Skip to main content
x

በአካል ጉዳተኞች ስም ሙስና እየተፈጸመ መሆኑ ተነገረ

በኢትዮጵያ በሚገኙ የአካል ጉዳተኞች ስም ከተለያዩ የዓለም አገሮች በርከት ያለ የገንዘብና የቁሳቁስ ዕርዳታ የሚገኝ ቢሆንም፣ እነሱን መነሻ አድርገው ለተቋቋሙ ድርጅቶች መጠቀሚያ የሚውል መሆኑንና ይህም ድርጊት ሙስና እንደሆነ አካል ጉዳተኞች ተናግረዋል፡፡

ክስ የተቋረጠላቸው ሁለት ባለሀብቶች ከውጭ ተመለሱ

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ከተመሠረተባቸው ታዋቂ ባለሀብቶች መካከል ክሳቸው የተቋረጠላቸው ሁለት ባለሀብቶች ወደ አገር ቤት ተመለሱ፡፡ በቅርቡ ክሳቸው የተቋረጠላቸውና ወደ አገር ቤት የተመለሱት ባለሀብቶች አቶ ጌቱ ገለቴና አቶ ገምሹ በየነ ናቸው፡፡ አቶ ጌቱ በሙስና ወንጀል መጠርጠራቸው ተገልጾ በቁጥጥር ሥር ከመዋላቸው በፊት ከአገር መውጣታቸው የተነገረው፣ ከአምስት ዓመታት በፊት እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ወደ አገር ቤት እስከተመለሱ ድረስ ዱባይ ይኖሩ ነበር፡፡

በሙስና ተጠርጣሪዎች መፈታት መልስ ያላገኙ ጥያቄዎች

ባለፉት ሦስት ዓመታት አገሪቱን ያናወጠውን ሕዝባዊ አመፅና ተቃውሞ ለማርገብና ኅብረተሰቡ ሲያነሳቸው ለነበሩ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሆኑ በማሰብ፣ አራቱ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) አባል ድርጅቶች ሊቃነ መናብርት ታኅሳስ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት የጋራ መግለጫ፣ የላቀ አገራዊ መግባባት ለማምጣትና የዴሞክራሲ ምኅዳሩን ለማስፋት እንዲያስችል፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር የሆኑና ሌሎች ግለሰቦች ከእስር እንዲፈቱ ተወስኖ ነበር፡፡

ቻይናዊው የኦሞ ኩራዝ አምስት ስኳር ፕሮጀክት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሳቸው በገለልተኛ አካል እንዲታይ ጥያቄ አቀረቡ  

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው እ.ኤ.አ. ጁላይ 25 ቀን 2017 በቁጥጥር ሥር የዋሉትና ክስ ተመሥርቶባቸው በእስር ላይ የሚገኙት የኦሞ ኩራዝ አምስት ስኳር ፕሮጀክት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚኒተር ዩዋን ጂያሊን፣ የተመሠረተባቸው ክስ በገለልተኛ አካል እንዲታይላቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በደብዳቤ ጥያቄ አቀረቡ፡፡

የመንግሥት ውሳኔዎች ምክንያታዊ ይሁኑ!

መንግሥት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይወስናል፡፡ ከብሔራዊ ጉዳዮች ጀምሮ በአኅጉራዊና በዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች በርካታ ውሳኔዎች ላይ ይደርሳል፡፡ ሁሉም ውሳኔዎች የሕዝብን መብትና ጥቅም፣ የአገርን ክብርና ብሔራዊ ደኅንነት ማስጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ውሳኔዎች እነዚህን መሠረታዊ ፍላጎቶች መነሻ አድርገው ሲተላለፉ፣ በዜጎች ዘንድ ይሁንታና ከበሬታ ያገኛሉ፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና እነ አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ 771 ሰዎች ከእስር ተፈቱ

በሽብርተኝነት የተፈረጀው የግንቦት ሰባት ድርጅት ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት እነ አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ፣ 771 ተከሳሾችና ፍርደኞች በይቅርታና ክስ በማቋረጥ ከእስር እንዲፈቱ ተደረገ፡፡

በሙስና ምክንያት የታሰሩ ተከሳሾች ቤተሰቦች ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ አቤቱታ አቀረቡ

የልጆቻቸውን የትምህርት ቤትና የቤት ኪራይ መክፈል እንዳልቻሉ የሚናገሩ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸውና በማረሚያ ቤት የሚገኙ የስኳር ኮርፖሬሽን የተወሰኑ ታሳሪዎች ቤተሰቦች፣ በቅርቡ ለተሾሙት የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቤቱታ አቀረቡ፡፡ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬም በአግባቡ ተቀብለውና አቤቱታቸውን ሰምተው ምላሽ እንደሚሰጧቸው በመንገር መልሰዋቸዋል፡፡

የ152 የሙስና ወንጀል ተከሳሾች ቤተሰቦች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቤቱታቸውን አቀረቡ

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው 152 የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎችና ሠራተኞች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አቤቱታ ካቀረቡ በኋላ፣ ከ60 በላይ የሚሆኑ ቤተሰቦቻቸው በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ተገኝተው አቤቱታቸውን አሰሙ፡፡

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱ 152 እስረኞች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቤቱታ አቀረቡ

ተለያየ የሙስና ወንጀል ተግባር ተጠርጥረው የታሰሩና ክስ ተመሥርቶባቸው የሚገኙ 152 ግለሰቦች፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የአቤቱታ ደብዳቤ ጻፉ፡፡ ተከሳሾቹ በቀጥታ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ዘርፍ በቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር በኩል እንዲደርስላቸው፣ ሰባት ገጽ አቤቱታ መጻፋቸውን ሪፖርተር ከምንጮች አረጋግጧል፡፡

በዓለም የሙስና መመዘኛ ኢትዮጵያ ሙሰኛ ከሚባሉ አገሮች ተርታ ተመድባለች

ዓለም አቀፍ የሙስና መመዘኛ መስፈርቶችን በማውጣት ለዓመታት የአገሮችን ደረጃ ሲያወጣ የኖረው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ዓመታዊ ሪፖርት መሠረት፣ ኢትዮጵያ ሙሰኛ ከሚባሉ አገሮች ተርታ እንደምትመደብ አስፍሯል፡፡