Skip to main content
x

የሹመቱን ነገር እስኪ እንነጋገር!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሥልጣን ከያዙ ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ ካቢኔያቸውን እንደገና አደራጅተው፣ ማክሰኞ ጥቅምት 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ሃያ አባላት ያሉትን ካቢኔ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ አፀድቀዋል፡፡

ውዥንብሮች ትርምስ እየፈጠሩ አገር አይታመስ!

ፈጣን፣ ቀልጣፋና ውጤታማ የመረጃ ልውውጦች ባለመኖራቸው ምክንያት ግልጽነት የጎደላቸው በርካታ ድርጊቶች ይስተዋላሉ፡፡ አንድ ብሔራዊ ጉዳይ ሲያጋጥም በቀጥታ የሚመለከተው መንግሥታዊ አካል በፍጥነት መረጃ ስለማይሰጥ፣ አገር ምድሩ በአሉባልታና በመሠረተ ቢስ ወሬዎች ይጥለቀለቃል፡፡

ጠመንጃ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ መውጣት አለበት!

በኢትዮጵያ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግሉን ለመቀላቀል የተለያዩ አማፂ ኃይሎች፣ ከኤርትራ በየተራ ወደ አገር ቤት መመለሳቸው ይታወሳል፡፡ እነዚህ አማፂ ኃይሎች ከዚህ ቀደም ትጥቅ አንግበው በረሃ የገቡት፣ በሥልጣን ላይ ያለው ኢሕአዴግ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንዳናደርግ ስለገፋን የትጥቅ ትግል ይሻለናል ብለው ነበር፡፡

የሐሳብና የተግባር አንድነት የሚረጋገጠው የሕግ የበላይነት ሲከበር ብቻ ነው!

ኢሕአዴግ በሐዋሳ ከተማ ያካሄደው 11ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ የሐሳብና የተግባር አንድነት ተረጋግጦ በነፃነት፣ በግልጽነትና በአሳታፊነት በተደረገ ውይይት ውሳኔ ላይ ተደርሶ እንዲጠናቀቅ የብዙዎች ጉጉት ነበር፡፡ በኢትዮጵያ የተጀመረው ለውጥ በሕዝብ ከፍተኛ ግፊት ተደርጎበት ከውስጥ ባሉ የለውጥ ኃይሎች የበላይነት ቢጀመርም፣ በተለያዩ መንገዶች ይደረጉ የነበሩ ችግር ፈጣሪ እንቅስቃሴዎች ለሰላምና ለመረጋጋት  ጠንቅ ሆነው ቆይተዋል፡፡

የኢሕአዴግ ነገር ብዙ ያነጋግራል!

የኢሕአዴግ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ከረቡዕ መስከረም 23 ቀን እስከ 25 ቀን 2011 ዓ.ም. በደቡብ ክልል ርዕሰ ከተማ ሐዋሳ ይካሄዳል፡፡ መሰንበቻውን የግንባሩ አራት ብሔራዊ ድርጅቶች በጉባዔያቸው የሥራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮሚቴዎች ምርጫ በማድረግ፣ በአመዛኙ አዳዲስ አመራሮች ወደፊት አምጥተዋል፡፡

አገር ፀንታ የምትቆመው ቅንነትና ሰፋ ያለ ዕይታ ሲኖር ነው!

በአሁኑ ጊዜ ውስብስቡን የኢትዮጵያ ችግር ለመፍታት የአገር ፍቅር፣ ዕውቀት፣ ብስለት፣ ቅንነትና ሰፋ ያለ ዕይታ ያስፈልጋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ጫፍ ድረስ በታሪኩ የሚታወቀው ለአገሩ ባለው ጥልቅ ፍቅርና ተወዳዳሪ በሌለው አስተዋይነቱ ነው፡፡

የሚያዋጣው በሥርዓት መምራትና መመራት ነው!

ተወደደም ተጠላም ለአገር የሕግ የበላይነት ያስፈልጋል፡፡ በሕግ የበላይነት የማይተዳደር አገር የሥርዓት አልበኞች መፈንጫ ይሆናል፡፡ የሕግ የበላይነት ማለት ደግሞ ሁሉም ዜጎች በሕግ ፊት እኩል የሚሆኑበትና የሚዳኙበት ነው፡፡ በሕግ የበላይነት ስም ግን አድልኦና ሸፍጥ የሚፈጸም ከሆነ፣ የምንነጋገረው ስለሕገወጥነት ይሆናል ማለት ነው፡፡

የሕዝብን ቀልብ የሚገዛው የላቀ ሐሳብ ብቻ ነው!

መልካም አጋጣሚዎችን በማምከን የሚታወቀው የኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ በመስዋዕትነት የተገኘውን ለውጥ ለመቀልበስ ለሚያግዝ ከንቱ ትንቅንቅ መደላድል እየፈጠረ ነው፡፡ ሕዝብ የዴሞክራሲ ጭላንጭል እያየ ተስፋ ሰንቆ አዲሱን ዓመት በተቀበለ ማግሥት፣ የተጀመረውን ለውጥ መቀመቅ የሚከት ሰቅጣጭ ጥቃት በወገኖቻችን ላይ ተፈጽሟል፡፡

ነውጠኛ ባህሪያት ለአገር አይጠቅሙም!

ኢትዮጵያን ከአምባገነናዊ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማሸጋገር የሚቻለው፣ ነውጠኛ ባህሪያትን አስወግዶ ዴሞክራሲያዊነትን በመላበስ ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚገነባው ደግሞ ልዩነቶችን ማክበርና መቀበል ሲቻል ነው፡፡ ዴሞክራሲ አፋኝነትን፣ ጉልበተኝነትንና ጥጋበኝነትን ማስተናገድ አይችልም፡፡