Skip to main content
x

ኢንጂነር ስመኘው በቀለ 1958 - 2010

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲነሳ የእሳቸው ስም፣ የእሳቸው ስም ሲነሳም የህዳሴው ግድብ በመነሳቱ የሚታወቁት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ስመኘው በቀለ (ኢንጂነር)፣ ሐሙስ ሐምሌ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ማለዳ በመስቀል አደባባይ ሞተው መገኘታቸው አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል፡፡

አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ከዳሸን ቢራ ቦርድ አባልነት ተሰናበቱ

የዳሸን ቢራ ፋብሪካ የቦርድ አባል የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን፣ አቶ ታደሰ ካሳና አቶ ወንድወሰን ከበደ ከቦርድ አባልነት መሰናበታቸው ይፋ ተደረገ፡፡ የዳሸን ቢራ ፋብሪካ የቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዴቪድ ሃምፒሻየር ሐሙስ ሐምሌ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ይፋ ባደረጉት መሠረት፣ ሦስቱ የቦርድ አባላት መሰናበታቸው ተረጋግጧል፡፡

አቶ በረከት ስምኦን ከዳሸን ቢራ ቦርድ አባልነት ተነሱ

የዳሸን ቢራ አክሲዮን ማኅበር በቦርድ አባልነት ሲያገለግሉ የቆዩትን አቶ በረከት ስምኦን፣ የጥረት ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩትን አቶ ታደሰ ካሳና አቶ ወንድወሰን ከበደን በአዳዲስ የቦርድ አባላት መተካቱን አስታወቀ፡፡

ሦስቱን ተነሺ የቦርድ አባላት የተኩት አዳዲሶቹ አባላት የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተርና የቀድሞ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አህመድ አብተው፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥና ቀድሞ የብሔራዊ የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ይናገር ደሴ (ዶ/ር) እና የጥረት ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስገፈጻሚና የቀድሞ የአማራ መልሶ ማቋቋም ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አምሳሉ አስረስ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

የወልዲያና የፍኖተ ሰላም ማረሚያ ቤቶች ተቃጠሉ

በአማራ ክልል በወልዲያና በፍኖተ ሰላም ማረሚያ ቤቶች በተነሳ ‹‹ግርግር›› ማረሚያ ቤቶቹ መቃጠላቸውንና ሌሎች ጉዳቶችም መድረሳቸውን፣ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስታወቁ፡፡

በማረሚያ ቤቶቹ ለተነሳው ግርግር ምክንያቱ በቅርቡ በፓርላማ የፀደቀው የምሕረት አዋጅ፣ እኛን ተጠቃሚ አያደርገንም በማለት የተቃወሙ እስረኞች ያስነሱት እንደሆነ አቶ ንጉሡ ገልጸዋል፡፡

የባሌ ጎባና የደምቢዶሎ ግጭቶች

ባለፉት ሦስት ዓመታት በተለያዩ ክፍሎች የተከሰቱ ተቃውሞዎችና አመፆች፣ በአገሪቱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ ያስከተሉ ነበሩ፡፡ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ጊንጪ ተነስቶ ክልሉን ያዳረሰው አመፅና ተቃውሞ፣ በአማራ ክልል በሰፊው የታየው ሕዝባዊ ተቃውሞና አመፅ የበርካቶች ሕይወት እንዲያልፍ፣ የአካል ጉዳቶች እንዲደርሱ፣ በርካቶች ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉና የአገሪቱ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ደረጃ እንዲጎዳ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

የደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤት ተቃጠለ

በአማራ ክልል የምሥራቅ ጎጃም ርዕሰ ከተማ ደብረ ማርቆስ ማረሚያ ቤትን እስረኞች ማክሰኞ ሐምሌ 17 ቀን 2010 ዓ.ም. ማቃጠላቸው ተገለጸ፡፡ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ የሚገኙ ከ1,200 በላይ የሚሆኑ ፍርደኞች፣ ተከሳሾችና ተጠርጣሪዎች መሀል ማረሚያ ቤቱን ያቃጠሉት፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የምሕረት አዋጁን በሚመለከት ሐምሌ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ያስተላለፈውን ማብራሪያ በቴሌቪዥን ካዩ በኋላ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ከታሪክ የማይማር ታሪክን ለመድገም ይገደዳል!

ከስሜታዊነት ይልቅ በምክንያታዊነት ላይ በመመሥረት በቅንነት፣ በድፍረትና በወሳኝነት ከ100 ቀናት በላይ የዘለቀው የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አመራር፣ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ አመኔታና ከበሬታ አግኝቷል፡፡