Skip to main content
x

ባንኮች በሁለት ሳምንት ውስጥ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ መንዝረዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ የውጭ ገንዘብ በእጃቸው የሚገኝ ዜጎች ወደ ባንክ እንዲያስገቡ ማሳሰባቸው ይታወሳል፡፡ ይህንኑ ተከትሎም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የግል ባንኮች ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ በሁለት ሳምንት ውስጥ እንደመነዘሩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

የዶላር ምንዛሪ በባንክና በጥቁር ገበያው መሳለመሳ እየሆነ ነው

በባንኮችና በጥቁር ገበያው መካከል የአንድ ዶላር የምንዛሪ ዋጋ ልዩነት እየወረደ በመምጣት በአሁኑ ወቅት በሳንቲሞች ደረጃ ተወስኗል፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት በጥቁር ገበያውና በመደበኛ ባንኮች በኩል የአንድ ዶላር ምንዛሪ ልዩነት ከሰባት እስከ አሥር ብር ልዩነት እንደነበረው ይታወሳል፡፡  

አቶ ግርማ ብሩ የብሔራዊ ባንክ ቦርድ ሰብሳቢ ሆኑ

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አቶ ግርማ ብሩ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ብንክ ቦርድ ሊቀመንበር እንዲሆኑ ተሰየሙ፡፡ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥን ጨምሮ ሦስት የመንግሥት ኃላፊዎች፣ በቦርድ አባልነት እንዲያገለግሉ ተመድበዋል፡፡

የግል ባንኮች ትርፍ ከ10.5 ቢሊዮን ብር በላይ ደረሰ

የአገሪቱ የግል ባንኮች በ2010 ሒሳብ ዓመት ከታክስና ከሌሎች ተቀናሾች በፊት ከ10.5 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፋቸው ታወቀ፡፡ የ16 የግል ባንኮች የ2010 ሒሳብ ዓመት ግርድፍ የሒሳብ ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ ከታክስና ከሌሎች ተቀናሾች በፊት ያገኙት የትርፍ መጠን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከ2.7 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ አለው፡፡

ብሔራዊ ባንክ ከንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ጋር በፋይናንስ ችግሮች ላይ ሊወያይ ነው

የንግድ ማኅበረሰቡ በፋይናንስ ተቋማት የብድር አሰጣጥና ሌሎች ችግሮች ላይ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች በማቅረባቸው፣ ከብሔራዊ ባንክ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ምክክር ሊያደርጉ ነው፡፡

ሚያዚያ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በሰጡት መመርያ፣ በፋይናንስ ተቋማት ላይ በቀረቡት አቤቱታዎች ላይ የብሔራዊ ባንክና የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ምላሽ እንዲሰጡበት አሳስበው ነበር፡፡

ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማሳሰቢያ ተፈጻሚ እንዲሆን የተሰጠው የጊዜ ገደብ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ቢሆንም፣ እስካሁን ሳይካሄድ ቆይቷል፡፡

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ የግል ባንኮች ባሉባቸው ችግሮችና መፍትሔዎች ዙሪያ እያነጋገሩ ነው

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) የግል ባንኮች ፕሬዚዳንቶችንና ሥራ አስፈጻሚዎችን በተናጠል ማነጋገር ጀመሩ፡፡ የባንኩ ገዥ የሁሉንም ባንኮች ኃላፊዎች በማነጋገር ላይ የሚገኙት ለሁሉም ባንኮች ባስተላለፉት ጥሪ መሠረት ሲሆን፣ የየባንኮቹ ኃላፊዎችም በተያዘላቸው ፕሮግራም መሠረት ከገዥው ጋር ለሰዓታት ውይይት ማድረግ ጀምረዋል፡፡