Skip to main content
x

ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ለኢትዮጵያ ገቢ ንግድ ዋስትና ገባ

ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (አይኤፍሲ) የኢትዮጵያን የገቢ ንግድ ለመደገፍ የብድር ዋስትና ገባ፡፡ ኢትዮጵያን እየጎበኙ የሚገኙት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ፍሊፕ ለ ሆሩ ተቋሙ የኢትዮጵያን የገቢ ንግድ ዘርፍ በተቀመጡ መስኮች ላይ ዋስትና በመስጠት እንደሚያግዝ ሰኞ ታኅሳስ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. አስታውቀዋል፡፡

የዓለም የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ለ500 ሜጋ ዋት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ድጋፍ ሊያደርግ ነው

ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ የተገኙት፣ የዓለም ባንክ አባል ድርጅት የሆነው የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (አይኤፍሲ) የመካከለኛው ምሥራቅና የአፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ሚስተር ሰርጂዮ ፒሜንታ፣ በኢትዮጵያ 500 ሜጋ ዋት የፀሐይ ኃይል የሚያመነጩ ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው አስታወቁ፡፡

ኢትዮጵያ ተቋርጦ የነበረው የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር እንዲጀመር ጠየቀች

ላለፉት ስድስት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር እንዲንቀሳቀስ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቀረበች፡፡ የዓለም ባንክ የመረጃና የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር ኪዝ ሮልዌል ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ እ.ኤ.አ. በ2012 ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት በድጋሚ እንዲንቀሳቀስ ጥያቄ ቀርቧል፡፡

ንግድ ሚኒስቴር አወዛጋቢ የነበሩ ሁለት መመርያዎችን አሻሻለ

ንግድ ሚኒስቴር አወዛጋቢ ሆነው የቆዩትን የቅድመ ንግድ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫና የኢትዮጵያ የንግድ ሥራ ፈቃድ መስጫ መደብ መመርያዎችን አሻሻለ፡፡ እነዚህ መመርያዎች በኢትዮጵያ በቀላሉ የንግድ ሥራዎችን ለማካሄድ እንቅፋት ናቸው ተብለው በንግዱ ማኅበረሰብ ከፍተኛ ቅሬታ የሚቀርብባቸው ናቸው፡፡

የፓርላማ አባላት በአገሪቱ የውጭ ዕዳ ክምችት ሥጋታቸውን ገለጹ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በአገሪቱ የውጭ ዕዳ ክምችት ላይ ያላቸውን ሥጋት ገለጹ፡፡ የፓርላማ አባላቱ ሥጋታቸውን ጠንከር ብለው የገለጹት፣ ሐሙስ ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ለምክር ቤቱ የቀረበውን የብድር አዋጅን ለማፅደቅ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡ ለምክር ቤቱ የቀረበው ለሁለት ፕሮጀክቶች መንግሥት ከዓለም ባንክ ጋር ያደረገው ስምምነት ቢሆንም የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ መንግሥት የፈቀደው ብድር በገበያ ዋጋ የሚተመን ወለድ የተጣለበት መሆኑ፣ የምክር ቤቱ አባላት ሥጋታቸውን እንዲያነሱ ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡

የብር ምንዛሪ ለውጥ የወጪ ንግዱን አሻሽሎታል ተባለ

ከዓመት ዓመት አልሳካ ያለውን የወጪ ንግድ ለማሳደግ በማሰብ በጥቅምት ወር 2010 ዓ.ም. የተደረገው የብር የምንዛሪ ለውጥ፣ የአገሪቱን የወጪ ንግድ ገቢ እንዳሻሻለው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ መንግሥት የብርን የመግዛት አቅም በ15 በመቶ መቀነሱ የሚታወስ ነው፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ የወጪ ንግድ ግኝት ከዕቅዱ አኳያ እምብዛም የተሳካ ባይሆንም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር መሻሻል እንዳሳየ ተናግረዋል፡፡

የዓለም ባንክ የ600 ሚሊዮን ዶላር ብድርና ዕርዳታ አፀደቀ

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ መንግሥት 600 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታና ብድር ሰጠ፡፡ የብድሩ ስምምነቱን የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የደቡብ ሱዳን ዋና ዳይሬክተር ሚስ ካሮሊን ተርክ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) ማክሰኞ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ተፈራርመዋል፡፡

በዓለም ባንክ ድጋፍ 200 ሺሕ አቅመ ደካሞች በምግብ ዋስትና ፕሮግራም ሊታቀፉ ነው

የዓለም ባንክ ከመደበው 450 ሚሊዮን ዶላር በጀት 70 በመቶ ድርሻ የያዘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በተያዘው በጀት ዓመት ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ 200 ሺሕ ነዋሪዎችን በምግብ ዋስትና ፕሮግራም እንደሚያቅፍ አስታወቀ፡፡ አስተዳደሩ ከተያዘው በጀት 32 ሺሕ ለሚጠጉ ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ አቅመ ደካሞች ቀጥታ ወርኃዊ ክፍያ ለመፈጸም፣ 168 ሺሕ የሚሆኑ ነዋሪዎች ደግሞ በማኅበረሰብ አቀፍ ፕሮግራም ታቅፈው የተለያዩ ሥራዎችን ሠርተው ወርኃዊ ክፍያ እንዲያገኙ ዕቅድ አውጥቷል፡፡

የዓለም ባንክ በስድስት ወራት ብቻ የ1.8 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ

በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ካሮሊን ተርክ ሐሙስ ታኅሳስ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ከገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) ጋር የ470 ሚሊዮን ዶላር ብድር ስምምነቶችን ሲፈርሙ እንደገለጹት፣ ባንኩ በተቻለው ፍጥነት የፋይናንስ ድጋፎችን ለማድረግ ካለው ፍላጎት በመነሳት እ.ኤ.አ. በ2017 ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ የ1.8 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገብቷል፡፡