Skip to main content
x

ፌዴራል ፖሊስ በአቶ ኢሳያስ ዳኘው ላይ ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ ተደረገ

የፌዴራል ፖሊስ በአቶ ኢሳያስ ዳኘው ላይ ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውደቅ አደረገው፡፡

ፍርድ ቤቱ አቶ ኢሳያስ ዳኘው የከፍተኛ ፍርድ ቤት አሥረኛ ወንጀል ችሎት በ50 ሺሕ ብር ዋስትናና ከአገር እንዳይወጡ ዕግድ በመጣል ከእስር እንዲፈቱ የሰጠውን ትዕዛዝ አፀና፡፡

ፌዴራል ፖሊስ በአቶ ኢሳያስ ላይ ያቀረበውን የወንጀል ጥርጣሬ መነሻ ሐሳብ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ ያደረጉት ለሦስተኛ ጊዜ ነው፡፡

የፍትሕ ሥርዓቱን ቁመና ገልጦ ያሳየው ፍትሕን ፍለጋ ጉዞ

ሕገ መንግሥቱ ያጎናፀፋቸውን ፍትሕ የማግኘት መብት ያጡ ወይም የተነፈጉ የተወሰኑ ግለሰቦች ላለፉት አሥር ዓመታትና አሁንም ባለመታከት እያደረጉት የሚገኘው የፍትሕ ፍለጋ ጉዞ የት ደረሰ? በጉዟቸው መሀል ያገኙዋቸው ምላሾች ተቃርኖ ስለሕግ ተርጓሚው የፍትሕ አካል ቁመና ምን ይናገራል? የሚለው የዚህ ዘገባ ትኩረት ነው። አንቀጽ 37 እንደ መነሻ

በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው በታሰሩት የቀድሞ የማዕከላዊ አሥር መርማሪዎች ላይ ክስ ተመሠረተ

በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) ከ2002 ዓ.ም. እስከ 2010 ዓ.ም. የወንጀል ምርመራ ዳይሬክተር፣ የምርመራ ቡድን መሪና መርማሪ ሆነው ሲሠሩ፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባትና የኦነግ አባል ናቸው ተብለው በተጠረጠሩና በታሰሩ በርካታ ግለሰቦች ላይ ተገቢ ያልሆነ የምርመራ ዘዴ ተጠቅመዋል በተባሉ በአሥር የቀድሞ ማዕከላዊ መርማሪዎች ላይ ክስ ተመሠረተ፡፡

ከቂሊንጦ ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ኢሰብዓዊ ድርጊት ፈጽመዋል የተባሉ ስምንት የማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ተከሰሱ

ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም. በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ቂሊንጦ የጊዜ ቀጠሮ እስረኞች ማቆያ ቤት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ፣ በኢሰብዓዊ ድርጊት ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ በነበሩ ስምንት የተለያዩ ክፍል ኃላፊዎች ላይ ማክሰኞ የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተ፡፡

ዓቃቤ ሕግ በኢምፔሪያልና በሪቬራ ሆቴሎች ላይ ባቀረበው ክስ ለቀረበበት መቃወሚያ ምላሽ ሰጠ

የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ በኮርፖሬሽኑ የተለያየ ኃላፊነት የነበራቸው ዘጠኝ ተከሳሾች፣ ከኢምፔሪያል ሆቴልና ከሪቬራ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባለቤቶች ጋር በጥቅም በመመሳጠር ግዥ እንዲፈጸም ተደርጓል በሚል በቀረበው ክስ ላይ፣ ተከሳሾቹ ያቀረቡትን መቃወሚያ በመቃወም ዓቃቤ ሕግ ምላሽ ሰጠ፡፡

በዋስትና እንዲፈታ ተፈቅዶለት የነበረው የሶማሌ ክልል ወንጀሎች ተጠርጣሪ በሙስና ወንጀል ሊከሰስ ነው

በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማና ሌሎች ከተሞች ላይ ተፈጥሮ የነበረውን ግድያ፣ ቃጠሎ፣ መፈናቀልና ሌሎች ወንጀሎችን እንዲቀጣጠሉ በማድረግ ተጠርጥሮ ታስሮ የነበረው አቶ ቴዎድሮስ አዲሱ (ቴዲ ማንጁስ) በ80 ሺሕ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈታ ፍርድ ቤት የሰጠው ትዕዛዝ ሳይፈጸም፣ በሙስና ወንጀል ክስ ለመመሥረት ዓቃቤ ሕግ ፍርድ ቤቱን ጠየቀ፡፡

በመንግሥት ላይ 71.6 ሚሊዮን ብር ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ የቀድሞ የሜቴክ ኃላፊዎች ተከሰሱ

በመንግሥት የተሰጣቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመገልገልና በጥቅም በመመሳጠር፣ በመንግሥት ላይ ከ71.6 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ በሜቴክ ውስጥ የተለያዩ ኃላፊነት የነበራቸው ስድስት ሠራተኞችና አንድ ነጋዴ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

አቶ ኢሳያስ ዳኘው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ በሰባት አባላት በፀደቀ ውሳኔ ሊጠየቁ እንደማይገባ ተናገሩ

የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት የሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው፣ ኢዲኤም ለተባለ የአሜሪካ አማካሪ ድርጅት ከተፈጸመ ክፍያ ጋር በተያያዘ በሙስና መጠርጠራቸውን ተቃወሙ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጨምሮ በሰባት አባላት በፀደቀ ውሳኔና በተፈጸመ ክፍያ እሳቸው ሊጠየቁ እንደማይገባም ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቶ ኢሳያስ ዳኘው ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጠ

የሥር ፍርድ ቤት ማለትም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አሥረኛ ወንጀል ችሎት በ100 ሺሕ ብር ዋስ እንዲፈቱ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ፣ ትዕዛዙ በይግባኝ ታግዶ ለአንድ ወር ታስረው የከረሙት አቶ ኢሳያስ ዳኘው በተመሳሳይ ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማክሰኞ የካቲት 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

የሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሐሰተኛ ማስተርስና ዶክትሬት ዲግሪ እንዲሰጥ አድርገዋል መባላቸውን ተቃወሙ

‹‹ካሊፎርኒያ ኢንተርናሽናል ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ›› ተብሎ ከሚጠራ ሐሰተኛ የፈጠራ ተቋም፣ ሐሰተኛ ሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ እንዲሰጥ አድርገዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው የሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው፣ የክስ መቃወሚያቸውን ለፍርድ ቤት አቀረቡ፡፡