Skip to main content
x

የኢጋድ ስብሰባ አሁንም ያለ ስምምነት ተበተነ

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) የደቡብ ሱዳን ልዩ መልዕክተኛ ቡድን ለኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት፣ ሁለቱ የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞች ሥልጣን መጋራትና ወታደራዊ ኃይል አወቃቀር ላይ መስማማት እንዳልቻሉ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግርና በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የሚኖረው ተፅዕኖ

ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ከሚሠሩ አገሮች አንዷ ነች፡፡ በሶማሊያ የመሸገውንና ራሱን ‹‹አልሸባብ›› ብሎ የሚጠራውን ቡድን ከመመከትና ከማዳከም ባሻገር፣ በሱዳንና በደቡብ ሱዳን መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ከላይ ታች ስትል ነበር፡፡

የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት ቁርጥ ያሉ ውሳኔዎች ያልተላለፉበት 30ኛው የመሪዎች ጉባዔ

30ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ጥር 20 እና 21 ቀን 2010 ዓ.ም. በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡ በአሁኑ የመሪዎች ጉባዔ የፀረ ሙስና ዘመቻ፣ የአፍሪካ ኅብረት ማሻሻያ፣ ነፃ የንግድ ቀጣና መመሥረት፣ የአፍሪካን የአየር ክልል ለአፍሪካ አየር መንገዶች ነፃ ማድረግና በአኅጉሪቱ በሚታዩ የፀጥታ ሥጋቶችና ሌሎች አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ ባለፈው እሑድና ሰኞ በተካሄደው 30ኛው የመሪዎች ጉባዔ የአርባ ዘጠኝ አገሮች መሪዎች ተገኝተው ነበር፡፡

የደቡብ ሱዳን አዲሱ የተኩስ አቁም ስምምነትና የተደቀነው ሥጋት

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ የፖለቲካ ኃይሎች ወደ እርስ በርስ ጦርነት ካመሩ አራት ዓመታት አለፉ፡፡ ይህ ግጭት ቆሞ በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ለማድረግ የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ በተለይ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) ሁለቱ ኃይሎች ያነገቡትን መሣሪያ በመጣል፣ ወደ ጠረጴዛ ውይይት እንዲመጡ ተደጋጋሚ ጥረት በማድረግ ተጠቃሽ ነው፡፡

የኢጋድ አባል አገሮች የደቡብ ሱዳን ተገዳዳሪ ኃይሎችን ለማስታረቅ እየጣሩ ነው

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርና ዋነኛ ተቃዋሚያቸው ሪክ ማቻር (ዶ/ር) መካከል ያለውንና ጉዳት እያስከተለ ያለውን ልዩነት ለመፍታት፣ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) አባል አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዓርብ ጥቅምት 3 ቀን 2010 ዓ.ም. በጁባ ውይይት አደረጉ፡፡