Skip to main content
x

በፓርኪንሰን ዙሪያ ያጠነጠኑት ሁለቱ መጻሕፍት

‹‹በፓርኪንሰን ላይ የሚነሱ 100 ጥያቄዎችና መልሶቻቸው›› እንዲሁም የፓርኪንሰን ፔሸንትስ ሳፖርት ኦርጋናይዜሽን ኢትዮጵያ›› በሚሉ ርዕሶች የታተሙ ሁለት የአማርኛ መጻሕፍት ባለፈው ሳምንት ለምረቃ በቅተዋል፡፡ በፓርኪንሰን ላይ የሚነሱ 100 ጥያቄዎችና መልሶቻቸው የሚለው መጽሐፍ የትርጉም ሥራ ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ በችግሩ ዙሪያ ስለሚሠራው ድርጅት አመሠራረትና ዕድገት የሚያብራራ ነው፡፡

ቲቢ ያመሳቀላቸው ነፍሶች

ከታክሲ ለመውረድ ወደ አንድ ግድም አነባብረው ያስቀመጧቸውን ድጋፎች አነሱ፡፡ ሁለቱን ክራንቾች በወጉ መጠቀም የለመዱ አይመስሉም፡፡ ለነገሩ በክራንች ታግዘው መሄድ ከጀመሩም ገና ዓመት አልሞላቸውም፡፡ ከትንሿ ታክሲ ለመውረድ ክራንቹ ብቻ በቂ ስላልነበር በጓደኛቸው መደገፍ ነበረባቸው፡፡

ለዓይን ተስፋ

የ65 ዓመቱ አዛውንት ካጠገባቸው ከተቀመጡት ሦስት ሰዎች በተለየ ከመቀመጫቸው  ተነስተው ከነበሩበት የአውሮፕላን ክፍል ወደ ሌላኛው ይራመዳሉ፡፡ እጃቸውን አጣምረው መለስ ቀለስ እያሉ ተራቸው እስኪደርስ ይጠባበቃሉ፡፡

ደም ባንክ የደም እጥረት አጋጥሞታል

ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ከፍተኛ የደም ዕጥረት እንዳጋጠመው አስታወቀ፡፡ እጥረቱ ያጋጠመው በባንኩ የነበረው ክምችት ከቡራዩ ዙሪያ ለተፈናቀሉና በደረሰባቸው የአካል ጉዳት ደም ለሚያስፈልጋቸው እንዲሠራጭ በመደረጉ እንደሆነ የደም ለጋሾች አገልግሎት ዘርፍ ዳይሬክተሩ ተመስገን አበጀ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልፀዋል፡፡

መድኃኒት የማይገታው የበሽታዎቹ ዑደት

ዓለም የዛሬውን ቅርጿን ሳትይዝ፣ አገሮች የየራሳቸው ሉአላዊ ድንበር ሳይኖራቸው፣ ምድር በሰባት አህጉሮች ሳይሆን በአካባቢ ግዛት ተከፋፍላ ትተዳደር በነበረበት፣ ጡንቻው የፈረጠመ አንድ መሪ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ደካማውን ያስገብር በነበረበት ጊዜ ጀምሮ ራስ ምታት የነበረ ጉዳይ ነው  አባሰንጋ (አንትራክስ)፡፡

በየዓመቱ 160 ሺሕ ኢትዮጵያውያንን የሚያጠቃው ካንሰር

የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው ደረጃ መሠረት አንድ የካንሰር ሕክምና ማዕከል አገልግሎት መስጠት ያለበት ለአንድ ሚሊዮን ሕዝብ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በማደግ ላይ ያሉ ሌሎች አገሮች ደግሞ በአንድ ማዕከል የሚያስተናግዷቸው የአገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር እስከ አምስት ሚሊዮን ድረስ ማስኬድ ይችላሉ፡፡

የማህፀን በር ካንሰር ክትባት በመደበኛነት መሰጠት ሊጀመር ነው

በሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ የሚከሰተውን የማህፀን በር ካንሰር ለመከላከል በመደበኛነት ክትባት መሰጠት ሊጀመር መሆኑ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ዕድሜያቸው 14 ዓመት ለሞላቸው ልጃገረዶች የሚሰጠው ይህ መከላከያ ክትባት፣ ከመጪው ዓመት ጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባዊ እንደሚደረግና በጤና ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶችና በጊዜያዊ የክትባት ማዕከሎች እንደሚሰጥም ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሕክምና ከየት እስከ የት

በባህላዊ የሕክምና ጥበብ ድልድይ ተሻግሮ ለተዓምር የቀረቡ ፈውሶችን መስጠት የቻለው ዘመናዊ ሕክምና ወደ ኢትዮጵያ የገባው ቆይቶ ነበር፡፡ ጉንፋን ሲይዘው ዳማከሴ ጨምቆ፣ አላስቆም አላስቀምጥ ለሚለው ጥርሱ ስራስር ነክሶ፣ ለሚያዋክበው ቁርጠት ጤና አዳም ጨምቆ፣ ክፉ መንፈስ ተጠናወተኝ ሲል በየሃይማኖቱ ፀልዮ፣ ድኝ ታጥኖ ሌላም ድንገተኛና አጣዳፊ ሕመም ሲያጋጥመው ቅጠል መበጠስ ለሚቀናው የኅብረተሰብ ዘመናዊ ሕክምና ብዙም አንገብጋቢ ጉዳይም አልነበረም፡፡

አዲሱ የጡት ወተት ፕሮጀክት

በመንግሥት ተቋማት ውስጥ ላሉ እናቶች የ120 ቀናት የወሊድ ፈቃድ ይሰጣል፡፡ ይህ ቀድሞ ከነበረው የ90 ቀን ፈቃድ ጋር ሲነፃፀር ለውጡ ተጠቃሽ ቢሆንም፣ አሁን ያለው የወሊድ ፈቃድ ሕፃናትን በሚፈለገው ሁኔታ ጡት ለማጥባት የሚያስችል አይደለም፡፡