Skip to main content
x

የዳንጎቴ ሲሚንቶ ሥራ አስኪያጅና ሠራተኞች ገዳዮችን ለመያዝ ከፍተኛ አሰሳ እየተካሄደ ነው

ረቡዕ ግንቦት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀኑ አሥር ሰዓት ላይ በጥይት ተደብድበው የተገደሉት የዳንጎቴ ሲሚንቶ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ጸሐፊና ሾፌር ገዳዮችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት ከፍተኛ አሰሳ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ተባብሶ መቀጠሉ ተገለጸ

መንግሥት ከፍተኛ የገንዘብና የእስራት ቅጣት የሚጥል ሕግ ያወጣ ቢሆንም፣ በተደራጀና ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ ሕጉን ተግባራዊ ሊያደርግ ባለመቻሉ በሕገወጥ ደላሎች የሰዎች ዝውውር ተባብሶ መቀጠሉ ተገለጸ፡፡ ከአራት ዓመታት በፊት በተለይ በሳዑዲ ዓረቢያ በቤት ሠራተኝነትና በሌሎች ሥራዎች ተሠማርተው በነበሩ ኢትጵያውያን ላይ በደረሰው ግድያ፣ አካል ማጉደልና ከፍተኛ እንግልት ምክንያት መንግሥት ዜጎች ወደ መካከለኛው ምሥራቃዊ አገሮች እንዳይጓዙ ዕግድ ጥሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡

የቀድሞ የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነርን ጨምሮ 29 ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ

በጋምቤላ ክልል በማዣንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ ሜጢ ከተማ ውስጥ በተፈጠረ ግጭት ለ79 ሰዎች ሞት፣ ለ27 ሰዎች ከፍተኛና ዝቅተኛ የአካል መጉደል፣ ለ273 መኖሪያ ቤቶች መቃጠል፣ ከ13,000 በላይ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ አድርገዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው፣ የቀድሞ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነርን ጨምሮ 29 ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ፡፡

የፍትሕ አካላት ነፃነትና ገለልተኝነት ከፍተኛ ትግል ያስፈልገዋል!

የፍትሕ መለያ የሆነችው ዓርማ ዓይኗ በጨርቅ መሸፈኗ የገለልተኝነት ተምሳሌት ነው፡፡ ይህ ተምሳሌት የፍትሕ አካላትን ነፃነትና ገለልተኝነት ይወክላል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ግን ኢትዮጵያ የጎደላት ከየትኛውም የተቋም ግንባታ ይበልጥ፣ ከየትኛውም ፓርቲ ወይም ቡድን ርዕዮተ ዓለም ጭምር ገለልተኛ የሆነ የፍትሕ ተቋም ነው፡፡ የኢትዮጵያ የፍትሕ ተቋማት ቋንቋ፣ አደረጃጀትና መፈክር ከሕገ መንግሥት ይልቅ ለፓርቲ ‹‹መስመር›› ይበልጥ የገበረ ነው፡፡

የፍትሕ ተቋማት በሚያገናኟቸው የሥራ ዘርፎች ውጤታማ ሥራ እያከናወንን ነው አሉ

አምስቱ የፍትሕ ተቋማት የሚባሉት የፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያገናኟቸው የሥራ ዘርፎች ላይ ውጤታማ ሥራ እያከናወኑ መሆኑን አስታወቁ፡፡

በኮማንድ ፖስቱ ታስረው የነበሩ የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ ምክትል አዛዥና የፍትሕ ቢሮ ቃል አቀባይ ተፈቱ

የካቲት 9 ቀን 2010 ዓ.ም. የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና ተግባራዊ መሆን የሚገባቸውን ድንጋጌዎች ተላልፈዋል ተብለው በኮማንድ ፖስቱ ታስረው የከረሙት፣ የኦሮሚያ ክልል ልዩ አድማ በታኝ ፖሊስ ምክትል አዛዥ፣ የፍትሕ ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን  ኃላፊና የአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህር ከእስር ተፈቱ፡፡

እነ እስክንድር ነጋ የዋስትና መብት ቢከበርላቸውም አልተፈቱም

እሑድ መጋቢት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ዓርማ የሌለው ሰንደቅ ዓላማ በመጠቀማቸው ምክንያት በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዷለም አራጌና ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ 11 ግለሰቦች በዋስትና እንዲፈቱ ቢፈቀድላቸውም፣ እስካሁን እንዳልተፈቱ ቤተሰቦቻቸው ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

በእስር ላይ የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት ማን እንዳሰራቸው ፍርድ ቤትን ጠየቁ

በሽብር ተግባር ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው ሁለት የዋልድባ መነኮሳት፣ ማን እንዳሰራቸው እንዲገለጽላቸው ለፍርድ ቤት ጥያቄ  አቀረቡ፡፡ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ጥያቄውን ያቀረቡት፣ አባ ገብረ ሥላሴ ወልደ ሃይማኖትና አባ ገብረየሱስ ኪዳነ ማርያም ናቸው፡፡ መነኮሳቱ ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት ‹‹ማነው ያሰረን?›› ጥያቄ ላይ እንደተናገሩት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታኅሳስ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ባሰሙት አዋጅ የተከሰሱበት ጉዳይ ቀርቶ እንዲፈቱ ውሳኔ አስተላልፈዋል፡፡

በቅርቡ ከእስር የተፈቱ 11 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

እሑድ መጋቢት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አቶ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ 11 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡ የመታሰራቸው ዋና ምክንያት ሕጋዊ ያልሆነ ወይም መሀሉ ላይ ያለውን ዓርማ ያልያዘ ልሙጥ ሰንደቅ ዓላማ ሰቅለው በመገኘታቸው መሆኑን ፖሊስ መናገሩ ታውቋል፡፡