Skip to main content
x

አገር የሚያስፈልጋት ከውድመትና ከጥቃት የፀዳ ትግል ነው

ላለፉት 26 ዓመታት ግንቦት 20 በመጣ ቁጥር አብዛኛውን ጊዜ በሐሳብና በምናብ፣ አንዳንዴም እዚህ ጋዜጣ ላይ በሚወጣ ጽሑፍ ኢሕአዴግን ‹‹በላ ልበልሃ!›› እያልኩ የምሞግትበት አንድ ጉዳይ አለ፡፡ ግንቦት 20 ለኢሕአዴግ ከሞላ ጎደል አልፋና ኦሜጋው ነው፡፡ አዲሲቷ ኢትዮጵያ የተመሠረተችበት፣ ታሪኳ መጻፍ የጀመረበት፣ ወዘተ ነው፡፡ ኢሕአዴግ ያለውን ቢልም አንድ ነገር ግን እውነት ነው፡፡ ግንቦት 20 የወታደራዊ አምባገነንነት እንዳይሆን የፈረሰበት፣ ፈላጭ ቆራጮች እምቧጮ የሆኑበት፣ ወታደራዊ ኃይላቸው፣ የፀጥታ መረባቸውና ፓርቲያቸው የተበጣጠሰበት ዕለት ነው፡፡

ለኅብረ ብሔራዊ ትግል ወደፊት በሉለት!

እነሆ የ2010 ዓ.ም. የካቲት አባተ፡፡ የ1966 ዓ.ም. የየካቲት አብዮትም 44 ዓመት ሞላው፡፡ ሃያኛው ክፍለ ዘመን ተጋምሶ 1966 ዓ.ም. በመጣበት ጊዜም ቢሆን፣ የመሳፍንቱንና የመኳንንቱን ኢኮኖሚያዊ የበላይነት እያሳሳና እያደከመ የተባዛና የተጠናከረ ሥልጣን የቀረው የካፒታሊስት መደብ በኢትዮጵያ አልተፈጠረም ነበር፡፡ መሳፍንቱንና መኳንንቱም ወደ ካፒታሊስትነት የተሸጋገሩበት ለውጥ አልነበረም፡፡ ስለዚህም ያኔም ዋናው ጉዳይና ትግል እንደ ከዚያ በፊቱ ጭሰኝነትና ገባርነትን የማስወገድ ለውጥ ነበር፡፡

ለንቀትም ለእብሪትም የማይመች ዴሞክራሲያዊ ትግል ያስፈልገናል

ስለሕዝቦች ልዕልናና ስለዴሞክራሲ ድል መምታት እነሆ አሁንም 27 ዓመት ላይ ሆነን እያወራን ቢሆንም፣ ዛሬም የፀረ ዴሞክራሲ የአፈና ዘይቤዎች እንደደላቸው ናቸው፡፡ አሁንም የሕዝብ ቅሬታዎች መተንፈሻ አጥተው መጠራቀማቸውና አጋጣሚ እየጠበቁ መፈንዳታቸው አልተቋረጠም፡፡ ስለጥበትና ስለትምክህት አደገኛነት ለዓመታት ስናወራ ብንኖርም፣ ዛሬም አገሪቷን የሚንጧትን ችግሮች መስፋፋታቸውን ማዳከምና አደጋቸውን ማምከን አልተሳካልንም፡፡

የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ሆይ!

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የታኅሳስ ወር 2010 ዓ.ም. ‹‹ጥልቅ›› የግምገማና የውሳኔ ዜና እና ሪፖርት ዛሬም ጥር ወር አጋማሽ ላይ እያለንም በእንጥብጣቢ ከሚነገረን በላይ፣ የፓርቲውንም ሆነ የመንግሥትን ሙሉ እምነትና ሁሉንም እውነት ዝርግፍ አድርጎ የሚያሳይ አይደለም፡፡ የዓለም የመገናኛ ብዙኃንና ስም ያላቸው መንግሥታትና የመንግሥታት ማኅበራትና ቡድኖች በተለይ ትኩረት ሰጥተው ዜና ያደረጉትና ያበረታቱት፣ ‹‹የታሰሩ ፖለቲከኞች›› ወይም ‹‹የፖለቲካ እስረኞች›› ጉዳይም ገና እንዳወዛገበ ነው፡፡

የአገራዊ ራዕይ አልባነት ጉዞ እስከ መቼ?

ዓለም ከሥልጣን ፖለቲካ ወደ ፖለቲካ ተሻግሮ፣ ስለታሪክ ከመነታረክ ወጥቶ ታሪክ ስለመሥራት በሚታገልበት፣ ከጥቃቅንና አነስተኛ ሐሳቦች ወጥቶ እጅግ ወደ ላቀና ውስብስብ ሐሳብ በገባበት፣ ከጓዳ ፖለቲካ ወደ አደባባይ ፖለቲካ፣ ከድንበር ተሻግሮ በዓለም አቀፋዊነት በሚተጋበት እኛ ከከባቢያዊነት ወደ መንደርተኝነት ስንገሰግስ፣ ዓለም ወደ ፊት ቀን ከለሊት ሲተጋ፣ እኛ ወደ ኃላ እያሰብን ሴራ ስንጎነጉን፣ ዓለም በነገ ማዕቀፍ ሲተጋ እኛ በትናንት ማዕቀፍ ለመኖር ስንተጋ፣ ፖለቲካችን እንደ ሕፃን ልጅ በትናንሽ ነገሮች እየረካ፣ ዓለም ከመሬት ፍትጊያ ወደ ስፔስ (ህዋ) ፍትጊያ ሲገባ፣ የእኛ ግን ነገር መብላት ብቻ ቢሆን ለምን ብሎ መጠየቅ ዜጋዊ ግዴታ ሆነና ጥያቄ አነሳሁ፡፡

የኢሕአዴግ የችግሮች ሁሉ ችግር እኔ ብቻ ባይነት

ኢሕአዴግ ከታኅሳስ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ታኅሳስ 20 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ ያካሄደውን ‹‹የሁኔታዎች ግምገማ›› ካጠናቀቀ በኋላ፣ በተለይም የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ሊቃነ መናብርት ታኅሳስ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት አምስት ሰዓት የፈጀ ‹‹መግለጫ›› ግንባሩ የውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲ ችግር እንዳለበት ነግሮናል፡፡ ኢሕአዴግ ችግር አለብኝ ሲል ይህ የመጀመርያው ጊዜ አይደለም፡፡

ኢሕአዴግ ምን አለ?

ኢሕአዴግ 2008 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ የጀመረው ሁለተኛውና ‹‹እንደ ገና በጥልቀት የመታደስ›› ንቅናቄው ዛሬም ከአንድ ዓመት ከሩብ ያህል በቀጠለ ተከታታይ፣ እያገረሸና አላባራ እያለ ካስቸገረ ሁከት፣ ቀውስና አለመረጋጋት ጋር እንዳጋጠመን ይገኛል፡፡ ‹‹ባለፉት ሁለት ዓመታት ድርጅታችን ኢሕአዴግ ያደረገው የጥልቅ ተሃድሶ እንቅስቃሴ በርካታ አበረታች ውጤቶች የተገኙበት ቢሆንም፣ በሚፈለገው ደረጃ ጥልቀት ያልነበረው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተመልሰን ወደ አዘቅቱ መመለስ መጀመራችንን [ድርጅቱ] በትክክል አስቀምጧል›› ያለው ኢሕአዴግ ራሱ ከታኅሳስ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ባካሄደው የ17 ቀናት ግምገማ መካከል ታኅሳስ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ነበር፡፡

የዴሞክራሲ ትግሉ ችግሮች ሥረ መሠረት አላቸው

የካቲት 2010 ዓ.ም. ሲመጣ የ1966 አብዮት 44 ዓመት ይሞላዋል፡፡ ከ1966 አብዮት እስከ ዛሬ ድረስ ያለው ጊዜ ከዴሞክራሲ እንቅስቃሴ አኳያ የብዙ ነገር ድፍርስርስ በተለያየ ሙቀትና ንቅናቄ ሲናጥና ሲንቦጫረቅ የታየበት፣ የሚተነው ተኖ የሚዘቅጠው ዘቅጦ ሊጠራ ነው ሲባል ተመልሶ እንብክብኩ መውጣትና ሲከፋም ተከልብሶ የንፋስና የትቢያ እራት መሆን፣ እንደገና ጥንስስና ቅራሪ ቢጤ እዚያም እዚያም መቋጠር የቀጠለበት ረዥም የመንገጫገጭ ጊዜ ነው፡፡

ኧረ ለመሆኑ ኪራይ ሰብሳቢነት ምንድን  ነው? ኪራይ ሰብሳቢውስ ማነው?

የአገር ልጆች ሲተርቱ ‹‹ሰው ኑሮውን ይመስላል›› ይላሉ፡፡ የምሳሌው ትርጓሜ ድህነትም ሆነ ጌትነት ዝርዝሩን ቁመና ላይ ይጽፋል ማለት ነው፡፡ የገበሬና የወዛደሩ የኑሮ ቆፈንና አሳር የፊት ቆዳው ላይ፣ ግንባርና መዳፉ ላይ ይቆጠራል፡፡ የጌታ ድሎትም እንዲሁ ነው፡፡ ‹‹አፍ ሲያብል ገላ በላሁ ይላል››፡፡ ምቾት ዓይንና ገላ ላይ ይታተማል፡፡ የትኛውም የኑሮ ዘይቤ ህሊናም ላይ እንዲሁ እያንዳንዱን ነገሩን ያትማል፡፡ የተገላቢጦሽ ግን አይደለም፣ ሐሳብና ምኞታችን ስለሰበክነው ወደ ኑሮነት አይሸጋገርም፡፡ ‹‹አትስረቅ፣ ክፉ አትሥራ፣ . . . ወዘተ›› ሲሰበክ ስንት ዘመኑ! ስብከቱን በየቀኑም ሆነ በየሳምንቱ እንጠጣዋለን፡፡ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ትንሽ ኃፍረትና ፀፀት ብጤ እንድንቀማምስ ወይም በአፍአዊ ጨዋነት ገመናን ለመሰወር ከመጥቀሙ ባሻገር እጅግም ኑሯችንን አላረመም፡፡ ክፉ ሥራውም፣ ሌብነቱም በተለያየ ደረጃና ሥልት እንደ ጉድ ይካሄዳል፡፡ በተሰባኪው ዘንድ ብቻ ሳይሆን በሰባኪዎቹ ውስጥም፡፡

ሁኔታዎች እንዳደረጉ አድርገው ይቅዘፉን ወይስ ልንቀዝፋቸው እንፈቅዳለን?

በጨዋታ ላይ “አዙረኝም አታዙረኝ” ማለት ይቻላል፡፡ በእውነተኛ ኑሮ ውስጥ ግን መደናበርን ኑሮ ካላደረጉት በቀር አንዱን መምረጥ ያሻል፡፡ ኢሕአዴግ ሙስናን/ኪራይ ሰብሳቢነትን እታገላለሁ የሚለው ራሱ የእነዚህ ሁሉ ወኪል ሆኖ፣ ለእነዚህ ችግሮች መቀጠልና ማደግ የሚስማማ ሁኔታ ታቅፎ ነው፡፡