Skip to main content
x

የባህል ልውውጡ የቶኪዮ የባህል ኦሊምፒያድ ይደርስ ይሆን?

የኢትዮጵያ የባህል ፖሊሲ የአገሪቱን ባህል ለተቀረው ዓለም በስፋት ለማስተዋወቅ የሚያስችሉ በባህል እኩልነትና የጋራ ጠቀሜታ ላይ የተመሠረቱ ጠንካራ አገራዊ፣ አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ግንኙነቶች መፍጠር እንደሚገባ ያመለክታል፡፡

በጠጅ ሰማይ

በኢትዮጵያ ጠጅን ጨምሮ ባህላዊ መጠጥ ማዘጋጀት መቼ እንደተጀመረ በልክ ባይታወቅም እስከዛሬ ድረስ በተደረጉ የአርኪዮሎጂ ጥናቶች፣ በቁፋሮ በተገኙ ቁሳቁሶች መሠረት በዘመነ አክሱም ከሦስት ሺሕ ዓመታት በፊት ጠጅ ይዘጋጅ እንደነበረ የሚያሳዩ በድንጋይ የተዘጋጁ መጠጫዎችና ብርጭቆዎች ተገኝተዋል፡፡

በቋንቋና ባህል ላይ ያተኮሩት አዲሶቹ ጥናቶች

በቋንቋና የጋራ ባህል እሴቶች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ባለሙያዎች ጋር የተካሄዱ ጥናቶች ስብስብን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለኅትመት አብቅቷል፡፡ የመጻሕፍቱን ማስተዋወቂያና ምረቃ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

የሁለት ቡሔዎች ወግ

ቡሔ ማለት ብርሃን፣ ገላጣ ወይም የብርሃን መገለጥ ማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ደብረ ታቦር ተብሎ የሚታወቀው ዓመታዊ በዓል በአውሮፓ ቋንቋዎች ‹‹ትራንስፊጉሬሽን›› (Transfiguration) ይባላል፡፡

31 ቀናት በሩሲያ ምድር

በዳዊት ቶሎሳየአውሮፕላኑ ካፕቴን በሩሲያዋ ዋና ከተማ ሞስኮ ከተማ ለማረፍ የደቂቃ ዕድሜ እንደቀረ ሲለፈፍ፣ ሁሉም ከእንቅልፉ መንቃት ጀመረ፡፡ በበረራ ቁጥር 1428 ግዙፉ የኳታር አውሮፕላን ውስጥ የነበረው ተሳፋሪ ሁሉ በጠባቧ መስኮት ብዙ የተነገረላትን ኃያል አገር ሞስኮ ለማየት ይንጠራራ ጀመር፡፡

‹‹ፎሌ በአያና ጩጳ››

ኢትዮጵያ ከምትታወቅባቸው የሃይማኖት በዓላት ውስጥ ጥምቀት አንዱ ነው፡፡ የገና ጾም ከተፈታ ሁለት ሳምንታት በኋላ መላውን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የሚያሰባስብ ክብረ በዓል ጥምቀት ቀዳሚ ነው፡፡ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎችም የአካባቢውን ወግና ሥርዓት በጠበቀ መልኩ ሲከበር ይስተዋላል፡፡ በምሥራቅ አርሲ ዞን ከጥምቀት በዓል ጎን ለጎን ‹‹ፎሌ›› ተጨማሪ ድምቀትን ይሰጣል፡፡

በዓል እና ገፀ በረከት

የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለች፣ ጓደኞቿ ለልደት በዓል ስጦታ መለዋወጥ እንደሚፈልጉ ነገሯት፡፡ የጓደኛሞቹ ስም በወረቀት ይጻፍና ተጠቅልሎ ዕጣ ይወጣል፡፡ ከመካከላቸው ማን የማን ስም የተጻፈበት ወረቅት እንደደረሰው ዕጣው በወጣበት ዕለት አይነጋገሩም፡፡ በሚስጥር ይያዛል፡፡ ወ/ሮ ቤተል ዓባይ እንደምትለው፣ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አንድ ወይም ሁለት ቀን ሲቀረው ስጦታ ይለዋወጣሉ፡፡

መሰናዶን በዲጂታል ማስታወቂያ

ብሩክ ሰውነትና ሲራክ ኃይሉ በአዲስ አበባና በሌሎች አጎራባች ከተሞችም የሚካሄዱ ዝግጅቶችን ከሚከታተሉ መካከል ናቸው፡፡ የጥበብ፣ የቢዝነስ፣ የጤና አልያም ሌላ መርሐ ግብሮች ሲዘጋጁ ስለ ዝግጅቶቹ መረጃ ለመሰብሰብ ይሞክራሉ፡፡ ሆኖም በአዲስ አበባም ይሁን በሌሎች ከተሞች ዝግጅቶች ሲኖሩ በተዋቀረ መንገድ ለሕዝብ የሚደርሱበት መንገድ እምብዛም ስላልሆነ ይቸገራሉ፡፡ ችግሩ የሁለቱ ብቻ ሳይሆን የብዙዎች ነው፡፡

ከአበቅየለሽ እስከ ፎር ሲስተርስ

‹‹ጨዋ ሰፈር›› የሚል መጠሪያ የተሰጠው መንደር ጎንደር ውስጥ ከሚገኙ ጥንታዊ መኖሪያ አካባቢዎች አንዱ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ የቦታ ስያሜ የሚሰጠው በምክንያት እንደመሆኑ፣ የአካባቢው ነዋሪዎችም ለሰፈሩ የሰጡትን ስም ምክንያት ያብራራሉ፡፡