Skip to main content
x

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደንበኞቹን ችግር መፍታት ያልቻለው በማስፈጸም አቅምና በግብዓት አቅርቦት ችግር ነው አለ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደንበኞቹን ችግር መፍታት ያልቻለው፣ የሰው ኃይል የማስፈጸም አቅም ውስን በመሆኑና በግብዓት አቅርቦት ችግር እንደሆነ አስታወቀ፡፡

ኢትዮጵያ ለከተሞችና ለጂኦተርማል ልማት 18 ሚሊዮን ዩሮ ዕርዳታ አገኘች

የኢትዮጵያ መንግሥት ለከተሞችና ለጂኦተርማል ልማት ኃይል 18 ሚሊዮን ዩሮ (569.6 ሚሊዮን ብር) ዕርዳታ አገኘ፡፡ ዕርዳታው የተገኘው ከፈረንሣይ መንግሥት አሥር ሚሊዮን ዶላር፣ ከአውሮፓ ኅብረት ስምንት ሚሊዮን ዩሮ በአጠቃላይ 18 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡

ልማት ፈንድ ለ16 ከተሞች የ1.1 ቢሊዮን ብር የብድር ስምምነት በማድረግ ዓመቱን አጠናቀቀ

የውኃ ልማት ፈንድ ጽሕፈት ቤት፣ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ፋይናንስ የሚደረጉበት ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ የተዘዋዋሪ ብድር ለ16 ከተሞች በማቅረብ የ2010 በጀት ዓመት እንቅስቃሴውን አሳርጓል፡፡ ጽሕፈት ቤቱ ሰሞኑን ከከተሞቹ ጋር ባደረገው የብድር ስምምነት መሠረት፣ ከ16ቱ መካከለኛና አነስተኛ ከተሞች ጋር ለንጹህ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ግንባታ የሚውል የ1.1 ቢሊዮን ብር የተዘዋዋሪ ብድር ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የኢንቨስትመንት ተቋም ተባለ

በየዓመቱ በዱባይ አዘጋጅነት በሚካሄደው ዓለም ዓቀፉ የኢንቨስትመንት ጉባዔ፣ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ውጤታማ አፈጻጸም ያሳዩ አገሮች ተወዳድረው በሚሸለሙበት መድረክ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ የዘንድሮውን ሽልማት ማሸነፍ ችሏል፡፡

ለሁለተኛው ዙር የከተሞች ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ሁለት ቢሊዮን ብር ተመድቧል

ሁለተኛው ዙር የከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም 250 ሺሕ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ታወቀ፡፡ ለዚህም ሁለት ቢሊዮን ብር በጀት የተመደበ ሲሆን፣ 200 ሺሕ የሚሆኑት ተጠቃሚዎች የደሃ ደሃ የሆኑ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ናቸው፡፡

ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ ነዋሪዎችን አንድ ዕርምጃ ለማሻገር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ድሪባ ኩማ ረቡዕ ሚያዝያ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. አስተዳደራቸው ጉልህ ሥፍራ ከሚሰጣቸው ፕሮግራሞች አንዱን ጎብኝተዋል፡፡ ከንቲባ ድሪባ ከከፍተኛ የከተማው ባለሥልጣናት ጋር ሆነው የጎበኙት በአዲስ አበባ ከተማ ከደኅንነት ወለል በታች የሚገኙ ነዋሪዎችን ለማቋቋም በዓለም ባንክ የሚደገፈውን ግዙፍ ፕሮግራም ነው፡፡

ሥራ ነጣቂ ሮቦቶች ለኢትዮጵያም ሥጋት እንደሚሆኑ ተተነበየ

ከጥቂት ወራት በፊት የዓለም ኢኮኖሚያዊ ሁኔታን በሚተነትነው ሪፖርቱ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም የንግድና የልማት ጉባዔ (UNCTAD) በአዲስ አበባ ይፋ ያደረገው አፍሪካ የሮቦቶች መምጣት ቢያንስ ለአሁኑ እንደማያሠጋት ነበር፡፡

የውኃ ልማት ፈንድ በአንድ ወር ውስጥ ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር ስምምነት ፈረመ

የውኃ ልማት ፈንድ ጽሕፈት ቤት በአብዛኛው ለመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ግንባታ የሚውል ብድር በማቅረብ ላይ የሚገኝ ተቋም ሲሆን፣ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከ1.1 በቢሊዮን ብር በላይ በጋራ ፋይናንስ መርህ መሠረት ከስምንት አነስተኛ ከተሞች ጋር የብድር ስምምነት ተፈራርሟል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ ሪፖርት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት ወደ ስድስት በመቶ ዝቅ ያደረገ ትንበያ አስቀምጧል

የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ ጥር 9 ቀን 2010 ዓ.ም. በኮትዲቯር ዋና ከተማ አቢጃን ይፋ ያደረገው ሪፖርት፣ ከቃኛቸው አገሮች ውስጥ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴም ተቃኝቷል፡፡ ባንኩ ‹‹አፍሪካን ኢኮኖሚክ አውትሉክ፣ 2018›› በሚል ርዕስ ይፋ ያደረገው ሪፖርት የአፍሪካ አገሮችን ኢኮኖሚያዊ ክንውን ከመዳሰስ ባሻገር በመጪዎቹ ዓመታት ማለትም እ.ኤ.አ. እስከ 2019 ሊታዩ የሚችሉ ኢኮኖሚያዊ ትንበያዎችንም አስፍሯል፡፡

ቦታውን እያስረከበ የመጣው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከባለሁለት አኃዝ ዕድገት ተራርቋል 

ተሰናባቹ የምዕራባውያኑ 2017 በርካታ ክስተቶችን አስተናግዷል፡፡ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ በግዙፉ ከሚጠቀሱ ክስተቶች መካከል መንግሥት የወሰደው የ15 በመቶ የምንዛሪ ለውጥ አንዱ ነው፡፡ አገሪቱ በኢኮኖሚ ረገድ ከምሥራቅ አፍሪካ ግዙፍ በመሆን ኬንያን ስለመብለጧም ይፋ የተደረገው በተካተተው ዓመት ነበር፡፡ የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ያወጣው ሪፖርትም ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው የ8.3 በመቶ ዕድገት በዓለም ትልቁ በመሆኑ ቀዳሚነቱን ይዞ እንደነበር ማስነበቡ ይታወሳል፡፡