Skip to main content
x

አንዲትን ላም በመቶ ሺሕ ጥጆች የመመንዘር ቀመር

ተሽሎ የተገኘውን ዝርያ መርጦ ከብቶችን የማዳቀልና የማባዛት ታሪክ የበረዶ ዘመን ማብቂያ ላይ ከዛሬ 10,000 ዓመታት በፊት ጀምሮ የተመዘገበ ነው፡፡ ለጅምሩ ዋነኛ ምክንያቶች የነበሩትም የሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሄድና የአየር ንብረት ለውጥ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በዚህ መነሻነት የተጀመረው እንስሳትን የማዳቀል ሳይንስ ለዘመናዊው ውስብስብ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶች መሠረት ሆኗል፡፡

ከ18 አገሮች የተውጣጡ ኩባንያዎች የሚታደሙበት ዓውደ ርዕይ

ፌርትሬድ የተሰኘው የጀርመኑ ኩባንያ ከአገር በቀሉ ፕራና ኤቨንትስ ኩባንያ ጋር በመተባበር በቋሚነት ማዘጋጀት በጀመረው የግብርና፣ የምግብና መጠጥ ማቀነባበሪያ እንዲሁም የፕላስቲክ ኅትመትና ምርት ማሸጊያዎች የንግድ ዓውደ ርዕይ ላይ ከ18 አገሮች የተውጣጡ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉበት ተገለጸ፡፡

ተማሪዎቹ በገበሬው ማሳ

በላይነሽ ቀለሜ የአሥረኛ ክፍል ትምህርቷን ያጠናቀቀችው በ2008 ዓ.ም. ነበር፡፡ በጊዜው ያመጣችው ውጤት ወደ መሰናዶ ትምህርት የሚያስገባት ባለመሆኑ በአቅራቢያዋ በሚገኝ ቀበሌ በግብርና ዘርፍ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች ድጋፍ እንድታደርግ ተመርጣ መሥራት ጀመረች፡፡

ለሜካናይዜሽን እርሻ የታጩት የአርሲ ባሌ ወጣቶች

የግብርናው ዘርፍ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዋልታ ቢሆንም፣ ከዘመናዊ አሠራሮችና የአመራረት ስልቶች ጋር ያለው ቁርኝት ብዙ ይቀረዋል፡፡ ለዘመናት የዘለቀው የኢትዮጵያ ግብርና፣ ዛሬም በጥማድ በሬ፣ ይህም ካልተገኘ ፈረስና ሌላም የጋማ ከብት ሲብስም አራሹ ራሱን ከእንስሳቱ ጋር በማጣመር ሞፈርና ቀንበር እየጎተተ የሚያርስ ገበሬና ሁዳድ የበዛበት ግብርና ነው፡፡

የግብርና ሚኒስቴር የመኸር ምርት እንዳይባክን እየሠራሁ ነው አለ

የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር በ2009/10 መኸር ምርት ዘመን በ13 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ላይ የለሙ የተለያዩ ሰብሎችን ለመሰብሰብ ዕቅድ በመያዝ እስካሁን በዘጠኝ ሚሊዮን ሔክታር ላይ ያለ ምርት ሰብስቢያለሁ አለ፡፡ በሰብል የተሸፈነው 13 ሚሊዮን ሔክታር መሬት በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በትግራይ፣ በደቡብና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እንደሆነ ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ መንግሥቴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፣ በሰብል ከተሸፈነው 13 ሚሊዮን ሔክታር መሬት 345 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ እንደታቀደ አስታውቀዋል፡፡

ግብርና ምርምሩን እጀ ሰባራ ያደረገ የቅንጅት ችግር

በስልሳዎቹ መጨረሻ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት አርሶ አደር ጫላ መርጊያ፣ በምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ ባኮ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው የበቆሎ ማሳቸው ውስጥ ሆነው ለአጨዳ የደረሰውን የበቆሎ አገዳ እያሻሹ ስለዘንድሮ የምርት ውጤት ፈገግታ በተላበሰ ገጽታቸው ለጎብኚዎቻቸው ያስረዳሉ፡፡

ትኩረት የሚሹ የግብርናው እክሎች

  በሁለተኛው ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ከተያዙ ዕቅዶች መካከልም የግብርናውን ዘርፍ ዘመናዊ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ዋናው ነው፡፡ አርሶ አደሩ ገበያን ታሳቢ አድርጎ እንዲያመርት፣ አነስተኛ መስኖዎችን በማስፋፋት የተሻሻሉ ዝርያዎችንና ግብዓቶችን በመጠቀም ምርታማነቱን እንዲያሳድግ፣ በገበያ ላይ ያለውን ተወዳዳሪነት እንዲጨምር፣ ዘመናዊ የእርሻ መሣሪያዎችን የመጠቀም ልምዱን እንዲያዳብርና የምርት ብክነቱን እንዲቀንስ በማድረግ ዘርፉ በየዓመቱ የስምንት በመቶ አማካይ ዕድገት እንዲያስመዘግብም ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ ቢሆንም፣ ዕቅዱን ለማሳካት የተለያዩ ችግሮች ማነቆ ሆነዋል፡፡

ምድረ በዳ ማሳዎች

በጋ ከክረምት ለመቶ ዓመታት ያህል ምንም ነገር በቅሎበት አያውቅም፡፡ ሌሎች በዙሪያው የሚገኙ ማሳዎች ልምላሜ ለብሰው ይኼኛው ቦታ ግን በተለየ ምድረ በዳ ሆኖ መታየቱ ለብዙዎች ያልተለመደና እንግዳ ነገር ነው፡፡ በአካባቢው ይኖሩ የነበሩና አሁን የሚገኙ አርሶ አደሮች ሰይጣናዊ መንፈስ ተጠናውቶታል በሚል ማረስ ከተው ዓመታት ተቆጥረዋል ይባል፡፡

የዘረ መል ቴክሎጂዎችን በአማራጭነት የመጠቀም ዕድል ለሴት አምራቾች እንዲመቻች ባለሙያዎች ጠየቁ

የዘረ መል ቴክሎጂዎችን በአማራጭነት የመጠቀም ዕድል ለሴት አምራቾች እንዲመቻች ባለሙያዎች ጠየቁ

የአሜሪካ መንግሥት ባዘጋጀውና መስከረም 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በተካሄደው  ዓውደ ጥናት ወቅት ተመራማሪዎች በግብርናው መስክ የተሰማሩ ሴቶች በዘረ መል ምህንድስና (ጄኔቲካሊ ሞዲፋይድ) የተመረቱ የግብርና ቴክሎጂዎችን በአማራጭነት የመጠቀም ዕድል እንዲመቻችላቸው ጠይቀዋል፡፡ 

የ118 ሚሊዮን ዩሮ ፕሮጀክት ትሩፋቶች

ለም የሆነው ቀይ አፈር ወድቆ የተገኘ ፍሬ ሁሉ የሚያበቅል ይመስላል፡፡ አቀበታማና ቁልቁለታማ የሆነው ሥፍራው ሙሉ በሙሉ አረንጓዴ ለብሷል፡፡ ከፊሉ የከብቶች ግጦሽ፣ የተቀረው ደግሞ የተለያዩ ጥራጥሬዎችና ሰብሎች ለምተውበታል፡፡ የአገሪቱ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነው የጫካ ቡናም ይለማበታል፡፡ ቦታው ፍፁም አረንጓዴ ነው፡፡