Skip to main content
x

ክልል ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን አዲስ አበባ የመዳኘት ኢሕገ መንግሥታዊነት

በወንጀል ድርጊት ተጠርጥረው የተከሰሱ እንዲሁም ጥፋተኛ ተብለው ፍርደኞች የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በይቅርታ ከማረሚያ ቤት ወጥተዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የወንጀል ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉትና መደበኛ አድራሻቸው በየክልሉ የሆኑት በርካታ ናቸው፡፡ ለነገሩ ክሳቸው ያልተቋረጠ ወይም በይቅርታ ያልተለቀቁ ነገር ግን የወንጀል ድርጊቱን ፈጽመዋል በተባለበት ወቅት አድራሻቸው ክልሎች ውስጥ የነበሩ በርካታ ተከሳሾች ጉዳያቸው አዲስ አበባ በሚገኙ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በመታየት ላይ ነው፡፡

የሕዝብ ቆጠራ ሕገ መንግሥታዊ አንድምታው

አራተኛው ዙር የሕዝብ ቆጠራ በቅርቡ የሚካሔድ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ቀድሞ ከተከናወኑትም የተሻለ ጥራት እንዲኖረው በቆጠራው የሚሰማሩትም ይሁኑ ተቆጣጣሪዎቹ ለእዚሁ አገልግሎት ሲባል ጥቅም ላይ የሚውሉ ኮምፒውተሮችን እንደሚጠቀሙ ይፋ ሆኗል፡፡ የሚሰበሰበው መረጃ የተሻለ ጥራት እንዲኖረው ለማድረግ ያግዛል፡፡ ኮምፒተሮቹ ላይ የሚጫኑት ፕሮግራሞች ላይ ስህተት ከሌለ ወይም ካልተፈጠረ በስተቀር በወረቀት ላይ ከሚሠራው እንደሚሻል ዕሙን ነው፡፡ 

ነሲባዊነት የነገሠባቸው በርትዕ የሚወሰኑ የጉዳት ካሳዎች

ውልን መሠረት ያላደረጉ የፍትሐ ብሔር ጉዳቶች ሲያጋጥሙ የካሳ አከፋፈሉን ሁኔታ የሚወሰነው በፍትሐ ብሔር ሕጉ አንቀጽ 2090 እና ተከታዮቹ አማካይነት መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ በእነዚህ ድንጋጌዎች መሠረት ካሳ ለማግኘት ጉዳት መኖር አለበት፡፡ ጉዳቱ በእርግጥም የደረሰ ወይም ወደፊት የሚደርስ ሊሆን ይችላል፡፡ ጉዳቱ የሚያስከትለው ኪሳራ ሊኖር ይገባል፡፡ ኪሳራው አንድም ገንዘብን  አንድም ሞራልን (ህሊናን) የሚነካ ሊሆን ይችላል፡፡

በኪነ ጥበብ ሐሳብን የመግለጽ መብት ይዘቱና ገደቡ

ባለፈው ሳምንት አርቲስቲ ቴዲ አፍሮ (ቴዎድሮስ ካሳሁን) በባህር ዳር የሙዚቃ ዝግጅት ማቅረቡ የሚታወቅ ነው፡፡ በባህር ዳር ማቅረቡም የመወያያ አጀንዳ እንደነበርም ግልጽ ነው፡፡ አጀንዳ እንዲሆን ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ ከዚህ ቀደም አዲስ አበባ ላይ ተመሳሳይ ዝግጅት ብቻ ሳይሆን አንድ ነጠላ አልበሙን ለማስመረቅ ሲባል የተዘጋጀው ፕሮግራም እንዲሁ አስተዳደራዊ እንደሆነ በተገለጸ ምክንያት ተከልክሎ ሳለ ባህር ዳር ላይ ግን መፈቀዱ ነው፡፡ በእርግጥ በተመሳሳይ ሁኔታ አርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳም እንዲሁ ተከልክሏል፡፡

ለአገራዊ መግባባት የፀረ ማሰቃየት (ቶርቸር) ሕግ አስፈላጊነት

ከ1966 ዓ.ም. ጀምሮ በምርመራ ሰበብ እጅግ በርካታ እስረኞች የሚሰቃዩበት ‘ማዕከላዊ’ በመባል የሚታወቀው ማረፊያ ቤት ተዘግቶ ሙዚየም እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ይፋ አድርገዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው በመታየት ላይ ያሉ ተከሳሾች የተለያዩ ድብደባና ሌሎች ኢሰብዓዊ ድርጊቶች እንደተፈጸሙባቸው ለችሎቱ ጉዳት የደረሰበትን አካላቸውን ጭምር እያሳዩ እንደሆነ በተለያዩ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡

የምሕረት አደራረግ ሕጉና ዓላማው ሲገለጥ

የኢሕአዴግ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከአባል ድርጅቶቹ ሊቃነ መናብርት ጋር በመሆን የግንባሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለ17 ቀናት ያደረገውን ግምገማ መሠረት በማድረግ ማብራሪያና መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫውም፣ የተሻለ አገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የዴሞክራሲ ምኅዳሩን ለማስፋት በጥፋታቸው ምክንያት ጉዳያቸው በዓቃቤ ሕግ ተይዞ በእስር የሚገኙም ሆኑ የተፈረደባቸው አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትናና ግለሰቦች ክሳቸው እንደሚቋረጥ ወይም ምሕረት እንደሚደረግላቸው አስታውቀዋል፡፡

የመተማመኛ ድምፅ መስጠትና መንፈግ ሕጋዊነትን ለማስፈን

ገዥው ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከሁለት ሳምንታት በላይ የፈጀ ስብሰባ በማድረግ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሠረት ፓርቲው ራሱ በተለይም ሥራ አስፈጻሚው የፈጸማቸውን ስህተቶች አምኖ ምን ማድረግ እንዳለበትም በተከታታይ በመግለጽ ላይ ይገኛል፡፡

በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ አጋርነት ረቂቅ አዋጅ ላይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2009 ዓ.ም. መደበኛ የሥራ ዘመኑን ከማጠናቀቁ በፊት ከሚኒስትሮች ምክር ቤት በመቀበል ወደ ቋሚ ኮሚቴዎች ከመራቸው ረቀቂ አዋጆች አንዱ የመንግሥትና የግሉን ዘርፍ አጋርነትን (Public Private Partnership) የሚመለከተው ነው፡፡

ሕጉን መሙላት ያልቻሉት የማሟያ ምርጫዎች

በተለያዩ እርከን ላይ የሚገኙ የሕዝብ ምክር ቤቶች አባላታቸው በሚጓደሉባቸው ጊዜያት የማሟያ ምርጫ እንዲደረግ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ አሁን በሥራ ላይ ያለውን የፌዴራሉን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በምሳሌነት ብንወስድ እንኳን ቢያንስ ሁለት አባላቱ እንደሞቱ ይታወቃል፡፡ አንዱ ከአዲስ አበባ፣ ሌላዋ ደግሞ ከአማራ ክልል የተወከሉ፡፡ ይሁን እንጂ በአሠራሩ ላይ የሁለት ድምፅ መጉደል ልዩነት እንደማያመጣበት በመገመትም ይሁን በሌላ ምክንያት የማሟያ ምርጫ አልተደረገም፡፡