Skip to main content
x

በሦስት ወራት ሊሰበሰብ ከታቀደው የታክስ ገቢ ውስጥ 10 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ አልተቻለም

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በ2011 ዓ.ም. የመጀመርያ ሩብ ዓመት ለመሰብሰብ ካቀደው ገቢ ውስጥ ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ እንዳልቻለ ተመለከተ፡፡ በዚህ ወር ከ23 ቢሊዮን ብር በላይ ይሰበሰባል ተብሏል፡፡  

በእንስሳት ሀብት ላይ ያተኮረው ዓውደ ርዕይ ለመኖ ዕጦት መፍትሔ አመላካች ጉባዔ አሰናድቷል

የአፍሪካ የእንስሳት ሀብት ዓውደ ርዕይና ጉባዔ፣ ለአራተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ከጥቅምት 8 እስከ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. እንዲካሄድ መሰናዶው ከተጀመረ ሰነባብቷል፡፡ በዚህ ዓውደ ርዕይ ትልቁን ትኩረት ካገኙት ጉዳዮች መካከል የእንስሳት መኖ እጥረት ዋናው እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸዋል፡፡

ያሽቆለቆለው የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት ኢትዮጵያን ከደረጃ ውጪ አድርጓታል

ላለፉት ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚ የውጭ ኢንቨስትመንት መዳረሻ ሆና ስለመቆየቷ በርካታ ተቋማት ሲያስተጋቡት የቆየ አንኳር ጉዳይ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚህ ዓመት ግን የኢትዮጵያ ደረጃ እንደሚጠበቀው እንደማይሆን አመላካች መረጃዎች ወጥተዋል፡፡

በ33 ሚሊዮን ዶላር የብረት ፋብሪካ ተገንብቶ ተመረቀ

በደቡብ ኮሪያ ባለሀብቶች የተቋቋመው ኢኮስ የብረታ ብረት ማምረቻ ኃላፊነቱ የግል ማኅበር፣ በ33 ሚሊዮን ዶላር ያስገነባው ፋብሪካ በይፋ ተመርቆ ተከፈተ፡፡ ኩባንያው በዱከም ከተማ ያስገነባውን ፋብሪካ ማክሰኞ ጥቅምት 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ሲያስመርቅ፣ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ጨምሮ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል የተለያዩ የመንግሥት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ማብራሪያ የሚያስፈልገው የፕሬዚዳንቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ አቅጣጫ

ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) በሳምንቱ መጀመርያ ላይ ለሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ላይ የ2011 ዓ.ም. የመንግሥት የትኩረት አቅጣጫ የሚጠቁም ንግግር አድርገዋል፡፡ በዚህ ንግግራቸው ውስጥ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ሊያስቀጥሉ የሚችሉ የተለያዩ ነጥቦችን አንስተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ሪል ስቴት ለማልማት ሦስት ተቋማት ጥምረት ፈጠሩ

በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በገንዘብ ፋይናንስ የሚያደርገው የአሜሪካው የኢንቨስትመንት ኩባንያ ኤስጂአይ ፍሮንቲር ካፒታልና በሪል ስቴት ልማት የተሰማራው ሮክስቶን ሪል ስቴት ከቢጋር የግንባታና ሪል ስቴት አልሚ ኩባንያ ጋር በመሆን በአዲስ አበባ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን ለማልማት ጥምረት ፈጠሩ፡፡

ኢትዮጵያ ከቻይና ከምታገኘው ጥቅል ብድር ውስጥ የዕርዳታ ምጣኔው ከፍ ተደረገ

በከፍተኛ የዕዳ ጫና ውስጥ ለምትገኘው ኢትዮጵያ ከቻይና መንግሥት ከሚገኝ ጥቅል ኮንሴሽናል ብድር ውስጥ የዕርዳታ ምጣኔው ከፍ ተደረገላት፡፡ ቻይና ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ አገሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ አዲስ የኮንሴሽናል ብድር ሥሌት ተግባራዊ ማድረጓ ታውቋል፡፡

የመስከረም ወር የዋጋ ግሽበት በ12 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ይፋ አደረገ

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ይፋ ያደረገው የዋጋ ግሽበት መረጃ እንዳመለከተው፣ በተያዘው ወር የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት በ2010 ዓ.ም. መስከረም ወር ላይ ከተመዘገበው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት አኳያ የ12 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ሲታይ፣ የምግብ ዋጋ ግሽበቱም ካለፈው ዓመት መስከረም ወር ይልቅ በዚህ ዓመት የ13.5 በመቶ ዋጋ ጭማሪ ተመዝግቧል፡፡

የደን ማስተር ፕላን ከ22 ሚሊዮን ሔክታር በላይ የተራቆተ መሬት ለማገገም የሚቻልበትን ተስፋ ሰንቋል

ከሦስት ዓመታት በፊት ይፋ በተደረገ ጥናት መሠረት፣ በኢትዮጵያ እያደገ ከመጣው የማገዶ ፍጆታ በመነሳት በመጪዎቹ አሥር ዓመታት ውስጥ 300 ሚሊዮን ዛፎች መተከል እንዳለባቸው ተጠቅሶ ነበር፡፡