Skip to main content
x

ኑሮአችን የውሸት ሞታችን የእውነት እየሆነ ተቸገርን!

እነሆ ዛሬ የምንጓዘው ከቦሌ ወደ ካዛንቺስ ነው። ሁሉም አካባቢ አቋራጭ እንጂ አገር አቋራጭ ባለመሆኑ፣ ከአንድ ራሱ በቀር ተጎታች ሳይኖረው ይሳፈራል። ወያላው ራቅ ብሎ ቆሟል። ‹‹የት ነው?›› እያለ እርስ በርሱ ተጠያይቆ የሚሳፈረው መንገደኛ ብዙ ነው።

ወሬና ንፋስ ምንና ምን ይሆኑ?

እነሆ መንገድ! እነሆ ጉዞ! ከመገናኛ ወደ ስድስት ኪሎ። የጎዳናው ጭብጥ ተደጋጋሚ ነው። ሕይወት ቀለም ያለቀባት ትመስላለች። በመንጋ ቅርፅ አሠልፋ የምትነዳው ሕዝብ እልፍ ነው። ሲቃችን ተያያዥ ነው።

ወይ ጭቅጭቅና ብሽሽቅ?

እነሆ ጉዞ ከኮተቤ ወደ መገናኛ። ምን እንደገጠማቸው ያልታወቀ ሁለት ሴቶች ፊት ለፊት ተላተሙ። “አንችዬ!ምነው ዓይንሽ ቢያይ?” ብላ ግንባሯን እያሸች አንደኛዋ ቆመች።

የድል አጥቢያ አርበኛው በዛሳ?

እነሆ መንገድ። ከጳውሎስ ወደ ፒያሳ ልንጓዝ ነው። አላፊ አግዳሚው ወጪ ወራጁ ከምትፋጀው ፀሐይ ለመጠለል ታዛ እየፈለገ ይሰባሰባል። ተራ አስከባሪዎቹ ‹‹አንድሽም ሳትሠለፊ አትሳፈሪም፤›› እያሉ ያስፈራሩናል። ‹‹እናንተ ሰዎች ለምን አትተውንም ግን? የት እንድረስላችሁ?›› ትላለች የመረራት መሳይ። ‹‹የት ይደረሳል ብለሽ ነው? በየደረሽበት ሁሉ መደብደብ ነው።

ዓሳ የሚጠመደው አፉን ሲከፍት ነው!

እነሆ መንገድ ከመገናኛ ወደ ስድስት ኪሎ። የጎዳናው ጭብጥ ተደጋጋሚ ነው። ሕይወት ቀለም ያለቀባት ትመስላለች። በመንጋ ቅርፅ አሠልፋ የምትነዳው እልፍ ነው። ሲቃችን ተያያዥ ነው። ውክቢያው ዓይን ያጥበረብራል። ደምቆ ካማረበት ይልቅ ገርጥቶ ያስቀየመው ልቋል።

አዋቂ ተንቆ ታዋቂ በዛሳ?

በበዓል ማግሥት እነሆ መንገድ ተጀመረ። የሕይወት አዘቦት አያሳርፍምና የአዳም ዘር ይንቀሳቀሳል፡፡ በማለዳ ከሜክሲኮ ወደ ብሥራተ ገብርኤል ቤት ልንጓዝ ነው። ስትበር ያገኘናት ሚኒባስ ታክሲ ለቃቅማ ሞልታን ቦታ ቦታ ይዘናል። ሁሌም በማንጠፋበት በዚህ መንገድ ሁላችንም የነፍስ አድን ኑሮ ተኮር ሩጫችን ላይ እንረባረባለን። የሩጫችንን ጎዳና ላስተዋለው ትዕይንቱ ዓምደ ብዙ ነው።

ኳስ በመሬት መጫወት ሲያቅት መጠለዝን ምን አመጣው?

እነሆ ከጎተራ ወደ ቄራ ልንጓዝ ነው። “ብርቱካን በልቼ ሎሚ ሎሚ አገሳኝ፣ አንቺ እንደምን አለሽ እኔን ጤና ነሳኝ . . .” የሚለው ዕድሜ ጠገብ ዜማ ይናኛል። የሕዝብ ግጥም በሕዝብ ዜማ ይንቆረቆራል። “የድሮ ሰው የግጥምና የዜማ ድርሰት አይገርምም ግን?” ይላል ጋቢና የተቀመጠ ወጣት መነጽሩን እየወለወለ።

ታዝላችሁ ገብታችሁ ምነው ባታስቁን?

እነሆ ከሽሮ ሜዳ ወደ ሜክሲኮ ልንጓዝ ነው። ‹‹እዚህ ጋ ጠጋ! ጠጋ! ‘ለማዘር’ እዚህ ተጠጉላቸው፤›› የወያላው ተለምዷዊ ቀጭን ትዕዛዝ ናት። ዛሬ ግን መብት አስከባሪ ገጥሞታል። ‹‹አልጠጋም! ለምንድነው የምጠጋው? የከፈልኩህ ለአንድ መቀመጫዬ ብቻ መሰለህ?›› ተጠጊ የተባለችው ወይዘሮው ብልጭ ብሎባታል።

ወደ ላይ እንጂ ወደ ታች ምን ያሳየናል?

እነሆ መንገድ፡፡ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ ልንጓዝ ነው። ጎዳናው በባለርስቶቹ ዘመን ብዙ ለምዶ ኖሮ እንደተወረሰ ሰፊ እልፍኝ፣ ‘ወይኔ! ወይኔ! አልኩኝ ብቻዬን ቀርቼ. . .’ ይባልበት ይዟል። እልፍ ብንሆንም ብቻ ለብቻ ቆመናል። ሐሳቦቻችንና ውጥኖቻችን በሕይወት መድረክ ላይ የተጠላለፉ ነባርና ደብዛዛ መስመሮች ሆነዋል። ያ ወንድሜ እንደማያውቀኝ፣ ያቺ እህቴ እንዳልተዋለደችኝ አቀርቅራ ትጓዛለች።