰርቪሱ ግን የስድስት ቢሊዮን ብር ብቻ ሥራ እንደሚያከናውን የሚጠቁም መረጃ በመገናኛ ብዙኃን ሲያስተላልፍ ሰምቻለሁ።

አዲስ አበቤዎች ለምን ደመ መራር ሆኑ?

እንደሚመስለኝ አዲስ አበባን የመሠረቷት ሁሉም ኢትዮጵያን ናቸው፡፡ እንደ ዕድል ሆኖ አዲስ አበባ የታላቋ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ሆነች፡፡ ይኼን ዕድል ባታገኝ ኖሮ አካባቢው ወይም ለእርሻ ተስማሚ ነው እንደሚባለው ትልቅ ማሳ ይወጣት ነበር፡፡

ማጠንጠኛ

መኖርን የመሰለ ነገር የለም ሲባል እንዲያው ዘበት ይመስላል፡፡ መኖር ደግ ነው፡፡ ደጉንም ክፉውንም፣ ወጪውንም ወራጁንም በየፈርቁ ያሳያል፡፡ መኖር የእውነትም የቀጠሮና ጊዜ መጠበቂያ ነው፡፡ ‹እውነትና ንጋት እያደር ይገለጣል› እንዲሉ፡፡

በለውጥ ምዕራፍ ለአሳሳቢ ግጭቶች ተገቢው ትኩረት ይሰጥ!

ኢትዮጵያ ከተያያዘችው የመደመርና ይቅርታ ለውጥ ጎን ለጎን አሳሳቢ የሆኑ አካባቢያዊ ግጭቶች እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ እነዚህ ግጭቶች የብዙ ዜጎች ሕይወት አካልና ሥነ ልቦና ላይ አስከፊ ጉዳቶችን ከማድረሳቸው በተጨማሪ፣ ዜጎች ያፈሩትን ንብረት ለዘረፋና ውድመት በማጋለጥና ረጅም ጊዜ ከሚኖሩበት አካባቢ በማፈናቀል ከፍተኛ ማኅበራዊ ቀውስ አስከትለዋል፡፡ የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ ከጥልቅ ሐሳብ የመነጩና ግጭትን በመከላከል ረገድ ትኩረት የሚሹ የመፍትሔ ዕርምጃዎችን በመሰንዘር አስተዋጽኦ ለማበርከት ያለመ ነው፡፡

ኢሕአዴግ በመንታ መንገድ ላይ

የሰው ልጅ ለአቅመ አዳም ደረሰ የሚባለው ዕድሜው ሰላሳ ዓመት ሲሞላው እንደሆነ ብዙዎች ያምናሉ፡፡ ይኼ ጊዜ አፍላ የጉርምስና ወቅት ተጠናቆ ሰው በአስተሳሰቡ መብሰልና መጎልመስ የሚጀምርበት ዕድሜም  ነው፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት አዳም ሲፈጠር የሰላሳ ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ነበር፡፡

‘አያ ጅቦ ሳታማሃኝ ብላኝ’

አገርና የፖለቲካ ድርጅት አንድ እንዳልሆኑና በአንድ ዓይነት መስፈሪያ እንደማይመዘኑ መናገር፣ መአልትና ሌሊት እየቅል መሆናቸውን የማስረዳት ያህል ነው፡፡ ታዲያ ይህ ሚስጥረ ሥላሴ እንዳልሆነ እየታወቀ ከሰፊው አገራዊ ጥቅም ይልቅ፣ ለአንድ የተወሰነ ቡድን ፖለቲካዊ ትርፍ ወይም ለግለሰብ መሪዎቹ ስምና ዝና የበለጠውን ትኩረት በመስጠት ሁለቱን ሆን ብሎ ለምን ማምታታት ይኖርብናል?

ውለታን አለመክፈል ከክህደት አይተናነስም

ሊቁ አንድን ሰነፍ ተማሪ ሁል ጊዜ ሲያነብ ንባብ ያርሙታል፡፡ በዚህም የተነሳ ጓደኞቹ እየናቁት ሄዱ፡፡ እርሱም ንባቡን ከማሻሻል ይልቅ መምህሩን ዝም የሚያሰኝበት ሌላ መንገድ አሰበ፡፡ አንድ ቀን በጋቢው ውስጥ አናት ውኃ የሚያደርግ የወይራ ዱላ ይዞ ወደ ንባቡ ቀረበ፡፡