Skip to main content
x

ምርት ገበያ በደረሰኝ ዋስትና የባንክ ብድር ማግኘት የሚቻልበትን አሠራር ሊተገብር ነው

የመጋዘን ደረሰኞች የባንክ ብድር ዋስትና ይዘት ኖሯቸው እንዲያገለግሉ ለማድረግ ብሎም በሁለተኛ ገበያ በኩል የቦንድና የአክሲዮን ግብይቶችን ለማስጀመር ተቋማዊ አቅሙን እየገነባ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ገለጸ፡፡ በነሐሴ ወር ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶችን ማገበያየቱም ታውቋል፡፡

በነሐሴ ወር ከ94 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ የቡና የቅመማ ቅመምና የሻይ ምርት ወደ ውጭ መላኩን ባለሥልጣኑ አስታወቀ

ከአገሪቱ የወጪ ንግድ ምርቶች ውስጥ ቡና፣ ቅመማ ቅመምና ሻይ ይጠቀሳሉ፡፡  የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን የእነዚህን ምርቶች ወርሃዊ የወጪ ንግድ ዕቅድና አፈጻጸም በተመለከተ ካሠራጨው መረጃ መረዳት እንደተቻለው፣ የነሐሴ 2010 ዓ.ም

የይርጋጨፌ ቡና የዓለም ዲጂታል ግብይትን የሚቀላቀልበት ሙከራ ተጀመረ

ብሩክሊን ሮስቲንግ የተሰኘው የቡና ኩባንያ ከታዋቂው የኮምፒውተርና የሶፍትዌር አምራች አይቢኤም ኩባንያ ጋር በመሆን የይርጋጨፌ ቡናን በዓለም የዲጂታል ግብይት መድረክ ለማገበያየት የሚያስችል የሙከራ ትግበራ ለመጀመር መዘጋጀታቸው ታወቀ፡፡

በምርት ገበያው የሚያዝያ ወር ግብይት አሽቆለቆለ

ባለፉት ተከታታይ ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኩል ከፍተኛ ግብይት ሲፈጸምባቸው የነበሩት የቡና፣ የሰሊጥ፣ የቦሎቄና የማሾ ምርቶች በሚያዝያ ወር ያስመዘገቡት የግብይት መጠን ዝቅተኛ እንደነበር ተገለጸ፡፡ በሚያዝያ ወር የተመዘገበው ዝቅተኛ ግብይት፣ አጠቃላይ የምርት ገበያውን ወርኃዊ የግብይት መጠንና የግብይት ዋጋ ከቀደመው ወር አኳያ ዝቅ እንዲል አስገድዷል፡፡

የንግድ ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ዛሬ ይፋ ይደረጋል

ንግድ ሚኒስቴር የአገሪቱን አጠቃላይ የዘጠኝ ወራት የወጪና ገቢ ንግድ አፈጻጸም ሪፖርት ለማሳወቅ ለረቡዕ ግንቦት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ቢይዝም፣ ከቡና ወጪ ንግድ የተመዘገበው የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ይፋ ተደርጓል፡፡  በ2010 በጀት ዓመት ከሐምሌ እስከ መጋቢት ወራት ውስጥ የታየው የቡና የወጪ ንግድ አፈጻጸምን በማስመልከት የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ግብይትና ልማት ባለሥልጣን ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያሳየው ለውጭ ገበያ ከቀረበው ቡና የተገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ 560.24 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡