Skip to main content
x

ለኮንትሮባንድ ከዛቻም ከዘመቻም የበለጠ ሥራ ያስፈልጋል

ኢኮኖሚው እንደሚፈለገው መጓዝ እንዳይችል፣ ለአገር ዕድገትና ለውጥ እንቅፋት መሆኑ እየታወቀም ከመቀነስ ይልቅ እየጦዘ የሚገኘው ሕገወጥ ንግድ፣ በኢትዮጵያ ያፈጀ ነባር ችግር መሆኑ ብቻ ሳይሆን ብሶበት መታየቱ አሳሳቢነቱን አጉልቶታል፡፡  

ቤት ሆይ ወዴት አለህ?

የመኖርያ ቤት ችግር የጥያቄ ምንጭ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ከመሠረታዊ የሰው ልጅ ፍላጎቶች የሚመደበው የመጠለያ ችግር በተለይ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች የዘመናት ፈተና ነው፡፡

ብላሽ ግንባታ

ስለአገሪቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ብዙ ሲባል ኖሯል፡፡ በኢኮኖሚው ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ የያዘው ይህ ዘርፍ፣ ካለው አጠቃላይ ትይዩ ባሻገር ለአገር ሀብት ብክነትም ከፍተኛ ድርሻ አለው፡፡

‹‹እጠየቃለሁ››ን ጠበቅ!

የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከደንበኞቻቸው ወይም ከባለጉዳዮች ጋር ሊኖራቸው በሚገባው ግንኙነት ውስጥ ተጠያቂነትን ያካተተ አሠራር ይከተሉ ነበር ለማለት ይቸግራል፡፡ ጤናማ ግንኙነት አላሰፈኑም ለማለት የሚቻልባቸው በርካታ መገለጫዎች አሉ፡፡ ተቋማቱ ደንበኞቻቸውን በአግባቡ አያገለግሉም፡፡ አያስተናግዱም፡፡

በቀረጥ ነፃ ብዝበዛ

በየግብይት ሥርዓቱ ውስጥ የሚካሄዱ በርካታ ሸፍጦችና ወንብድናዎች ተበራክተዋል፡፡ የመንግሥት ሹማምንት ሳይቀር በንግድ መስመሮች ውስጥ በስውር እየተሳተፉና ከነጋዴዎች ጋር ‹‹በኔትወርክ›› እየተመሳጠሩ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ያለርኅራሄ የአገር ሀብት አባክነዋል፡፡

ድክ ድክ የሚለው የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ያገኙት የሕዝብ ድጋፍ አገሪቱን ወደፊት ለማራመድ እንደ መልካም ዕድል የሚወሰድ ስለመሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ይህ ድጋፍ በተለያዩ መንገዶች የተገለጸ ሲሆን፣ በተለይ ዳያስፖራው ለእርሳቸው የሰጠው ግምት ከፍተኛ ነው፡፡ ለዚህም ዳያስፖራው ከአንድ ማኪያቶው በቀን አንድ ዶላር አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ያደረጉትን ጥሪ በደስታ ነበር የተቀበለው፡፡

ባለድርሻዎች ከዛሬ ትርፍ ለነገ ጥቅም ይታጠቁ!

ሰሞኑን የፋይናንስ ተቋማት የ2010 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸማቸውን ለባለአክሲዮኖቻቸው ሪፖርት ሲያቀርቡ ሰንብተዋል፡፡ እንደተለመደውና እንደወትሮው ሁሉም አትራፊ ሆነው ዓመቱን እንዳጠናቀቁ አስታውቀዋል፡፡ ባንኮቹና መድን ኩባንያዎች ሌሎች አትራፊ ተቋማት፣ የውጭም ሆኑ የአገር ውስጥ ኩባንያዎች የማይወዳደሯቸው አትራፊዎች መሆናቸው የታወቀ ነው፡፡

ነዳጅ አንዳጅ!

አገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከምታፈስባቸው መሠረታዊ አቅርቦቶች ውስጥ ነዳጅ ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛል፡፡ በየዓመቱ በአሥር በመቶ ፍላጎቱ እየጨመረ የሚገኘው ይህ ምርት በ2011 በጀት ዓመት ከ83 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚጠይቅ ይጠበቃል፡፡