Skip to main content
x

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ መጓተቱን የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ

በአዲስ አበባ ከተማ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለማግኘት ተመዝግበው በየወሩ እየቆጠቡ የሚገኙ ቢሆንም፣ ግንባታው ግን አዝጋሚ መሆኑ በፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ ተገለጸ፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ በ20/60 እና በ40/80 ቤቶች ፕሮግራም ሳይቶች ላይ ባካሄደው ቅኝት  ግንባታው በተያዘለት ዕቅድ ከመሄድ ይልቅ እየተጓተተ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ለአዲስ አበባና ለኦሮሚያ ልዩ ዞን ነዋሪዎች የመጠጥ ውኃ ለማቅረብ ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለከተማዋና በአዲስ አበባ ዙሪያ ለሚገኙ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞች ነዋሪዎች ንፁህ የመጠጥ ውኃ ለማቅረብ፣ የነደፈውን ግዙፍ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ ዓለም አቀፍ ጨረታ አወጣ፡፡

ከ60 በላይ የታክሲ ማኅበራት ያለቀረጥ ታክሲዎችን ለማስገባት ያቀረቡት ጥያቄ በመዘግየቱ ቅሬታ አቀረቡ

ከሦስት ሺሕ በላይ አባላት ያሉዋቸው 65 የታክሲ ማኅበራት፣ ያለቀረጥ አዳዲስ ታክሲዎችን ለማስገባት ያቀረቡት ጥያቄ በመዘግየቱ ቅሬታ አቀረቡ፡፡ ቅሬታውን ያቀረቡት የታክሲ ማኅበራት ኃላፊዎች ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የአዲስ አበባን ገጽታ የሚቀይሩና ዘመናዊ መሣሪያ የተገጠመላቸው ከሦስት ሺሕ በላይ ታክሲዎችን ለማስገባት ከአንድ ዓመት በፊት ለመንግሥት ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ እስካሁን ድረስ ወደ ተግባር አልተገባም፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ3.4 ቢሊዮን ብር የ850 አውቶብሶች ግዥ ፈጸመ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው የተንሰራፋውን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት በ3.4 ቢሊዮን ብር የ850 አውቶብሶች ግዥ ፈጸመ፡፡ ከነዚህ አውቶብሶች መካከል 150 የሚሆኑት አገር ውስጥ ገብተው በቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ በመገጣጠም ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ከእነዚህ አውቶብሶች ውስጥ 100 የሚሆኑት በሸገር ብዙኃን መገናኛ ድርጅት አማካይነት ለተማሪዎች አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡

በአደይ አበባ ስታዲየም ዙሪያ የሚካሄዱ ግንባታዎችን የሚያስተባብር ኮሚቴ ተቋቋመ

የፌዴራል መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ እያስገነባ ያለው ‹‹አደይ አበባ ስታዲየም›› የግንባታ ሒደት ፈጣን ቢሆንም፣ መንገድን ጨምሮ በአካባቢው የሚያስፈልጉ መሠረት ልማቶች ግንባታ እስካሁን ባለመጀመሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ኮሚቴ አቋቋሙ፡፡

የካቢኔ ጉዳዮችና የከንቲባ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ለሁለተኛ ጊዜ ከሙስና ወንጀል ነፃ ሆኑ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የግብዓት አቅርቦትና አስተዳደር መምርያ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሲሠሩ ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመገልገል የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ክስ የቀረበባቸው፣ በቅርቡ የካቢኔ ጉዳዮችና ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ሆነው ተሹመው የነበሩት አቶ በፈቃዱ አሰፋ ለሁለተኛ ጊዜ ከሙስና ወንጀል ነፃ ሆኑ፡፡

የ40/60 የጋራ ቤቶች ዕድለኞች ንግድ ባንክ ግንባታው አልተጠናቀቀም በማለት ሊያስረክበን አልቻለም አሉ

ዕጣ የደረሳቸው ግንባታው ለዘገየበት ወለድ እንዲከፍሉ ተደርጓል በሐምሌ ወር 2009 ዓ.ም. መጀመርያ ሳምንት በዕጣ ከተላለፉ የ40/60 የጋራ መኖርያ ቤቶች፣ በዕጣ ከደረሳቸው የተወሰኑት የሕንፃው ግንባታ ሙሉ በሙሉ እንደተጠናቀቀ ተደርጎ ሙሉ ክፍያ እንዲፈጽሙ የተደረጉት ትክክል አለመሆኑን፣ ሕንፃው ብዙ መጠናቀቅ የሚገባቸው ነገሮች እንደቀሩት ተናገሩ፡፡