Skip to main content
x

‹‹ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ተመሳሳይ ሪፖርት እያቀረብኩ ስለሆነ እንድትሰሙኝ እፈልጋለሁ›› ዋና ኦዲተር ገመቹ ዱቢሶ

ከተሾሙ አንስቶ ለዘጠነኛ ዓመታት ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርታቸውን ለፓርላማ ያቀረቡት ዋና ኦዲተር ገመቹ ዱቢሶ፣ ለዘጠነኛ ዓመት ተመሳሳይ ሪፖርት እያቀረቡ መሆኑን በመጥቀስ የፓርላማ አባላት እንዲሰሟቸውና ግፊት እንዲያደርጉ ጠየቁ፡፡

ለኔዘርላንድ ኩባንያ የተሰጠውን የጤፍ የባለቤትነት መብት ለማሰረዝ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሠርት ተወሰነ

የኢትዮጵያን የባለቤትነት መብት በመጣስ ለኔዘርላንድ ኩባንያ የተሰጠውን የጤፍ አዘገጃጀት ፓተንት (መብት) ለማሰረዝ ሲደረግ የቆየው ድርድርና ውይይት ባለመሳካቱ፣ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መደበኛ ክስ እንዲመሠረት መወሰኑን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከኃላፊነት የሚነሱ ባለሥልጣናትን በአምባሳደርነት መሾም በፓርላማ ጥያቄ አስነሳ

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሥልጣን ጊዜያቸውን ጨርሰውም ሆነ ሳይጨርሱ ከኃላፊነት የሚነሱ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ ባለሥልጣናት በአምባሳደርነት የሚሾሙበትን አሠራርና የፍትሐዊነት ችግር በተመለከተ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ ተነሳ፡፡ ጥያቄው የተነሳው ሐሙስ ግንቦት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) የመሥሪያ ቤታቸውን የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ሲያቀርቡ ነው፡፡

ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ጋር የተጀመረው ድርድር አንድምታ

መንግሥት መቀመጫውን በአሜሪካ ካደረገው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ጋር የፖለቲካ ድርድር መጀመሩ፣ ድርድሩም ኦዴግ አገር ውስጥ ገብቶ እንዲሳተፍ በሚችልበት መርሆዎች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ኦዴግ የተጀመረውን ድርድር አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ካወጣ በኋላ፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤትም ሰኞ ግንቦት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ድርድሩ መጀመሩን በይፋ አረጋግጧል፡፡

የማዳበሪያ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች በአስቸኳይ ወደ ሥራ እንዲገቡ ማሳሰቢያ ተሰጠ

የማዳበሪያ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ያሉባቸው ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተቀርፈው በአስቸኳይ ወደ ሥራ መግባት እንዳለባቸው፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡ ቋሚ ኮሚቴው በግብርና ግብዓት አቅርቦትና ተግዳሮቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚሰጠውን የታሪክ ትምህርት ሊከልስ ነው

በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚሰጠው የታሪክ ትምህርትና ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ታሪክ አዲስ የመጻሕፍት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን፣ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የትምህርት ሚኒስትሩ ጥላዬ ጌቴ (ዶ/ር) ማክሰኞ ሚያዝያ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ሲያቀርቡ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ባደረገው ፍተሻ መሠረት  የመጻሕፍት ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በፓርቲ ተፅዕኖ ሥር የወደቀውን የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ግንኙነት ተቋማዊ ለማድረግ የተዘጋጀ የፖሊሲ ማዕቀፍ ለፓርላማ ተላከ

በአሁኑ ወቅት በአንድ ፓርቲ ተፅዕኖ ሥር እንደወደቀ በይፋ የታመነበትን የፌዴራልና የክልል የመንግሥታት ግንኙነት ከፓርቲና ከግለሰቦች ተፅዕኖ በማላቀቅ፣ ተቋማዊ መሠረትና ሕጋዊ ሥርዓት እንዲኖረው ለማድረግ የተረቀቀ የፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲፀድቅ ለፓርላማ ተላከ፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግሥታት ግንኙነት የፖሊሲ ማዕቀፍ›› የሚል መጠሪያ የተሰጠውን ይህንን የፖሊሲ ማዕቀፍ ያረቀቁት፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የፌዴራል አርብቶ አደርና ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር ናቸው፡፡

ዴሞክራቲክ ተቋማት በነፃነትና በገለልተኝነት እንዲደራጁ ግፊት ይደረግ!

ኢትዮጵያ ውስጥ ላጋጠሙ ሥር የሰደዱ ችግሮች እንደ መነሻ ተደርጎ የሚወሰደው፣ የዴሞክራቲክ ተቋማት በነፃነትና በገለልተኝነት አለመደራጀትና ሥራቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አለመደረጉ ነው፡፡ ዴሞክራቲክ ተቋማት የሚባሉት ምርጫ ቦርድ፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ ዕንባ ጠባቂ ተቋምና ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ተጠሪነታቸው ለፓርላማው እንደሆነ ተደንግጓል፡፡

ሚድሮክ ወርቅና ሶዳ አሽ ፋብሪካ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በተያያዘ በፓርላማ ጥያቄ ተነሳባቸው

በለገደንቢ የሚገኘውን ሚድሮክ ወርቅ ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ፋብሪካዎች፣ በአካባቢና በኅብረተሰቡ ላይ በሚያደርሱት ብክለትና ጉዳት መንግሥት ዕርምጃ ባለመውሰዱ በፓርላማ ጥያቄ ተነሳበት፡፡

የግብርናና እንስሳት ሀብት ሚኒስቴሮች በመዋሀዳቸው የቀድሞ ሚኒስትሮች ዕጣ ፈንታ አለየም

የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴርና የእንስሳት ሀብት ልማት ሚኒስቴር በድጋሚ ተዋህደው  አንድ ሚኒስቴር በመሆናቸው፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የሁለቱ የቀድሞ ሚኒስትሮች ዕጣ ፋንታ እስካሁን አለየም፡፡