Skip to main content
x

‹‹ሁሉም አካላት [ለላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት]  አስፈላጊውን ድጋፍና ቅንጅት እንዲያረጋግጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን›› የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን

እንደሚታወቀው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ከዕድሜ ርዝመት እንዲሁም የተለያዩ ተፈጥሮአዊና ሰው ሠራሽ ምክንያቶች በተለያየ ደረጃ የእርጅናና የስንጥቅ ጉዳት ይስተዋልባቸዋል፡፡ የጥገና ፍላጎትን መሠረት ተደርጎ ላለፉት ዓመታት የተለያዩ የጥገና ትግበራ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

ግምገማዊ አስተያየት በተናፋቂ ትዝታዎቻችን

በተሾመ ብርሃኑ ከማል የመጽሐፉ ርዕስ - ተናፋቂ ትዝታችን የመጽሐፉ ደራሲ - ኮሎኔል መለሰ ተሰማ የመጽሐፉ ገጽ - 232 ኤ5 መጠን መጽሐፉ የክብር ዘበኛ አካዴሚ ሁለተኛ ኮርስ አባላትንና የኮሪያ ጦርነትን የሚያመለክቱ ፎቶግራፎችን ይዟል፡፡ የዘማቾች የስም ዝርዝርም ተካቶበታል፡፡

የአገራችን የትምህርት ጥራት ውድቀት በቀላሉ የሚታይ አይደለም

ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ጥራት መውደቅ ውጫዊና ውስጣዊ ነገሮች ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ውጫዊው አስቀድሜ የጠቀስኩት የመንግሥት አላስፈላጊ ውሳኔዎች፣ የተማሪው ቅድመ ዝግጅትና አስተሳሰቡ፣ የተማሪዎች መብዛት፣ በዚያው ልክ ብቃት ያላቸው መምህራን አለመኖር፣ ቤተ ሙከራዎች አለማዳረስ ወዘተ. ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡

የአገራችን የትምህርት ጥራት ውድቀት በቀላሉ የሚታይ አይደለም

አገሪቱ በአሁኑ ጊዜ በለውጥ ሒደት ላይ ናት፡፡ ይኼም ለውጥ ከዚህ በፊት ከነበሩት ሁሉ ለየት የሚያደርገው ‹‹አገራችንን መምራት ያለብን በነፍጥ ኃይል በማሸነፍ ሳይሆን፣ በፍቅር ተደምረን፣ በመነጋገር አገራችንን እንቀይራት፤››  የሚለው ነው፡፡ ይኼንንም ለውጥ በመቀበል አሉ የሚባሉ አማራጭ አስተሳሰብ ያላቸው ስብስቦች ወደ አገራችን ገብተዋል፡፡

ይድረስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድና ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ

እንደ እኔ ንጉሥም ይሁን ወታደር ወይም ነፃ አውጪ፣ መሪ ማለት በአጭሩ የራሱን ሐሳብ፣ እምነት፣ ግምትና መላምት በሚመራው/በሚወክለው/ ነፃ በሚያወጣው ሕዝብ ላይ በኃይል የሚጭን ሳይሆን፣ የሚመራውን/የሚወክለውን ወይም ነፃ የሚያወጣውን ሕዝብ ፍላጎት ጠይቆ አወያይቶና አጥርቶ ለይቶ፣ አጥንቶ፣ መርምሮና ቀምሮ ሊተገበር የሚችል ዘላቂ ፕሮግራም ነድፎና ዕቅድ አውጥቶ ሕዝቡ ወደሚፈልገው ግብ መርቶ የሚያደርስ ብቻ ሳይሆን፣ ሕዝቡ ከሚፈልገው ግብ በአስተማማኝ መድረሱን የሚያረጋግጥ ጭምር ነው፡፡

የኤርትራ ሙስሊሞች ከሃያ ዓመታት በኋላ  ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቻቸው ጋር ያከበሩት የዓሹራ በዓል

የኤርትራውያን ሙስሊሞች ከሃያ ዓመታት በኋላ የዓሹራ በዓልን መስከረም 10 ቀን 2011 ከኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወንድሞቻቸው ጋር አብረው ለማክበር በቅተዋል። በዓሉ ሁለቱ ወንድማማች ሕዝብ ዳግም የተገናኘበት ነው፡፡  ለመሆኑ የዓሹራ በዓል ለምን በትግራይ በአልነጃሺ መስጊድ ይከበራል? እነማንስ ያከብሩታል? እንደምንስ ይከበራል?

ዓብይ ዓብይ ነው!!

የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የድጋፍና የምሥጋና ሠልፍ ላይ በመስቀል አደባባይ በእስጢፋኖስ አቅጣጫ ተሠልፌ ነበር፡፡ በሠልፉ ላይ ከአንድ ባልና ሚስት አዛውንቶች ጋር አብረን ቆመን የዶ/ር ዓብይን መምጣት እንጠባበቅ ነበር፡፡

ለእኔ ኢትዮጵያዊነት ማለት…

ቀኑ ነሐሴ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ነበር፡፡ በጠዋቱ የልጆች የቡሔ ጭፈራ ድምፅ ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ፡፡ አማራጭ አልነበረኝምና እንደተለመደው ቁርሴን በልቼ ከጨረስኩ በኋላ ሁልጊዜ ቅዳሜ እንደማደርገው ሁሉ፣ ቤቴ ከሚገኝበት ቦሌ ቡልቡላ  ጀምሬ እስከ ሳሪስ ድረስ በእግሬ ለመጓዝ ስል እየተጣደፍኩ ወጣሁ፣ ስፖርት መሆኑ ነው፡፡

ብዙ ገንዘብን በትንሽ ገንዘብ መግዛት

‹‹መጽሐፍ መግዛት ብዙ ገንዘብን በትንሽ ገንዘብ መግዛት ነው፤›› ይህን ጥቅስ ያገኘሁት ከሃያ ዓመት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ የሜጋ መጻሕፍት መደብሮች ውስጥ በአንዱ ነው፡፡ ድንቅ ጥቅስ ነው፡፡