Skip to main content
x

ቅዱስ ሲኖዶስ ግብፅ በዴር ሡልጣን ገዳም እየፈጠረች ላለው ችግር መንግሥት መፍትሔ እንዲያስገኝ ጠየቀ

ግብፅ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ዴር ሡልጣን ገዳም ይዞታ ላይ እየፈጠረች ያለውን አሳሳቢ ችግር መንግሥት አስፈላጊውን መፍትሔ እንዲያስገኝ ቅዱስ ሲኖዶስ ጠየቀ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለ11 ቀናት ያካሄደውን ጉባዔ ማጠናቀቁን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፣ የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ በይዞታችን ላይ አግባብነት የሌለው ሥራን የማደናቀፍና በታሪክም ሆነ በማንኛውም የሰነድ መረጃ የሌለው የባለቤትነት ጥያቄ በማንሳት እየተፈጠረ ያለውን አላስፈላጊ ሁከትና ብጥብጥ ማቆም አለባቸው ብሏል፡፡

የቅዱስ ላሊበላ የታደጉን ድምፆች

‹‹ታሪክና ቅርስ እየፈረሰ አዲስ ታሪክ አይሠራም፣ ቅርሳችን ሲፈርስ እያየን ዝም አንልም፣ ላሊበላን መታደግ ኢትዮጵያን መታደግ ነው. . .›› እነዚህንና መሰል ኃይለ ቃሎችን በሰሌዳ ይዘው በላሊበላ ከተማ ሠልፍ የወጡ ያስተጋቡት ድምፅ ነው፡፡

በጥንታዊ ጽሑፎች ላይ የሚመክረው ዓለም አቀፍ ጉባዔ

ኢትዮጵያ በመንግሥታቱ ድርጅት የባህል ተቋም ዩኔስኮ ይሁንታ አግኝተው በዓለም ቅርስነት ካስመዘገበቻቸው የማይዳሰሱና የሚዳሰሱ ሀብቶች በተጨማሪ ከጥንታዊ የሥነ ጽሑፍና የሥነ ጽሕፈት ሀብቷ የሚቀዱ የብራና መጻሕፍትም አሉበት፡፡

የመስከረሟ አደይና ሆያ ሆዬ

የአዲስ ዘመን ብስራት በአንድ ጎኑ መሬት ከፀሓይ ጋር ካላት ግንኙነት የሚከሰት ነው፡፡ አንድ ዓመት፣ ሁለት ዓመት እየተባለ የሚጠራው መሬት በፀሓይ ዙሪያ ጉዞዋን ለማድረግ የሚፈጅባትን የ365 ከሩብ ቀናት የሚፈጅባት ጊዜ ነው፡፡ በነዚህ የዐውደ ዓመት ቀናት አራቱ ወቅቶች ክረምትና በጋ፣ መፀውና ፀደይ ይፈራረቃሉ፡፡

‹‹የሀብቴ የእግር አሻራ. . .››

የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት (ኢቱንድ) መሰንበታቸውን የቱሪዝሙን አባት ገብተ ሥላሴ ታፈሰን ዘከረ፤ አሰበ፡፡ ሠዓሊና ገጣሚው የኢቱንድ ዋና ዳይሬክተር አሰፋ ጉያም ስንኞችን አሠረ፡፡

ቁሳዊና መንፈሳዊ ባህሎችን ተደራሽ ያደረጉት ኅትመቶች

‹‹ቅርሶች በታሪክ ምስክርነታቸው ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፉ ሳይንሳዊ ምዝገባና ቁጥጥር ማከናወን፣ ከቅርሶች የሚገኙ ጥቅሞች ለኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማቶች ዕገዛ እንዲያደርጉ ማስቻል፣ ቅርሶችን ማግኘትና ማጥናት›› የሚሉ ዓበይት ዓላማዎችን የያዘው የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን (ቅጥጥባ) ነው፡፡