Skip to main content
x

የተጠሪነት ወሰን ያልተበጀለት የኢትዮጵያ ስፖርት

ሕጋዊ ሰውነት ኖሯቸው በመንቀሳቀስ ላይ ከሚገኙ መንግሥታዊ ተቋማት መካከል ስፖርቱ ይጠቀሳል፡፡ ዘርፉ በተለያየ አደረጃጀት መልክ ተጉዞ አሁን የደረሰበት ደረጃ ላይ ቢገኝም፣ ቅርፅ ያለው የተጠሪነት ወሰን ሳይበጅለት አንዴ ከባህል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከወጣትና ከሌሎችም ለስፖርቱ ቅርበት አላቸው ተብሎ ከሚታመንባቸው ተቋማት ጋር ሲጋባና ሲፋታ ዕድሜውን መግፋቱ፣ ዘርፉ ራሱን የቻለ ተቋማዊ ቅርፅ ብቻ ሳይሆን፣ ለተጠያቂነትና ግልጽነት እንዲሁም ለውጤታማነት በሩን ዘግቶ እንዲቆይ ምክንያት መሆኑን የሚያምኑ አሉ፡፡

የተስፋ ጭላንጭል የነበራቸው ዋሊያዎቹ ከአፍሪካ ዋንጫ ውጪ ሆኑ

በመጪው ጥር በካሜሩን አስተናጋጅነት የሚካሄደው የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ የወራት ሳይሆን የቀናት ዕድሜ ቀርቶታል፡፡ ከጋና ከኬንያና ከሴራሊዮን ምድብ ውስጥ የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) የነበረው የተስፋ ጭላንጭል ሲያበቃለት፣ ኬንያና ጋና ከምድቡ አንደኛና ሁለተኛ ለመሆን አንድ ጨዋታ እየቀራቸው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

የመጀመሪያው የግንባታ ምዕራፍ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው ብሔራዊ ስታዲየም

በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት (1923-1967) ተገንብቶ እስካሁን ከእግር ኳሳዊ እንቅስቃሴዎች እስከ ኮንሰርት ዝግጅቶች እያስተናገደ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ መዲና ተብላ ዓመታት ላስቆጠረችው አዲስ አበባ በብዙዎች ዘንድ ‹‹አንድ ለእናቱ›› በሚል መጠሪያ የሚታወቀውን የአዲስ አበባ ስታዲየምን በውስጧ ይዛ እስከ ቅርብ ዘልቃለች፡፡

ብሔራዊ የዳኞች ኮሚቴ ፌዴራል ዳኛ ጌቱ ተፈራን ለአንድ ዓመት ተኩል አገደ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሔራዊ የዳኞች ኮሚቴ ፌዴራል ዳኛ ጌቱ ተፈራን አገደ፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ፋሲል ከተማንና ሐዋሳ ከተማን በጎንደር ስታዲየም ጨዋታውን በዋና ዳኝነት የመሩት ፌዴራል ዳኛ ጌቱ ስህተት መፈጸማቸውን ያመኑ ስለመሆኑ ጭምር ብሔራዊ የዳኞች ኮሚቴ በመግለጫው አብራርቷል፡፡

የጅማ አባ ጅፋርና የመከላከያ ክለቦች አኅጉራዊ ተሳትፎ

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የሚያከናውነውን ዓመታዊ የክለቦች ማጣሪያ ጨዋታን ጀምሯል፡፡ በመድረኩ ኢትዮጵያን የሚሳተፉት የጅማ አባ ጅፋርና የመከላከያ ክለቦች ሲሆኑ፣ ጅማ አባ ጅፋር ወደ ናይጀሪያ መከላከያ ደግሞ ወደ ምሥራቅ አፍሪካዊቷ ጅቡቲ አምርተዋል፡፡

የዋሊያዎቹ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ቴክኒክ ሪፖርትና የፌዴሬሽኑ ዝምታ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) በመጪው ጥር ካሜሩን ለምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታውን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ይሁንና ቡድኑ እስካሁን ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች ሜዳ ላይ የነበሩበትን ጠንካራና ደካማ ጎን የሚያመላክቱ ሪፖርቶች በፌዴሬሽኑም ሆነ ይመለከታቸዋል በሚባሉ አካላት አለመቅረቡ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡ ብሔራዊ ቴኪኒክ ኮሚቴው በበኩሉ የእያንዳንዱን የጨዋታ ሪፖርት ለፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት እንዳስረከበ ያስረዳል፡፡

ክለቦችን ለፋይናንስ ቀውስ እግር ኳሱን ለውድቀት የዳረገው የሊጎች የጨዋታ ቅርፅ

የስፖርት ታላቅነት ከሚወሳባቸው መካከል በሕዝቦች መካከል ወዳጅነትና ወንድማማችነትን ማስፈን መሆኑ በዘርፉ የቀረቡ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ ለዘመናትም የስፖርት መርሆዎች ከሆኑት ውስጥ ይህ ተልዕኮው ጠበኛ አገሮችን፣ ፖለቲከኞችንና ተቀናቃኝ ወገኖችን ወደ ሰላም መንገድ ወደ አብሮነት ጥርጊያ የመምራት ኃይል የተላበሰ፣ የሰው ልጆች የአብሮነት መገለጫ ስፖርት መሆኑ እንደ ማያጠያይቅም ብዙዎች የሚስማሙበት እሴት ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡

‹‹መዘናጋት›› የዋሊያዎቹ ብቃትና ነገን የማያመላክተው ሰበብ 

ካሜሩን በመጪው ጥር ለምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያውን እያከናወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) በሜዳቸው ባደረጉት አራተኛ የምድብ ጨዋታ በጋና 2 ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል፡፡ በርካቶችን ባስቆጣው የዋሊያዎቹ ውጤት፣ ዘንድሮም ለሽንፈቱ ‹‹መዘናጋት›› እና መሰል ምክንያቶች ቀርበዋል፡፡