Skip to main content
x

ሕጎችን የማሻሻል ተስፋና ሥጋቶች

ላለፉት በርካታ ዓመታት በአገሪቱ የፖለቲካ ልሂቃን፣ ፖለቲከኞች እንዲሁም የሰብዓዊ መብት አቀንቃኞች ዘንድ በተደጋጋሚ ለመንግሥት ከሚቀርቡ ጥያቄዎች ዋነኛውና አንዱ፣ ሕገ መንግሥቱን ጨምሮ በአገሪቱ እየተሠራባቸው የሚገኙ በርካታ ሕጎች እንዲሻሩ አልያም እንዲሻሻሉ የሚለው ይገኝበታል፡፡

በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት የመከረው ሳሙኤል ሃንቲግተንና የሰሞኑ ውይይት

አሜሪካዊው ሳሙኤል ሃንቲንግተን (ፕሮፌሰር) የዴሞክራሲ ሥርዓትን መገንባትና ማፅናት እንዴት ይቻላል? ወደዚህ መንገድ የሚወስዱ መሠረታዊያንስ ምንድን ናቸው? በሚሉ ጉዳዮች ላይ በመመራመርና በመተንተን ከመታወቁም በላይ፣ ከዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ፈጣሪ የፖለቲካ ሳይንቲስቶች መካከል ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው፡፡

የሥልጡን ፖለቲካ የጨዋታ ሕግ እፍርታም አይፈልግም!

ኢትዮጵያ ትልቅ አገር ናት ሲባል ለስታትስቲክስ ቀመር ማሟያ ብቻ አይደለም፡፡ ነገር ግን ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ በተዘረጋው ሰፊ ምድሯ ውስጥ የተለያዩ ማንነቶችን፣ ቋንቋዎችን፣ ባህሎችን፣ እምነቶችንና የአኗኗር ዘይቤዎችን ይዘው ኅብረ ብሔራዊነትን ጌጥ አድርገው የሚኖሩ 108 ሚሊዮን ያህል ዜጎች አገር ናት፡፡

ኦዴፓ የሚመራው የኦሮሚያ መንግሥትና ኦነግ የፈጸሙት ስምምነት የፈነጠቀው ተስፋና ሥጋቶቹ

የኦሮሞ ሕዝብ ለዓመታት ሲያካሂድ የነበረውን ፖለቲካዊ ትግል በመደገፍ ከሌሎች ለውጥ አራማጅ አጋሮቹ ጋር በመሆን ሌላ ፖለቲካዊ ትግል በኢሕአዴግ ውስጥ የከፈተው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ)፣ ትግሉን በድል አጠናቆ ኢሕአዴግንና የፌዴራል መንግሥትን መምራት የጀመረበትን አንደኛ ዓመት ከሁለት ወራት በኋላ ይደፍናል።

ራሱን እያስታመመ የሚገኘው ኢሕአዴግ

‹‹እንደሚታወቀው ኢሕአዴግ በየትግል ምዕራፉ ራሱን ከሁኔታዎች ጋር እያጣጠመ፣ እያስተካከለና እያጠራ የመሄድ ተሞክሮዎች ያሉት ድርጅት ነው። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ራሱን ከሕዝቡ ፍላጎቶችና ከአዳጊ ሁኔታዎች ጋር በማጣጣም፣ ከሚፈለገው የአመራር ብቃትና ቁመና ላይ ከመድረስ አኳያ ከፍተኛ ድክመቶች አሉበት። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገራችን ያጋጠመው የፖለቲካ ቀውስም ከዚሁ ድክመት የሚመነጭ ነው።››

በተቀናጀ መንገድ የሚመሩ ፀረ ለውጥ አስተሳሰቦች ለአገራዊ ለውጡ ተግዳሮት እንደሆኑ ኢሕአዴግ አስታወቀ

አሁን በአገሪቱ እየተከናወነ ያለው የለውጥ እንቅስቃሴ ምንም እንኳን ጥልቅ፣ ሰፊና ትልቅ ተስፋን ይዞ የመጣ ቢሆንም በተቃራኒው ሥጋቶች እንዳሉበት ‹‹ሕዝባዊ መሠረት የሌላቸው ፀረ ለውጥ አስተሳሰቦች በተቀናጀ መንገድ እየተመሩ ተግዳሮት ሆነውበታል፤›› ሲል፣ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መገምገሙን የግንባሩ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይትና ድርድር የሚመራበት ረቂቅ ደንብ ፀደቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያዘጋጀው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ በቀጣይ የሚያደርጉት ውይይትና ድርድር የሚመራበት 16 አንቀጽ ያለው ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይተው ማፅደቃቸውን፣ በውይይቱ ከተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡

መዋሀድ የከበዳቸው የመድረክ አባል ፓርቲዎች

አወዛጋቢው ምርጫ 97 በፖለቲከኞች፣ በሲቪክ ማኅበራት አመራሮች፣ እንዲሁም በጋዜጠኞች እስር መቋጨቱን ተከትሎ የአገሪቱ የፖለቲካ ምኅዳር ጭርታና ድብታ ወሮት ነበር፡፡ ይህንን ድብታ ለመስበር በሚመስል ሁኔታ የፖለቲካ ምኅዳሩን የተቀላቀለው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ)፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ በመሆን ለመሥራት እንቅስቃሴውን በ2000 ዓ.ም. ጀመረ፡፡