Skip to main content
x

በሕገወጥ መንገድ የተያዙ 500 ቤቶች በዕጣ ሊከፋፈሉ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ባደረገው ጥናት፣ በሕገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 500 ቤቶችን በማግኘቱ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች በዕጣ ሊያከፋፍል ነው፡፡ በምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) አዲስ ካቢኔ ውስጥ በመካተት የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት፣ ሰናይት ዳምጤ (ኢንጂነር) እንደተናገሩት፣ ከከተማ እስከ ወረዳ በተዘረጋ ጥናትና ክትትል እስካሁን 500 የጋራ መኖሪያ ክፍት ቤቶች፣ በሕገወጥ መንገድ የተያዙና ውል የሌላው ቤቶች ተገኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በድጋሚ የመኖሪያ ቤቶች ቆጠራ እንዲካሄድ አዘዘ

የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንዶሚኒየምና የቀበሌ ቤቶች ቆጠራ ቢያካሄድም፣ በውጤቱ ያልረካው የአዲሱ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ካቢኔ በድጋሚ ቆጠራ እንዲካሄድ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሒደት ራሱን ከመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ውጪ እንደሚያደርግ አስታወቀ

በኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ እየተፈተነ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከመኖሪያ ቤቶች ግንባታ እንደሚያወጣና ግንባታውን የግሉ ዘርፍ እንዲያካሂድ ማድረግ የሚያስችል አሠራር እንደሚዘረጋ አስታወቀ፡፡

ተሰናባቹ ከንቲባ ቀጣዩ አስተዳደር ሊያተኩርባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ጠቆሙ

ተሰናባቹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ሰኞ ሐምሌ 2 ቀን 2010 ዓ.ም. ለምክር ቤቱ ባቀረቡት የአምስት ዓመት የሥራ ዘመን ማጠቃለያ ሪፖርት፣ ቀጣዩ የከተማው አስተዳደር ነዋሪዎችን እያስጨነቁ የሚገኙ ችግሮች በተለይም ድህነት፣ ሥራ አጥነት፣ መልካም አስተዳደርና የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ላይ ትኩረት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳሰቡ፡፡

ለመንግሥት ተሿሚዎችና ሠራተኞች ከ16 ሺሕ በላይ ቤቶች በ33 ቢሊዮን ብር ሊገነቡ ነው

ከአንድ ዓመት በፊት እንደ አዲስ የተዋቀረው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ በአዲስ አበባ ለሚገኙ የመንግሥት ተሿሚዎችና ሠራተኞች 16,173 የጋራና ለኪራይ የሚውሉ ቤቶች በ33 ቢሊዮን ብር ለመገንባት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቁ፡፡

የውጭ ኩባንያዎችን በቤቶች ግንባታ ለማሳተፍ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ምክረ ሐሳብ ሊቀርብ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባቋቋሙት ካቢኔ አባል ሆነው ወደ ፌዴራል መንግሥት የመጡት የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትሩ አቶ ጃንጥራር ዓባይ፣ የውጭ አገር ኩባንያዎች በኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ እንዲሳተፉ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ምክረ ሐሳብ ሊያቀርቡ መሆኑ ታወቀ፡፡ ቀደም ሲል በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ እየተጓተተ በመሆኑና የኅብረተሰቡ የመኖሪያ ቤት ጥያቄ የዚያኑ ያህል አይሎ ስለነበር፣ የውጭ አገር ኮንትራክተሮችን ለማሳተፍ ታቅዶ  የጨረታ ሒደት ተጀምሮ ነበር፡፡

በግንባታ ማጠናቀቂያ ዕቃዎች የዋጋ ንረት ሳቢያ ይጠናቀቃሉ የተባሉት የ40/60 ቤቶች ችግር ገጥሟቸዋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ በ40/60 ቤቶች ፕሮግራም እየተገነቡ የሚገኙ 17‚737 ቤቶች በሚቀጥለው ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚጠናቀቁ ቢገልጹም፣ ዋጋቸው እየናረ ለሚገኘው የግንባታ ማጠናቀቂያ ዕቃዎች ዋጋ በጀት ባለመኖሩ ዕቅዱ የሚሠራ አለመሆኑን ምንጮች ገለጹ፡፡ ከንቲባ ድሪባ ከሳምንት በፊት ለከተማው ምክር ቤት ባቀረቡት የ2010 ዓ.ም. የዘጠኝ ወራት ሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ በ40/60 ፕሮግራም ከሚገነቡት 38‚240 ቤቶች ውስጥ 17‚737 ቤቶች በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ እንደሚጠናቀቁ ገልጸው ነበር፡፡

ለመንግሥት ሠራተኞች በኪራይ የሚተላለፉ አፓርታማዎች ግንባታ ተጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመንግሥት ሠራተኞች ብቻ በኪራይ የሚተላለፉ አፓርታማዎች ግንባታ ጀመረ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ በጀመረው ፕሮጀክት በመጀመርያው ዙር 23 ሕንፃዎች፣ በሁለተኛው ዙር 22 ሕንፃዎች፣ በድምሩ 1,718 መኖርያ ቤቶችን የያዙ 45 ሕንፃዎችን ለመገንባት ዕቅድ ይዟል፡፡

በርካታ የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ቁጠባቸውን እያቋረጡ ነው

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ባለቤት ለመሆን ከ900 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች የተመዘገቡ ቢሆንም፣ አብዛኞቹ ወርኃዊ ቁጠባቸውን እያቋረጡ መሆኑ ታወቀ፡፡  የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ነዋሪዎቹ ቁጠባቸውን የሚያቋርጡት ከአቅም ጋር በተያያዘ ከሆነ ምርጫቸውን ማስተካከል እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡

ከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር እስከ ሰኔ መጨረሻ 32 ሺሕ የጋራ ቤቶች ይጠናቀቃሉ አለ

በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ በተለያዩ ችግሮች እየተንጓተተ ቢሆንም፣ በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ 32 ሺሕ ቤቶች እንደሚጠናቀቁ ተመለከተ፡፡ በከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትሩ አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) የሚመራ ቡድን ሐሙስ ጥር 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በተለያዩ ሳይቶች ጉብኝት አድርጓል፡፡ አስተዳደሩ በአጠቃላይ ከሚገነቧቸው 94,070 ቤቶች ውስጥ በመጋቢት 2010 ዓ.ም. 22 ሺሕ ቤቶችን፣ ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ደግሞ 50 ሺሕ ቤቶችን የማጠናቀቅ ዕቅድ ነበረው፡፡