Skip to main content
x

አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለዚምባብዌ ምርጫ የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢ ቡድን እንዲመሩ ተመረጡ

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ ሐምሌ 23 ቀን 2010 ዓ.ም. በሚካሄደው የዚምባብዌ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በታዛቢነት የሚገኘውን የአፍሪካን ኅብረት ኮሚሽን ቡድን እንዲመሩ ተመረጡ፡፡

የአዲስ አበባ አስተዳደርን የሥልጣን ዘመን ለማራዘም የሕግ ማሻሻያ መቅረቡ ጥያቄ አስነሳ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የከተማ አስተዳደሩ ማቋቋሚያ ቻርተር ተሻሽሎ የሥራ ዘመኑን የጨረሰው የከተማዋ አስተዳደር ምርጫ እስከሚካሄድ በሥልጣን ላይ እንዲቆይ መወሰኑ፣ የሕግ ማሻሻያውም ለፓርላማ መቅረቡ የሕጋዊነት ጥያቄ አስነሳ።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዲስ ፕሬዚዳንት መረጠ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ግንቦት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. አፋር ሰመራ ባደረገው የፕሬዚዳንት ምርጫ ከኦሮሚያ ክልል የተወከሉትን አቶ ኢሳያስ ጅራን አዲሱ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ፡፡

ቀድሞ በተደረገ ምርጫ አቶ ኢሳያስ ከፍተኛውን ድምፅ አግኝተው የነበረ ቢሆንም፣ በፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት 50+1 ድምፅ ባለማግኘታቸው ምርጫው በድጋሚ ተካሄዷል፡፡

በዚህም መሠረት አቶ ኢሳያስ 87 ድምፅ ሲያገኙ፣ አቶ ተካ አስፋው ደግሞ 58 ድምፅ አግኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሒደት ውዝግብ አስነሳ

እሁድ ግንቦት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. በአፋር ክልል ሰመራ በተካሄደው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ከኦሮሚያ ክልል የተወከሉት አቶ ኢሳያስ ጅራ ከፍተኛውን ድምፅ ቢያገኙም፣ በፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ ምክንያት መራጭ ከሆኑ 145 የጠቅላላ ጉባዔ አባላት ከግማሽ በላይ (50+1) ድምፅ ባለማግኘታቸው ጉባዔው በድጋሚ ምርጫ እንዲያደርግ ተገደደ፡፡

አቶ ኢሳያስ 66 ድምፅ አግኝተው የነበረ ሲሆን፣ አቶ ተካ አስፋው 47 ድምፅ አግኝተዋል፡፡ አቶ ጁነዲን ባሻ 28 ድምፅ ሲያገኙ አቶ ተስፋዬ ካህሳይ ደግሞ 3 ድምፅ አግኝተዋል፡፡

አዲሱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የሚታወቅበት የሰመራው ጉባዔ

ከብዙ ንትርክና አተካራ በኋላ ቀጣዩን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት እሑድ ግንቦት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. ለመምረጥ የጠቅላላ ጉባዔ አባላቱ ሰመራ ላይ ከትመዋል፡፡ በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ጣልቃ ገብነት ምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዳግመኛ ከተዋቀረ በኋላ ውዝግብ የተነሳበትን የዕጩ ውክልናን በተመለከተ በርካታ ጥያቄዎችን ሲያስተናግድ ቆይቷል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስና የምርጫ ጨረታ

በካምቦሎጆ ዙሪያ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ የደራና የጦፈ የድለላ ሽሚያ የሚስተዋልበትን ክስተት ከመጋረጃ ጀርባ እያስተናገደ ይገኛል፡፡ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሜቴ ምርጫ ባልተከናወነበት በዚህ ወቅት፣ ጉዳዩ ለጨረታ የቀረበ እስኪመስል የተቋሙ የዋና ጸሐፊነት ቦታና ሌሎችም በንዑስ ኮሚቴ የሚመሩ ልዩ ልዩ ክፍሎች በእነማን እንደሚመሩ ከወዲሁ ለእነማን እንደሚሆን መቃወቅ የጀመረ ይመስላል፡፡

የእግር ኳሱ ጉባዔ ስያሜውን የሚመጥን ውሳኔ እንዲያሳልፍ ተጠየቀ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዓለም አቀፍ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (ፊፋ) የተላከውን የምርጫ ሕግ ለማፅደቅ ለቅዳሜ ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በካፒታል ሆቴል ጠቅላላ ጉባዔውን ጠርቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ጠቅላላ ጉባዔው ፊፋ ባስተላለፈው ትዕዛዝ መሠረት ቀጣዩን የፌዴሬሽኑን ፕሬዚዳንታዊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለመምረጥ የሚያስችለውን አዲስ አስመራጭ ኮሚቴ እንደሚሰየም ይጠበቃል፡፡

ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔውን አሰናብቶ በምትካቸው መረጠ

ላለፉት ሦስት ዓመታት በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ያለው አባተ ያቀረቡትን መልቀቂያ የተቀበለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ በምትካቸው ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂምን አፈ ጉባዔ አድርጎ መርጧል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኞ ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ባካሄደው መደበኛ ጉባዔው፣ ላለፉት ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩት አፈ ጉባዔ ያለው አባተ፣ ከአፈ ጉባዔነታቸው መነሳት እንደሚፈልጉ ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሏል፡፡

ፓርላማው የዘንድሮን ምርጫ ያራዘመበት ሒደት የሕጋዊነት ጥያቄ አስነሳ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዘንድሮ መካሄድ የነበረበትን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤትና የአካባቢ ምርጫን ያራዘመበት መንገድ የሕጋዊነት ጥያቄ አስነሳ፡፡ ምክር ቤቱ ሐሙስ ሚያዝያ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፣ ዘንድሮ መካሄድ የነበረበት ምርጫ ለ2011 ዓ.ም. እንዲሸጋገር በስምንት ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ወስኗል፡፡