Skip to main content
x

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፓርላማ ሳያፀድቀው አስፈጻሚ አካላትን ማደራጀት የሚያስችለው ሥልጣን ተሰጠው

ማክሰኞ ጥቅምት 6 ቀን 2011 ዓ.ም. የተካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክት ቤት የ4ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ባፀደቀው የፌዴራል መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅን ሲያፀድቅ፣ ካሁን በፊት በአዋጅ ይደረግ የነበረው የአስፈጻሚ አካላትን የማደራጀት ሥልጣን በደንብ አማካይነት ማድረግ እንዲችል ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ሥልጣን ሰጠ፡፡

የዜጎችን መብትና ነፃነት አፋኝ ነው የተባለው የፀረ ሽብርተኝነት ሕግ እንደገና እንዲቀረፅ ጥያቄ ቀረበ

በምርጫ 97 ማግሥት የወጣው የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ የዜጎችን መብት፣ ነፃነትና አጠቃላይ እንቅስቃሴን አፋኝና ገዳቢ በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ተሰርዞ ውይይት ተደርጎበት መቀረፅ እንዳለበት ተገለጸ፡፡

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ማበረታቻዎችን እንደሚከልስ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የአገሪቱን የኢንቨስትመንት አዋጅ በማሻሻል የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን እንደሚከልስ አስታወቀ፡፡ የኢንቨስትመንት ኮሚሽነሩ በላቸው መኩሪያ (ዶ/ር) ከምክትሎቻቸው ጋር በመሆን ማክሰኞ ነሐሴ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ በኢንቨስትመንት አዋጁ ላይ ማሻሻያ ይደረጋል፡፡

ከሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች ጋር የሚጣረሱና የሚቃረኑ አዋጆችን የማሻሻል ጅማሮ

ከአሥራ ሰባት ዓመታት የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ በ1983 ዓ.ም. ደርግን በማሸነፍ፣ የኢሕአዴግ መንግሥት ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ጀምሯል፡፡ ከአራት ዓመታት ቆይታ በኋላ አገሪቱ የምትመራበትን ሕገ መንግሥትም በ1987 ዓ.ም. አፅድቋል፡፡

ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ የቅጅ መብት ሕግ ጥሷል ተብሎ የፍትሐ ብሔር ቅጣት ተወሰነበት

ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 410/96 እና የተሻሻለውን አዋጀ ቁጥር 872/2007 አንቀጽ (41)ን ተላልፏል ተብሎ፣ የተመሠረተበትን የፍትሐ ብሔር ክስ ማስተባበል ባለመቻሉ ቅጣት ተወሰነበት፡፡

መንግሥት ያቀረበው የምሕረት መስጫ አዋጅ ሳይፀድቅ ፓርላማው ለእረፍት ተበተነ

በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው ለተያዙ፣ ለተፈረደባቸውና ሳይያዙ በውጭ አገር በስደት ለሚኖሩ ግለሰቦችና የሕግ ሰውነት ላላቸው አካላት ምሕረት ለመስጠት መንግሥት ያቀረበው የምሕረት መስጫ አዋጅ ሳይፀድቅ፣ ፓርላማው የዓመቱን የሥራ ጊዜውን አጠናቆ ለእረፍት ተበተነ፡፡

በኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ መካከል የሚደረገው የቤት ሠራተኞች ቅጥር ስምምነት አዋጅ ፀደቀ

በኢትዮጵያና በሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥታት መካከል የቤት ሠራተኞችን ቅጥር አስመልክቶ፣ ከአንድ ዓመት በፊት የተደረገው ስምምነት ረቂቅ አዋጅ በፓርላማ ፀደቀ፡፡ በተለይ በሳዑዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ ከአራት ዓመታት በፊት ደርሶ በነበረው የሞት፣ አካል መጉደልና እንግልት ምክንያት የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የሚደረጉ ጉዞዎችን ማስቆሙ ይታወሳል፡፡

የተዘነጋውን የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ዘመን ለማሻሻል ረቂቅ አዋጅ ቀረበ

ባለፈው ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተዘንግቷል የተባለለት የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ዘመን ለማራዘም ሲጠበቅ የነበረውን ቻርተር ለማሻሻል የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ፣ ማክሰኞ ሰኔ 26 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀረበ፡፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የአበል ማሻሻያ ረቂቅ አዘጋጅ

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉ ገቢዎች አፈጻጸምን የተመለከተውን መመርያ በማሻሻል፣ የትራንስፖርትና ሌሎች አበሎችን ክፍያ የሚያሻሽል ተጨማሪ ተፈጻሚ ድንጋጌዎችን ያካተተ ረቂቅ መመርያ አዘጋጀ፡፡ ሚኒስቴሩ በአዲሱ ረቂቅ መመርያ የትራንስፖርት አበልና የመጓጓዧ ወጪን በተመለከተ እንደጠቀሰው፣ ከግብር ነፃ እንዲሆን በቀድሞ ድንጋጌው ላይ የተጠቀሰውን የቀን ውሎ አበል ጣሪያ ከ225 ወደ 500 ብር ከፍ ተደርጓል፡፡