Skip to main content
x

የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ የማምጣት ፈተናና የተደቀነው ማኅበራዊ ቀውስ ሥጋት

የ2011 ዓ.ም. የፌዴራል መንግሥት ረቂቅ በጀት ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ይዘው የቀረቡት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) ያደረጉት የበጀት መግለጫ ንግግርን የአገሪቱን ኢኮኖሚ ጠፍረው ያሰሩ ችግሮችንና ለችግሮቹ ፈጣን መፍትሔ ካልተገኘ ሊፈጠር የሚችለውን ማኅበራዊ ቀውስ ያመላከተ ነበር፡፡

አነስተኛና መካከለኛ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለማስፋፋት የተያዘው ዕቅድ የበጀት ችግር ገጠመው

ከግዙፍ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ጋር ተመጋጋቢ የሚሆኑ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ለማቋቋም የተቀረፀው ፕሮጀክት፣ የሚጠይቀውን ፋይናንስ ማግኘት አለመቻሉ ታወቀ። በፌዴራል መንግሥት የተቀረፀው ይህ ፕሮጀክት በባለቤትነት ተግባራዊ እንዲሆን የሚፈለገው በክልል መንግሥታት ነው፡፡

ኢሕአዴግ ባድመ ለኤርትራ እንድትሰጥ የወሰነውን የአልጀርስ ስምምነት ሙሉ በሙሉ መቀበሉን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ማክሰኞ ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ፣ ባድመ ለኤርትራ እንድትሰጥ የወሰነው የአልጀርሱን ስምምነትና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ እንደወሰነ አስታወቀ፡፡ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አመሻሸ ላይ ባወጣው መግለጫ ከ20 ዓመታት ውዝግብና እሰጥ አገባ በኋላ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የድንበር ማካለል ኮሚሽን የወሰነውንና በሁለቱ መንግሥታት በአልጀርስ የተፈረመውን ስምምነት እንደሚቀበል ይፋ ሲያደርግ ምክንያቱ ምን እንደሆነ አሥፍሯል፡፡

ኢሠማኮ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ሠራተኞችን ማደራጀት እንዳልቻለ ይፋ አደረገ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በተከፈቱ ፋብሪካዎች ውስጥ የሚገኙ ሠራተኞችን የጥቅምና የመብት ጥበቃ ለማረጋገጥ በማኅበር ለማደራጀት ከዚህ ቀደም ይታይ የነበረው ችግር አሁንም እንዳልተፈታና የሠራተኞቹ መነሻ ደመወዝ እንዲስተካከል የተደገው ጥረት ውጤት እንዳላመጣ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አስታወቀ፡፡ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ ሠራተኞች እንዳይደራጁ የአንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት ተፅዕኖ ማድረጋቸውንም ገልጿል፡፡

ከአዋሽ እስከ ኮምቦልቻ ያለውን የባቡር መስመር በዲዝል ኃይል የትራንስፖርት አገልግሎት ለማስጀመር መታቀዱ ተሰማ

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከአዋሽ እስከ ኮምቦልቻ ያለው የባቡር መስመር ከሞላ ጎደል እየተጠናቀቀ በመሆኑ፣ በዲዝል ኃይል የትራንስፖርት አገልግሎት ለማስጀመር ማቀዱን ሪፖርተር ያገኛቸው መረጃዎች አመለከቱ።

የድሬዳዋ አስተዳደር አዲስ ማስተር ፕላን እያዘጋጀ ነው

ለረዥም ዓመታት ዕድገቷ ተገቶ የቆየችው የድሬዳዋ ከተማ አዲስ የተዘረጋው የኢትዮ ጂቡቲ የባቡር መስመርና በመገንባት ላይ ያለው ግዙፍ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሕይወት እየዘራባት በመሆኑ፣ አዲስ የከተማ ማስተር ፕላን በማዘጋጀት ላይ መሆኑን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

አራት የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮችን ለመገንባት የአዋጭነት ጥናት እየተካሄደ ነው

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋት በነደፈው ዕቅድ መሠረት የመጀመርያዎቹ አራት የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮችን ለመገንባት ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት እንደሚያስፈልግ ባለፈው ዓመት ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡ ይኼንን ተከትሎም ሲከናወኑ ከነበሩ ሥራዎች ውስጥ የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮቹን ዕውን ለማድረግ የሚረዱ የአዋጭነት ጥናቶች ሲካሄዱ መቆየታቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚታየውን የሠራተኞች ብዝበዛ ያጣጣለው የዓለም ሠራተኞች ኮንፌደሬሽን ዝቅተኛ የደመወዝ ጣሪያ እንዲደነገግ ጠየቀ

ለሁለት ቀናት በተካሄደውና የአፍሪካ ሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲደነገግላቸው የጠየቀውን ፎረም ያዘጋጀው የዓለም ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን፣ በኢትዮጵያ የሚታየው የሠራተኞች ብዝበዛን ከመንቀፉም በላይ አገሪቱ ለሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚደነግግ ሥርዓት እንድትዘረጋ ጠየቀ፡፡ የዓለም የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ዋና ጸሐፊ ሻረን ባሮው ከረቡዕ ጥር 9 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት የተካሄደውን የአፍሪካ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ፎረም ሲከፍቱ እንደጠየቁት፣ ምንም እንኳ ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ የወደፊቷ የጨርቃ ጨርቅ ማዕከል ስለመሆኗ ቢዘገብም፣ በሠራተኞች ረገድ ግን ብዝበዛ የሚፈጸምባት አገር እንደሆነች በምሳሌ አሳይተዋል፡፡