Skip to main content
x

በቦምብ ፍንዳታው የተጠረጠሩ የፖሊስ አመራሮች በገንዘብ ዋስትና እንዲፈቱ ተፈቀደላቸው

ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ የቦምብ ፍንዳታ የሥምሪት ክፍተት በመፍጠር የተጠረጠሩት የአዲስ አበባና የፌዴራል ፖሊስ አመራሮች፣ ዛሬ ነሐሴ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. የገንዘብ ዋስትና ተፈቀደላቸው፡፡

ዓቃቤ ሕግ ቦምብ በመወርወርና በማቀበል በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ክስ ሊመሠርት ነው

የፌዴራ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለመደገፍ በወጡ ሰዎች ላይ፣ ቦምብ በመወርወር በተጠረጠረው ጥላሁን ጌታቸውና ቦምቡን በማቀበል በተጠረጠረው ብርሃኑ ጃፋር ላይ ክስ ሊመሠርት ነው፡፡

በጅግጅጋና በሌሎች የሶማሌ ክልል ከተሞች የተቀሰቀሰው ግጭት የፈጠረው ውጥረት

ቅዳሜ ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የተቀሰቀሰው ግጭት በቀብረ ደሃር፣ በጎዴና በደገሃቡር ከተሞችም በመስፋፋት የክልሉ ብሔር አባላት ባልሆኑ ነዋሪዎች ላይ ያነጣጠረ ጉዳት ደርሷል፡፡

መኢአድ አንቀጽ 39 እንዲሰረዝ ጠየቀ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አገር ለማፍረስ የተቀመጠ ነው ያለውን የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 እንዲሰረዝ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ፓርቲውን ይህን ጥያቄ በይፋ ያቀረበው ሐሙስ ነሐሴ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ‹‹አገር ለማፍረስ የተቀመጠው አንቀጽ 39 የወለደው ችግር የበርካታ ዜጎችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል፤›› በማለት፣ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽሕፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ቁልፍ ቦታዎችን ይዘው የቆዩ ሁለት ባለሥልጣናት ተነሱ

ላለፉት አሥር ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቁልፍ ቦታዎችን ይዘው ሲመሩ የቆዩት አቶ ተወልደ ገብረ ፃድቃንና አቶ ኃይሌ ፍሰሐ ከሥልጣናቸው ተነሱ፡፡ አቶ ተወልደ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት ዋና አማካሪ፣ እንዲሁም በከተማው ሙሉ ሥልጣን ያለው የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ ሹም ሽር አካሄደ

ዓርብ ነሐሴ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. አስቸኳይ ስብሰባ የተጠራው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት፣ መሠረታዊ በሚባል ደረጃ የካቢኔ ሹም ሽር አካሄደ፡፡ በዕለቱ ሹመት ከተሰጣቸው 18 የቢሮ ኃላፊዎች መካከል አራቱ ብቻ ነባር ሲሆኑ፣ የተቀሩት በሙሉ አዳዲስ ተሿሚዎች ናቸው፡፡

በሶማሌ ክልል በተፈጠረው ቀውስ የነዳጅ ኩባንያዎች ሥራ አቋርጠዋል

በሶማሌ ክልል በተፈጠረው የፖለቲካና የፀጥታ ቀውስ ሥጋት የገባቸው በክልሉ የነዳጅ ፍለጋ ሥራ የሚያካሂዱ ኩባንያዎች ሥራ ማቋረጣቸው ታወቀ፡፡ በክልሉ በተፈጠረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ከሐምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በክልሉ ዋና ከተማ ጅግጅጋና ሌሎች አነስተኛ ከተሞች በተፈጠሩ ግጭቶች በርካታ ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸው፣ የንግድና የመኖሪያ ቤቶች፣ ባንክና ቤተ ክርስቲያኖች መዘረፋቸውና መቃጠላቸው የሚታወስ ነው፡፡

የቀንጢቻ ታንታለም ማውጫ እየተዘረፈ ነው

በኢትዮጵያ ማዕድን፣ ነዳጅና ባዮፊውል ኮርፖሬሽን ሥር የሚተዳደረው የቀንጢቻ የታንታለም ማዕድን ማውጫ በግለሰቦች እየተዘረፈ እንደሆነ ተገለጸ፡፡ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ጉጂ ዞን ሰባ ቦሩ ወረዳ፣ ልዩ ስሙ ቀንጢቻ በተባለ ሥፍራ የሚገኘው የታንታለም ማዕድን ማውጫ ከታኅሳስ 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ማምረት ማቋረጡ ይታወሳል፡፡

ሕወሓት በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ ማሻሻያዎችን ሊያደርግ መሆኑ ተሰማ

ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) በመተዳደርያ ደንቡ ላይ መጠነኛ ማሻሻያ ለማድረግ ረቂቅ ሰነድ ማዘጋጀቱን፣ ከነሐሴ አጋማሽ በኋላ በሚካሄደው በድርጅቱ ጠቅላላ ጉባዔም ተወያይቶ እንደሚያፀድቀው ተጠቆመ፡፡