Skip to main content
x

በመንግሥት ላይ 11.9 ሚሊዮን ብር ጉዳት በማድረስ የተከሰሱ ኃላፊዎች ገንዘቡን በመመለሳቸው ክሳቸው ተቋረጠ

የመንግሥትን ሥራ በማያመች አኳኃን በመምራት በመንግሥት ላይ ከ11.9 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ፣ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ከአንድ ዓመት በፊት ተመሥርቶባቸው የነበሩት፣ የቀድሞ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፀዳለ ማሞን ጨምሮ የአራት ኃላፊዎች ክስ ተቋርጦ ከእስር ተፈቱ፡፡

በቡራዩና አካባቢው ሰው በመግደልና ንብረት በማውደም 38 ግለሰቦች በሽብርተኝነት ተጠረጠሩ

ከመስከረም 2 እስከ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ በቡራዩ ከተማና አካባቢው በተፈጸመ ግድያ፣ የንብረት ቃጠሎና ዘረፋ ጋር በተያያዘ ታስረው ከነበሩት በርካታ ተጠርጣሪዎች ውስጥ፣ የ38 ግለሰቦች ድርጊት የሽብር ወንጀል ድርጊት ነው በመባሉ የ28 ቀናት የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ፡፡

መንግሥት የሽግግር ወቅት ፍትሕ እየተገበረ ይሆን?

‹‹አገር ተዘርፋ፣ ወገንም ተሰቃይቶ ከማለቁ በፊት ለውጥ እንዲመጣ ታግሎ አሁን ለደረስንበት የተስፋ ዘመን አድርሶናል፡፡ ስለዚህም መንግሥት የሕዝብን ጥያቄ መመለስ ውዴታው ብቻ ሳይሆን ግዴታውም ነው፡፡ ፍትሕ የተበደለን ሕዝብ የመካሻ አንዱ መንገድ ነውና፡፡››

የሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር በቁጥጥር ሥር ውለው አዲስ አበባ ገቡ

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የመያዣ ዋራንት ተቆርጦ ሲፈለጉ የነበሩት የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ (ሜቴክ) የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው፣ በሁመራ አድርገው ወደ ሱዳን ሊወጡ ሲሉ በትግራይ ክልል ልዩ ኃይል በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ አዲስ አበባ ገቡ፡፡

በሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና በከፍተኛ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 63 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የሚያዙ ሰዎችን ወደ መደበኛ እስር ቤት ከመቅረባቸው በፊት በአገሪቱ በተለያዩ ቦታ በሚገኙ ሥውር እስር ቤቶች ውስጥ በማሰር ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል የተባሉ፣ እንደሁም ሕገወጥ ግዥ በመፈጸም በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ዘርፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ 63 ግለሰቦች ቅዳሜ ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ውለው፣ ሰኞ ኅዳር 3 ቀን 2011 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

የክስ መመሥረቻ የመጨረሻ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው የቦምብ ፍንዳታ ተጠርጣሪ ላይ ተጨማሪ ጊዜ ተፈቀደ

የክስ መመሥረቻ የመጨረሻ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሹም የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ተጨማሪ ምርመራ ተፈቀደ፡፡ በተጠረጠሩበት የወንጀል ድርጊት ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ ለከሳሽ ዓቃቤ ሕግ የምርመራ መዝገቡን በማስረከቡ፣ የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ዓቃቤ ሕግ በሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም.

በቡራዩና በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጸሙ ግድያና ውድመት የተጠረጠሩ 89 ግለሰቦች ምርመራ ወደ ፌዴራል ተዛወረ

ከመስከረም 2 እስከ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩ ከተማና አካባቢው፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍላተ ከተሞች ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ በበርካታ ሰዎች ሞት፣ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዝርፊያ የተጠረጠሩ 89 ግለሰቦች ምርመራ ወደ ፌዴራል የሕግ ተቋማት ተዛወረ፡፡

የፍትሕ ሥርዓቱ ነፃነትና ገለልተኝነት መፈተን አለበት!

በኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት ላይ በዋነኛነት ከሚነሱ ችግሮች መካከል ተጠቃሹ የሕዝብ አመኔታ ማጣት ነው፡፡ የሕዝብ አመኔታ ያጣ ተቋምን እንደገና እንዲያንሰራራ ለማድረግ መሠረታዊ ለውጥ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ለውጥ ግን ማዕበል መፍጠር አለበት፡፡ በሕዝብ ዘንድ የነበረውን የተበላሸ ገጽታ መለወጥ የሚፈልግ የፍትሕ ሥርዓት፣ ከማዕበሉ በኋላ ራሱን ችሎ መቆም መቻልም ይኖርበታል፡፡

በሙስና ወንጀል በተከሰሱት የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ ኃላፊ ላይ ብይን ተሰጠ

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የሺፒንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት ዓለሙ አምባዬ (ቺፍ ኢንጂነር)፣ ተጠርጥረው በተከሰሱበት ከባድ የሙስና ወንጀል እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ፡፡+-+-+-

በከባድ የሙስና ወንጀል የተከሰሱት የስኳር ኮርፖሬሽን ኃላፊዎችና ግለሰቦች ተከላከሉ ተባሉ

መንግሥት በመጀመርያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ሊገነባቸው ካሰባቸው አሥር የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ በሆነው ኦሞ ኩራዝ 5 ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ላይ፣ ከባድ የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ሦስት ኃላፊዎችና አራት ግለሰቦች እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ፡፡