Skip to main content
x

ሮጠን ብንቀድምም ቆመን እየጠበቅን ነው!

ሰላም! ሰላም! እንዴት አላችሁ? ይኸው እኔ እንዲህ ትንፋሽ የማይሰጥ ትውስታ እየደራረበ የሚነጉድ ዘመን ይመጣል ሳልል ‘ፉል’ እያለ ባስቸገረኝ ‘ሚሞሪዬ’ ተወጥሬ አለሁላችሁ። ይኼ የ‘ዲጂታል’ ዘመን ከእኔ በባሰ ባሻዬን ክፉኛ አሥግቷቸዋል።

ለመተማመንም እንፈራረም እንዴ?

ሰላም! ሰላም! አንዱ በቀደም ሰተት ብሎ በጠዋቱ ቤቴ መምጣቱ፣ ስንተዋወቅ እኮ ገና ሰባት ቀናችን ነው። ማንጠግቦሽ፣ ‹‹እንኳን ሰባት ቀን ሰባት ደቂቃ ቆሞ የሚያወራህ በጠፋበት በዚህ ጊዜ እንዲህ አትበል. . . ›› እያለች ለምሳ የቆጠበችውን ለእንግዳው ጨምራ ቁርስ ታቀርባለች።

ኃጢያታችንንና ሒሳባችንን እኩል ብናወራርድስ?

ሰላም! ሰላም! ውዷ ማንጠግቦሽ ስወጣ ስገባ፣ ‹‹አደራ ጠንቀቅ እያልክ?›› ስትለኝ ሰነበተች። ‘በተጠንቀቅና በመጠንቀቅ የምናመልጠው ስንቱን ይሆን?’ እያልኩ በውስጤ ‹‹ምኑን?›› ስላት፣ ‹‹ይኼን የሰሞኑን ቫይረስ ነዋ!›› አለች ጭንቅ ብሏት።

‹ለሁሉም ጊዜውን ይጠብቅለታል…›

ሰላም! ሰላም! ‹‹የጊዜ እንጂ የሰው ጀግና የለውም›› ይባል ነበር አሉ፡፡ ጊዜ ይህንን ያህል ክብር ሲያገኝ እኛ ለምን እንረክሳለን? ግራ ይገባኛል፡፡ የጊዜ ነገር ሲነሳ ብዙ የሚባሉ ጉዳዮች አሉ፡፡ ጊዜን የመሰለ ዳኛ እያለ እንዴት አይባልም፡፡ የሰሞኑ አገርኛ ጉዳያችን ከሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እስከ የአገር ሀብት ዘረፋ ተጠርጣሪዎች ላይ መሆኑ ደርሶ እንደ ወፈፌ ብቻዬን ያስቀባጥረኛል፡፡

ተመርምረን ቢለይልንስ?

ሰላም! ሰላም! ባሻዬ ሰሞኑን በጠና ታመዋል። ሕመማቸው የተፈጥሮ አይደለም። ነገሩ ወዲህ ነው። ልጃቸው በውርጃ ዙሪያ የተሠራ አንድ ጥናት እያነበበ ወደ ቤት ይገባል። እሳቸው ሰዓተ ዜና ያዳምጣሉ፣ ድንገት መብራት ይጠፋል። ላለመበሳጨት ወደ ቀኝ ሲዞሩ ልጃቸው የለም። ይዞት የነበረው ወረቀት ክንፉን እንደ አውራ ንስር ዘርግቶ ተኝቷል። እንደ ቀልድ ብድግ አድርገው ባትሪያቸውን አብርተው ማንበብ።

ብንተሳሰብስ?

ሰላም! ሰላም! እነሆ ለሰፊው ሕዝብ ጥቅም ስል ጨዋታዬን ልጀምር ነው። ጠቅሞ ስለመጠቀም ካነሳን ዛሬ የምንለያይ አይመስለኝም። እንዴት ይዟችኋል? ሕዝብና ስፋት አብሮ ሲጠመድ ለወግና ለፖለቲካ እንደሚመች ምን ሌላ ነገር ሲመች አይታችኋል? ምንም! ደላላ ነኝና ይህችን ይህችን ለእኔ መተው ያዋጣል! ታዲያ ይኼ የመጠቃቀም ፖለቲካ ለመዘወር የመመቸቱን ያህል አያይዞ ገደል የከተተ ጊዜ አይጣል ነው።

የአሉባልታ ፈረስ ካሰቡት አያደርስ!

ሰላም! ሰላም! ሐሜቱ፣ አሉባልታው፣ መውጣቱ፣ መውረዱ እንዴት እያደረጋችሁ ነው? ‹‹እንደ እንስሳ ሆዱን መቼ ይመለከታል፣ ሰው ፍቅር ካገኘ ምግብማ ሞልቷል፤›› ያለው የአገራችን ሙዚቃ ንጉሥ ትዝ እያለኝ እኔ እንዳለሁ አለሁ። ደብዳቤ አስመሰልኩት እንዴ? ምን ይደረግ ሰው በነገር ሆዱን ሲታመም ንግግሩ ሁሉ ብሶት፣ ብሶቱ ደግሞ ደብዳቤ መምሰሉ አይቀሬ ነው። ሰው ደግሞ እንደምታውቁት ነው።

መውደድስ አገርን ነው!

ሰላም! ሰላም! ኑሮው፣ ወሬው፣ ሥራው፣ ፓርላማው፣ አዳዲሶቹ ሹማምንት እንዴት ሰነበቱ? በጣም የማፈቅራት ውድ ባለቤቴ ማንጠግቦሽ ሰሞኑን ኮራ ብላለች፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ ግማሹ በሴቶች መሞላቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተመቻት ማለት አይገልጸውም፡፡

እስኪ ዱብ ዱብ!

ሰላም! እንዴት ይዟችኋል? ያው እኔም እንዳቅሚቲ ሮጥ ሮጥ እያልኩ ፑሽ አፕ እየሠራሁ ጤንነቴን ስንከባከብ ነበር፡፡ ይህንን የሰሞኑ ተግባሬን የታዘበችው ውዷ ማንጠግቦሽ በአሽሙር፣ ‹‹ደግሞ ምን አስበህ ነው ላይ ታች የምትለው?›› ስትለኝ ባላየ ባልሰማ በዝምታ አለፍኳት፡፡