Skip to main content
x

የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የስንብት ጥያቄ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሐሙስ የካቲት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ከኢሕአዴግ ሊቀመንበርነትና ከመንግሥት ኃላፊነት በራሳቸው ፈቃድ ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸውን ማስታወቃቸው፣ የሰሞኑ አንዱ የአገሪቱ መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥልጣን የመሰናበት ጥያቄ አገሪቱ በገጠማት የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት በመሆኑ፣ በሕዝቡ ውስጥ የተደበላለቁ ስሜቶች ተንፀባርቀዋል፡፡ ላለፉት ስድስት ዓመታት ያህል በኢሕአዴግ ሊቀመንበርነትና በጠቅላይ ሚኒስትርነት የሠሩት አቶ ኃይለ ማርያም፣ ለሦስት ዓመታት ያህል መቆም ባልቻለው የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት በደረሰ ጉዳት በርካቶች በመሞታቸው፣ በመጎዳታቸውና ከቀዬአቸው በመፈናቀላቸው ሳቢያ ሥልጣን ለማስረከብ መገደዳቸው ታውቋል፡፡ 

የተምች ወረርሽኝ በዚህ ዓመት ከፍተኛ አደጋ መደቀኑ ተገለጸ

ምንጩ ከወደ ፓስፊክ አገሮች፣ ማዕከላዊ አሜሪካ ከመሆኑም በላይ የአሜሪካ የፀደይ ወራት ስያሜ በመያዝና በዩኤስ አሜሪካም ተንሰራፍቶ እንደሚገኝ የሚጠቀስለትና ‹‹ፎል አርሚዎርም›› በመባል የሚጠራው የተምች ወረርሽኝ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገሮችን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አዳርሶ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅትም  ካለፈው ዓመት የበለጠ ጥፋት በኢትዮጵያ ሊያስከትል እንደሚችል ተገምቷል፡፡ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (ዩኤስአይዲ) አማካይነት በሚመራው ፊድ ዘ ፊውቸር የኢትዮጵያ እሴት ሰንሰለት ፕሮግራም ቺፍ ኦፍ ስታፍ ኢያን ቼስተርማን ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቆይታ ወቅት እንዳስታወቁት፣ የተምች ወረርሽኙ የአገሪቱን ሰብሎች በመላመዱና የአየሩ ጠባይ ለመራባት ምቹ ስለሆነለት በዚህ ዓመት ሊያደርስ የሚችለው ጥፋት ካለፈው ዓመት ይልቅ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቡና በዓለም የጥራት መድረክ በአሸናፊነት መጓዙን የሚሞግቱ ምልከታዎች

የኢትዮጵያ ቡና በዓለም መድረክ በተለይም በየዓመቱ በአሜሪካ በሚካሄድ የቡና ቅምሻ ውድድር ላይ በበላይነት ለማጠናቀቅ የሁሉም ተወዳዳሪዎች ምርጫ ሆኖ ከሰነበተ በጥቂቱ አምስት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ልዩ ልዩ የምግብ ጣዕሞችና ጥራታቸው በሚፈተሽበት በአሜሪካው ‹‹ጉድ ፉድ አዋርድ›› ውድድር ላይ አብዛኞቹ ቡና ቆዪዎች፣ እንደ ወትሯቸው በኢትዮጵያ ቡና በመወዳደር ዘንድሮም ድል ተቀዳጅተዋል፡፡ ሪፖርተር ስለዚሁ ውድድር ዝግጅት ከጥቂት ወራት በፊት ባስነበበው ዘገባ መሠረት፣ ከ27 በላይ ኩባንያዎች ለውድድሩ በኢትዮጵያ ቡና እንደሚሳተፉ ዘግቦ ነበር፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት ይፋ በተደረገው ውጤት መሠረትም በኢትዮጵያ ቡና ተወዳድረው አሸናፊ የሆኑት ኩባንያዎች ሙሉ ለሙሉ በኢትዮጵያ ቡና የተወዳደሩት መሆናቸው ይፋ ተደርጓል፡፡

በሱዳንና ሳዑዲ ዓረቢያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ ኢትዮጵያ ለማዘዋወር መንግሥት እንቅስቃሴ ጀመረ

በፈጸሙት ወንጀል ተፈርዶባቸው በሱዳንና በሳዑዲ ዓረቢያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ ኢትዮጵያ ለማዘዋወር፣ መንግሥት እንቅስቃሴ መጀመሩን የሪፖርተር ምንጮች አመለከቱ፡፡ ለጉዳዩ በጣም ቅርብ የሆኑ የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት ፍርደኛ ኢትዮጵያውያኑን ከሱዳንና ከሳዑዲ ዓረቢያ እስር ቤቶች ወደ ኢትዮጵያ እስር ቤቶች ለማዘዋወር በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው፣ ሕጋዊ ሥልጣን ያለው የአገሪቱ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተቋም ነው፡፡

መሰቦ ሲሚንቶ የ70 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራረመ

በኤፈርት ሥር ከሚተዳደሩት በርካታ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው መሰቦ ሲሚንቶ የግንባታ ዕቃዎች የሚያመርት ኩባንያ በ70 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ለማቋቋም፣ ኩስቶ ግሩፕ ከተሰኘ የሲንጋፖር ኩባንያና ፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ከተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የመኢአድና የሰማያዊ አመራሮች የሰሜን አሜሪካ ቆይታቸው ውጤታማ እንደነበር አስታወቁ

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) ባደረገላቸው ጥሪ መሠረት በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ያደረጉት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውጤታማ እንደነበር፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሊቀመንበር በዛብህ ደምሴ (ዶ/ር) እና የሰማያዊ ፓርቲ (ሰማያዊ) ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ አስታወቁ፡፡

የአሜሪካ ኤምባሲ በኢትዮጵያ የሚታየው ግጭት አሳስቦኛል አለ

የአሜሪካ ኤምባሲ በጨለንቆና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተነሱ ግጭቶች የሰዎች ሕይወት በመጥፋቱና የአካል ጉዳት በመድረሱ እጅግ እንዳሳሰበውና እንዳዘነ ገለጸ፡፡ ኤምባሲው በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ለተጎጂ ቤተሰቦችና ወዳጆች መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

በአገር ውስጥ ለሚከናወኑ ግዥዎች ከውጭ መክፈል የሚቻልበት ሥርዓት ተዘረጋ

በውጭ የሚኖሩ አፍሪካውያን በተለይም ኢትዮጵያውያን ባሉበት ሆነው ለተለያዩ አገልግሎት ክፍያዎችን መፈጸም የሚችሉበት ‹‹መላ›› የተሰኘ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ሥራ ጀመረ፡፡ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች የስልክ፣ የውኃ፣ የኤሌክትሪክ፣ የዕድር፣ የትምህርት ቤት፣ የሆስፒታል፣ የኢንሹራንስና ሌሎች የቤተሰቦቻቸውን የቤት ውስጥ ወጪዎችን ጭምር መክፈል የሚችሉበት ሥርዓት ሲሆን፣ ሥርዓቱን የዘረጉት ክፍያ ፋይናንሺያል ሰርቪስና ማስተር ካርድ በጥምረት ሆነው ነው፡፡

ከ660 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮችን ለመርዳትና ግጭቱ ዕልባት እንዲያገኝ አሜሪካ እገዛ አደርጋለሁ አለች

በመስከረም ወር በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች በተቀሰቀሰ ግጭት ለተፈናቀሉ ከ660 ሺሕ በላይ ዜጎች፣ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረግና ግጭቱ ዕልባት እንዲያገኝ እገዛ ለማድረግ ፍላጎቱ መሆኑን የአሜሪካ መንግሥት አስታወቀ፡፡

ከጂቡቲ ኢትዮጵያ ሊዘረጋ የታሰበው የነዳጅ መስመር ፕሮጀክት ታጠፈ

ኢትዮጵያ በከፍተኛ ወጪ ከጂቡቲ ወደብ ወደ መሀል አገር የምታስገባው የተጣራ የነዳጅ ውጤቶች ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ፕሮጀክት እንደታጠፈ ታወቀ፡፡ ተቀማጭነቱ በደቡብ አፍሪካ የሆነው ብላክ ራይኖ የተባለ ኩባንያ ከጂቡቲ ወደብ አዋሽ አርባ የሚገኘው የነዳጅ ዴፖ የሚደርስ 550 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ለመዘርጋት የሚያስችል ዕቅድ፣ ለኢትዮጵያ መንግሥት ማቅረቡ ይታወሳል፡፡