Skip to main content
x

ኔክሰስ ሆቴል በ410 ሚሊዮን ብር ያካሄውን የማስፋፊያ ግንባታ  አጠናቀቀ

ኔክሰስ ሆቴል በ410 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ 85 የመኝታ ክፍሎች ያሉት ሕንፃ ግንባታ አጠናቆ ለአገልግሎት ማብቃቱን አስታወቀ፡፡ ሆቴሉ በሁለት ምዕራፍ ያካሄደው ኢንቨስትመንት ከ560 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሆነና የመኝታ ክፍሎቹንም ወደ 115 እንዳደረሰ አስታውቋል፡፡

በፋይናንስ አቅርቦት ችግር የ15 ባለ ኮከብ ሆቴሎች ግንባታ እየተጓተተ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ 15 ባለ ኮከብ ሆቴል ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተካሄደ ቢሆንም፣ ብድርም ሆነ የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ባለመቻላቸው ለከፍተኛ ችግር እየተዳረጉ መሆኑ ታወቀ፡፡ ከኢትዮጵያ ሚሊኒየም ወዲህ በርካታ ሆቴሎች በአዲስ አበባ የተገነቡ ሲሆን፣ አሁንም በርካታ የሆቴል ፕሮጀክቶች በማያቋርጥ የግንባታ ሒደት ላይ ይገኛሉ፡፡

በሐዋሳ ከ3.5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገነባው የሀያት ሪጀንሲ ሆቴል ውዝግብ አስነሳ

በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ ከ3.5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት የሚገነባው የሀያት ሪጀንሲ ሆቴል ፕሮጀክት የመሬት ይገባኛል ውዝግብ ተነሳበት፡፡ ሆቴሉ ሊገነባበት በታሰበበት ቦታ ላይ የይገባኛል ጥያቄ ያነሳው የመከላከያ ሚኒስቴር መሆኑም ታውቋል፡፡ ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ ጥር የሆነን ሆቴል በሐዋሳ ለመገንባት  የይሁንታ ደብዳቤ በከተማ አስተዳደሩ ተሰጥቶኛል የሚሉት ባለሀብቱ አቶ ቴዎድሮስ ሽፈራው፣ ሆቴሉን ለማስገንባት ዲዛይን ለማሠራት ያደረጉት እንቅስቃሴ መደናቀፉን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ቅርሶችን በተሻለ ለማስጠበቅ የሚረዳ ሕግ እያረቀቀ እንደሚገኝ አስታወቀ

በአገሪቱ የሚገኙ ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ የተፈጥሮና ሌሎችም ቅርሶችን በተሻለ ክብካቤና በባለቤትነት ስሜት ለማስጠበቅ ያግዛል ያለውን የሕግ ረቂቅ ማዘጋጀት እንደጀመረ ያስታወቀው ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ በቅርስ መዳረሻዎች አካባቢ የሚኖሩ ማኅበረሰቦች ከሚገኘው ገቢ እስከ 30 በመቶ እንዲደርሳቸው ማቀዱን ይፋ አድርጓል፡፡

ሁለት የራዲሰን ብሉ ብራንዶች ገበያውን ሊቀላቀሉ ነው

በዓለም አቀፍ ደረጃ በሆቴል ማስተዳደር ሥራ በሚታወቀው ካልሰን ሬዚዶር ግሩፕ ሥር የሚገኙት ራዲሰን ብሉና ፓርክ ኢን ባይ ራዲሰን የተባሉ የሆቴል ብራንዶች በኢትዮጵያ የሚያስተዳድሩትን ሆቴል ወደ አራት ከፍ የሚያደርግላቸውን ሁለት አዳዲስ የኮንትራት ስምምነቶች ፈጸሙ፡፡

ማሪዮት በኢትዮጵያ ተጨማሪ ሆቴል ለመክፈት ስምምነት ማድረጉን አስታወቀ

ኢትዮጵያን ጨምሮ በአራት አገሮች ሰባት አዳዲስ ሆቴሎችን ለመክፈት ተስማምቷል በሩዋንዳ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ሆቴል ኢንቨስትመንት ፎርም ወቅት፣ ማሪዮት ኢንተርናሽናል 165 ክፍሎች የሚኖሩትና ፕሮቲያ ሆቴል የተሰኘውን ብራንድ ቸርችል ጎዳና አካባቢ እ.ኤ.አ. በ2021 እንደሚከፈት የሚጠበቀውን ሆቴል በአዲስ አበባ ዕውን ለማድረግ የሚያስችለውን ስምምነት ማከናወኑን አስታውቋል፡፡