Skip to main content
x

ለደሃ አገሮች ቃል የተገባላቸው ድጋፍ ካልተተገበረ የኑሮ ልዩነት እንደሚባባስ ተመድ አስጠነቀቀ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንግድና የልማት ጉባዔ በቅርቡ ይፋ ባደረገው ትንታኔ መሠረት፣ አብዛኞቹ በድህነት ውስጥ የሚገኙ 47 በኢኮኖሚ ኋላ የቀሩ አገሮችን ከኢኮኖሚ ለመደገፍ የበለፀጉ አገሮች ቃል ቢገቡም፣ በዓለም ኢኮኖሚ ዕድገት መዳከም ሳቢያ ለመስጠት የገቡትን ቃል ከማክበር ሲያፈገፍጉ ይታያሉ፡፡ በዚህ ሳቢያም ልዩ ድጋፍ ሊደረግላቸው የሚገባቸው ድሆቹ አገሮች እ.ኤ.አ. በ2030 መጨረሻ ዕውን እንዲሆኑ የተቀመጡትን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ያወጣቸውን ዘላቂ የልማት ግቦች የማሳካት ዕድላቸው የመነመነ ስለመሆኑ አስጠንቅቋል፡፡

ሙዚቃ ለሰላም

‹‹ሚውዚክ ፎር ፒስ›› (ሙዚቃ ለሰላም) የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት የተካሄደው የአፍሪካን አርቲስትስ ፒስ ኢንሽዬቲቭ (ኤኤፒአይ) ፎረምን ተከትሎ ነበር፡፡ በአፍሪካ ውስጥ ያሉ አርቲስቶችና የመብት ተሟጋቾች ስብስብ የሆነው ኤኤፒአይ፣ የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤን አስታኮ የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ የውይይቱ ቀዳሚ ትኩረት ሙስናን በመዋጋት ረገድ አፍሪካውያን አርቲስቶች ምን ሚና አላቸው? የሚለው ነበር፡፡ በውይይቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የተውጣጡ ድምፃውያን፣ ገጣሚዎች፣ ዲዛይነሮች፣ ፊልም ሠሪዎችና ሌሎችም የጥበብ ሰዎች ተሳትፈዋል፡፡ ጥር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. የተጀመረው ውይይት የተገባደደው ጥር 19 በተካሄደው የሙዚቃ ኮንሰርት ነው፡፡

የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ተቃውሞ ገጠመው

የአፍሪካን የአየር ትራንስፖርት አውታር ወደፊት እንደሚያራምድ የታመነበት የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ምሥረታ ተቃውሞ ገጠመው፡፡ የአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ገበያ በክልከላ የተተበተበ በመሆኑ የአፍሪካ የአየር መንገዶች ዕድገት ፈታኝ እንዳደረገው ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የገበያ ክልከላን በማስቀረት የአፍሪካ አየር መንገዶች አፍሪካ ውስጥ በነፃነት ከአገር አገር እንዲበሩ የሚያስችል የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ምሥረታ፣ ጥር 20 እና 21 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በተካሄደው 30ኛው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባዔ በይፋ አውጇል፡፡ ሰኞ ጥር 21 ቀን በተካሄደው የመሪዎች ጉባዔ የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ መመሥረቱን ያወጁት አዲሱ የኅብረቱ ሊቀመንበር የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ናቸው፡፡ ፖል ካጋሜ የአፍሪካ የጋራ የአየር ትራንስፖርት ገበያ ምሥረታ ለአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ዕድገት ትልቅ ዕርምጃ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

30ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔና የአኅጉሪቱን ሁለንተናዊ ችግሮች ለመፍታት ቁርጠኝነት ማጣት

የአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት፣ የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተቋቋመው በ1955 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ነው፡፡ ድርጅቱ ለመጀመርያ ጊዜ የተቋቋመው በ32 የአፍሪካ አገሮች ነው፡፡ ኅብረቱ ደቡብ አፍሪካ አባል እስከሆነችበት እ.ኤ.አ 1994 ድረስ 53 አገሮችን በአባልነት የያዘ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት 55 አገሮችን ያቀፈ አኅጉራዊ ድርጅት ቢሆንም፣ ከእነዚህ መካከል በኅብረቱ ንቁ ተሳትፎ የሌላቸው አገሮች ይገኙበታል፡፡

ጽንፈኝነት ለማንም አይበጅም!

ኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊ አገር ናት፡፡ ከብሔር ማንነት ጀምሮ ቋንቋ፣ ባህል፣ እምነትና የመሳሰሉ በርካታ መገለጫዎች ባሉባት በዚህች ታሪካዊ አገር ውስጥ የአንድ ጎራ ኃያልነት ወይም የበላይነት ከቶውንም ሊኖር አይችልም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለያዩ ዘመናት በተነሱ ገዥዎች ሥር ቢተዳደርም፣ ደጉንና ክፉን ጊዜ ያሳለፈው ግን ተሳስቦና ተደጋግፎ መሆኑን ፈጽሞ መካድ አይቻልም፡፡ ይህ ጨዋና አስተዋይ ሕዝብ አገሩን ከወራሪዎችና ከተስፋፊዎች በአንድነት ሲጠብቅ ዘመናትን ያሳለፈው፣ ከልዩነት ይልቅ ለአንድነት ትልቅ ግምት በመስጠቱ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የሚታየውን የሠራተኞች ብዝበዛ ያጣጣለው የዓለም ሠራተኞች ኮንፌደሬሽን ዝቅተኛ የደመወዝ ጣሪያ እንዲደነገግ ጠየቀ

ለሁለት ቀናት በተካሄደውና የአፍሪካ ሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲደነገግላቸው የጠየቀውን ፎረም ያዘጋጀው የዓለም ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን፣ በኢትዮጵያ የሚታየው የሠራተኞች ብዝበዛን ከመንቀፉም በላይ አገሪቱ ለሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚደነግግ ሥርዓት እንድትዘረጋ ጠየቀ፡፡ የዓለም የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ዋና ጸሐፊ ሻረን ባሮው ከረቡዕ ጥር 9 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት የተካሄደውን የአፍሪካ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ፎረም ሲከፍቱ እንደጠየቁት፣ ምንም እንኳ ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ የወደፊቷ የጨርቃ ጨርቅ ማዕከል ስለመሆኗ ቢዘገብም፣ በሠራተኞች ረገድ ግን ብዝበዛ የሚፈጸምባት አገር እንደሆነች በምሳሌ አሳይተዋል፡፡

የአይኤምኤፍ ዳይሬክተር የኢትዮጵያ የገንዘብ ፖሊሲ እንዲላላ ጠየቁ

ለግሉ ዘርፍ በሩን መክፍቱ የሉዓላዊነት ችግር አያመጣበትም ብለዋል የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስቲን ላጋርድ በኢትዮጵያ ባደረጉት የሁለት ቀናት ቆይታ፣ መንግሥት የገንዘብ ፖሊሲውን ማላላት እንዳለበት ጠየቁ፡፡ የተደረገውን የምንዛሪ ማሻሻያ እንደሚደግፉም አስታውቀዋል፡፡

የመሬት አልባ ወጣቶች ጉዳይ ወቅቱን ጠብቆ የሚፈነዳ ፈንጅ እንዳይሆን ምሁራን ሠግተዋል

ሊቢያውያን በስደተኞች የተፈጸሙት ፀያፍ ተግባር በርካቶችን አስቆጥቷል በአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ላይ ምሁራንና የባህል መሪዎች ከየአገራቸው በመሰባሰብ በአዲስ አበባ ሲመክሩ ሰንብተዋል፡፡ ስብሰባቸውን ሲቋጩም የአፍሪካ መሪዎች ስለወጣቶች እንዲያስቡ፣ በመሬት ፖሊሲዎቻቸው ውስጥ የወጣቶችን ባለድርሻነት እንዲያሰፍኑ የጠየቁት ተሰብሳቢዎቹ፣ የአፍሪካ ወጣቶች በአኅጉሪቱ የመሬት ይዞታ ውስጥ የባለቤትነት ድርሻ ከተነፈጋቸው ወደፊት ጊዜ ጠብቀው ሊፈነዱ የሚችሉ ፈንጂዎች ናቸው ሲሉም ሥጋታቸውን ሲያስተጋቡ ተደምጠዋል፡፡

ለኮንፈረንስና ለጉብኝት ኢትዮጵያ ለሚመጡ ቪዛ በቦሌ ኤርፖርት ማግኘት የሚችሉበት አሠራር መመቻቸቱ ተነገረ

ከአፍሪካ አገሮች ለኮንፈረንስ፣ እንዲሁም ከአውሮፓና ከአሜሪካ ለጉብኝት ኢትዮጵያ ለሚመጡ ቪዛ በቦሌ ኤርፖርት የሚያገኙበት አሠራር መመቻቸቱን፣ የኢምግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች ዋና መምርያ አስታወቀ፡፡

የአፍሪካ አገሮች ለወጣቶች ፍትሐዊ የመሬት ሥርጭትን የሚከተል ሥርዓት እንዲዘረጉ ተጠየቁ

የቀድሞው የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ኢኒሺዬቲቭ በአሁኑ አጠራሩ የአፍሪካ የመሬት ፖሊሲ ማዕከል የተሰኘው ተቋም፣ ከኅዳር 4 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ቀናት በሚቆየውና በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በመካሄድ ላይ በሚገኘው ስብሰባ የታደሙ ባለሙያዎች ወጣቶችን አሳታፊ የሚያደርግ ፍትሐዊ የመሬት ፖሊሲ በአፍሪካ እንዲተገበር ጠይቀዋል፡፡