Skip to main content
x

‹‹የኮርፖሬሽኑን ቤቶች በሕገወጥ መንገድ በያዙና ባስተላለፉ ላይ ዕርምጃ ይወሰዳል››

በኢትዮጵያ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ የመኖርያ ቤቶች እጥረት እንዳለ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ከዚህ ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው በአዲስ አበባ ከተማ የተፈጠረው እጥረት ነው፡፡ የደርግ ዘመን ካበቃ በኋላ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በሕዝብ ቁጥር ዕድገቱ ልክ የመኖሪያ ቤቶች ባለመገንባታቸው፣ ጫናው መሰማት የጀመረው ዘግይቶ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ1996 ዓ.ም.

‹‹ከ6.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚፈልጉ የኤሌክትሪክ ኃይልና የትራንስፖርት ፕሮጀክቶችን በመንግሥትና በግል አጋርነት ለማከናወን የጨረታ ሒደት እየተጠበቀ ነው››

ተሾመ ታፈሰ (ዶ/ር) ዋና ዳይሬክተር በመሆን በቅርቡ በአዋጅ የተቋቋመውን የመንግሥትና የግል ዘርፍ አጋርነት ዳይሬክቶሬት ጄኔራል የተሰኘውንና በገንዘብ ሚኒስቴር ሥር የሚገኘውን መሥሪያ ቤት በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ ተመድበው ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡

‹‹በነዳጅ ላይ እየተከሰተ ያለው ችግር አሻጥር ነው›› አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም፣ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ

አገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከምታወጣባቸው የገቢ ምርቶች ውስጥ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት ውስጥ አንዱ ነዳጅ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በዓመት እስከ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ለነዳጅ ግዥ ታወጣለች፡፡

‹‹ወደብ አልባ አገር ሆኖ ባህር ኃይል መገንባት ይከብዳል››

ካፒቴን አየለ ኃይሌ፣ የቀድሞ ባህር ኃይል አካዴሚ ዋና አዛዥና የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት የሥልጠና ማዕከል መሥራች ካፒቴን አየለ ኃይሌ የተወለዱት የቀድሞው ሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት ኤጀርሳ ጎሮ ለመድረስ ሦስት ኪሎ ሜትር ሲቀረው በሚገኘውና ልዩ ስሙ ጣጤሳ በተባለው መንደር ነው፡፡ የሦስት ዓመት ሕፃን እያሉ አባታቸው በጦር ሜዳ በፋሺስት ጣሊያን ጦር ተረሽነዋል፡፡ አባቶቻቸው በጦር ሜዳ ለተሰውባቸው ልጆች ተብሎ በተቋቋመው ሐረር ልዑል ራስ መኮንን የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ከዚያም በአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ትምህርት ቤት ገብተው ተምረዋል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁን ያለበትን ጉዞ ባናጨናግፍ ጥሩ ነው›› አቶ ግርማ ዋቄ፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ

አቶ ግርማ ዋቄ በወጣትነታቸው ኢትዮጵያ አየር መንገድ በመግባት፣ እዚያው ተምረውና አድገው በተለያዩ ኃላፊነት ቦታዎች ለ34 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በመካከል ቅሬታ አድሮባቸው ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሄደው የገልፍ አየር መንድንና ዲኤቾ ኤል ኩባንያን በኃላፊነት አገልግለዋል፡፡

‹‹የሴቶች አመራር ለውጥ ያመጣል ብዬ አስባለሁ›› ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጥ፣ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጥ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት የመጀመርያዋ ሴት ሆነዋል፡፡ ከአንድ ሳምንት በፊት ንግድ ምክር ቤቱ ባካሄደው ምርጫ ወ/ሮ መሰንበት ተፎካካሪያቸውን በሰፊ ልዩነት በማሸነፍ፣ የፕሬዚዳንትነቱን ኃላፊነት ተረክበው ሥራ ጀምረዋል፡፡ የ54 ዓመቷ ወ/ሮ መሰንበት ከዚህ ቀደም የንግድ ምክር ቤቱ ቦርድ አባል በመሆን ያገለገሉ ሲሆን፣ ለንግድ ምክር ቤቱ አዲስ አለመሆናቸውንም ይገልጻሉ፡፡

‹‹የግሉ ዘርፍ የሚያቀርባቸውን መፍትሔዎች በመጠቀም በርካታ የሥራ ዕድሎችን መፍጠር ይቻላል››

ሰርጂዮ ፒሜንታ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (አይኤፍሲ) ምክትል ፕሬዚዳንት ሲሆኑ፣ የተቋሙን የአፍሪካና የመካከኛው ምሥራቅ የኦፕሬሽን ሥራዎች እንዲመሩ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል፡፡ የዓለም ባንክ የግሉ ዘርፍ ክንፍ የሆነው ይህ ተቋም የልማት ፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፎችን በማቅረብ፣ በተለይም የግል ዘርፉን በመደገፍ የሚታወቅ የዓለም ባንክ አካል ነው፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት ችግር እንዲፈጠር አንፈልግም››

ሳዓድ ዓሊ ሺሬ (ዶ/ር) የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ. በ2015 ለዚህ ኃላፊነት በተሾሙ ጊዜ አገሪቱን ያስተዳድር የነበረው መንግሥት ሌላ ነበር፡፡ ይሁንና ባለፈው ዓመት በተደረገ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሁን አገሪቱን የሚመሩት ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ ዓሊ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦታቸውን ይዘው እንዲቀጥሉ መርጠዋቸዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያን አንድ ላይ ሆነን የምናሳድግበት ጉዳዮች ላይ ከተስማማን ሁሉም ነገር ቀላል ነው›› አቶ ታደሰ ጥላሁን፣ የኖክ ዋና ሥራ አስፈጻሚና የኢትዮጵያ ነዳጅ ኩባንያዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት

አቶ ታደሰ ጥላሁን የናሽናል ኦይል ኩባንያ (ኖክ) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡ የከፍተኛ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ  ከ40 ዓመታት በላይ በተለያዩ ኩባንያዎች ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነቶች ሠርተዋል፡፡ መጀመርያ ተቀጥረው የሠሩት በአዲስ አበባ ሲሚንቶ ፋብሪካ ነው፡፡