Skip to main content
x

አንድነት ፓርቲ አዲስ አበባን ባለአደራ አካል እንዲያስተዳድራት ጠየቀ

አዲስ አበባ የሚያስተዳድራት አካል የሥራ ጊዜውን የጨረሰ በመሆኑ ባለድርሻ አካላትን ያካተተ ባለአደራ አስተዳደር እስከ ጠቅላላ ምርጫ ድረስ እንዲቋቋምና ይህም ተግባራዊ እንዲሆን፣ ከሌሎች የዴሞክራሲ ኃይሎች ጋር በጋራ በመሆን እንደሚታገል አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) አስታወቀ፡፡

ለጎዳና ተዳዳሪዎችና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የተጀመረው ፕሮጀክት ፈተና ገጥሞታል

በአዲስ አበባ ከተማ የጎዳና ተዳዳሪዎችንና ቀጥታ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ለማደራጀት በቅርቡ ሥራ የጀመረው ፕሮጀክት ፈተና እንደገጠመው ተነገረ፡፡ ፕሮጀክቱ በመጀመርያው ዙር አምስት ሺሕ ዜጎችን ለማንሳት ዕቅድ ይዞ 3,147 የጎዳና ተዳዳሪዎችን፣ የአዕምሮ ሕሙማንን፣ አረጋውያንን፣ ሠርቶ ማደር የማይችሉ አካል ጉዳተኞችንና የመሳሰሉትን ስምንት ማዕከላት ውስጥ ማስገባቱ ይታወሳል፡፡

በአዲስ አበባ ጉዳይ ለመወያየት በተጠራ ስብሰባ የተሳተፉ ወጣቶች ታስረው ተለቀቁ

‹‹ስለአዲስ አበባ ምን ይደረግ?›› በሚል መሪ ቃል እሑድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት፣ በባልደራስ የቤተ መንግሥት ጡረተኞች አክሲዮን ማኅበር አዳራሽ ውስጥ ተገኝተው የነበሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች፣ ‹‹የመረበሽ አዝማሚያ አሳይተዋል›› በማለት የፌዴራል ፖሊስ ተይዘው የታሰሩ ቢሆንም፣ በማግሥቱ ሰኞ መጋቢት 2 ቀን 2011 ዓ.ም. ተፈቱ፡፡

የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ለማስተላለፍ የወጣው ዕጣ ተቃውሞ ቀረበበት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ13ኛው ዙር የኮንዶሚኒየም የመኖሪያ ቤቶችን ለማስተላለፍ የዕጣ ሥነ ሥርዓት ካደረገ በኋላ፣ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የተቃውሞ ሠልፎች ተደረጉ፡፡ የኦሮሚያ ክልል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ውሳኔ ተቃውሟል፡፡

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ተመዝጋቢዎች መቆጠብ ያለባቸው የገንዘብ መጠን ይፋ ሆነ

የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣ በሚወጣባቸው 18,576 የ40/60 ባለ አንድ፣ ባለ ሁለትና ባለ ሦስት መኝታ ቤት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ የሚካተቱት ተመዝጋቢዎች፣ እስካሁን መቆጠብ ያለባቸው 40 በመቶ የገንዘብ መጠን ይፋ ሆኗል፡፡

አምስት ሚሊዮን ብር ለሚከፈልበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የራት ግብዣ ምላሾች እየመጡ ነው

በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት ለአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻዎች ልማት ፕሮጀክት ገቢ ማሰባሰቢያነት በተጠራውና ‹‹ገበታ ለሸገር›› በተሰኘው የአምስት ሚሊዮን ብር (በአንድ ሰው) የራት ግብዣ፣ በርካታ ምላሾች ከወዲሁ እያስተናገደ እንደሚገኝ ታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ የነዋሪነት መታወቂያ የሚሰጥበት መመርያ ሥጋት አጭሯል

በአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አጥ ወጣቶች የነዋሪነት መታወቂያ እንዲያገኙ በከተማ አስተዳደሩ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ የተላለፈው መመርያ፣ በነዋሪዎች ላይ ሥጋት አጭሯል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ሥራ አጥ ወጣቶች የነዋሪነት መታወቂያ ስለሌላቸው መንግሥት በሚያመቻቸው የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆን አለመቻላቸውን በመጥቀስ፣ የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አንፃር የመታወቂያ ችግር እንዲፈታላቸውና የሥራ ዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በክፍላተ ከተሞች መጠየቁን ኤጀንሲው ገልጿል፡፡

በሪል ስቴት  የተሰማሩ ኩባንያዎች የመሬት ሊዝ  ውላቸውን እንዲያድሱ  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሰነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ውስጥ በሪል ስቴት ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች የመሬት ሊዝ ውላቸውን እንዲያድሱ፣ የቤቶች ግንባታ በማካሄድ ላይ ያልሆኑት ደግሞ የሊዝ ውላቸው ተቋርጦ የወሰዱት ይዞታ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ወሰነ።