Skip to main content
x

ለእግር ኳሱ ብሎም ለህልውናው የሚሰበከው ሰላም

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከደርቢ ጨዋታዎች የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና ክለቦች የሚያደርጉት ግጥሚያ ይጠቀሳል፡፡ እሑድ፣ ታኅሣሥ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም የተከናወነው የሁለቱ ቡድኖች ግጥሚያ በሌሎች አገሮች ከሚታዩ ደርቢዎች አንፃር ሲታይ ሚዛን ባይደፋም፣ እንደ አንጋፋ ተቀናቃኝነታቸው፣ እንደ ደጋፊዎቻቸው ብዛትና ንቃት ብዙ የተጠበቀው ጨዋታ ጉጉትን ቢያኮስስም፣ በዕለቱ የተላለፈው መልዕክት ግን በሰላም ዕጦት መደበኛ መርሐ ግብራቸውን ማከናወን ለተሳናቸው በርካታ ክለቦች የጎላ ፋይዳ እንዳለው ታይቷል፡፡

‹‹ለስፖርታዊ ጨዋነት መጓደልና ውጤት መጥፋት ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ተጠያቂ ናቸው›› የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ

በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች የሰላምን እሴቶች ጠብቀው መከናወን ይችሉ ዘንድ ስፖርት ኮሚሽንና ብሔራዊ ፌደሬሽኖች የተቀናጀ ሥራ መሥራት እንዳለባቸው የሴቶች፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጠይቋል፡፡

የአፄ ቴዎድሮስ 150ኛ ዓመት መታሰቢያ

ከዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ጋር ስማቸው አብሮ የሚነሳው አፄ ቴዎድሮስ በአኃዳዊ የአገዛዝ ሥርዓት አገሪቷን ያስተዳደሩ መሪ ናቸው፡፡ በትውልድ ስማቸው ካሳ ኃይሉ፣ በፈረስ ስማቸው አባ ታጠቅ፣ በወታደራዊ ስማቸው መይሳው ካሳ እንዲሁም አንድ ለእናቱ የተባሉ የአፄውን የተለያዩ ማንነቶች የሚያንፀባርቁ ስያሜዎች ናቸው፡፡ የተወለዱትም አገሪቷ በባላባቶች ተከፋፍላ በምትመራበት በዘመነ መሳፍንት  ወቅት ነበር። አባታቸው ደጃዝማች ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ የቋራ ገዢ ነበሩ።

ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ማገዱ ተሰማ

የኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ላለፉት ዘጠኝ ወራት የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅትን በዋና ዳይሬክተር ሲመሩ የቆዩትን አቶ ዮሐንስ ጥላሁን ከሰኞ የካቲት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ከሥራ እንዳገደ ተሰማ፡፡ ምክትላቸው አቶ የቻለ ምሕረት ድርጅቱን በውክልና እያስተዳደሩ እንዲቆዩ ወስኗል፡፡

የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ኢትዮጵያ የተከተለችውን የቱሪስቶች የቆይታ ጊዜና የገቢ ስሌት ውድቅ አደረገ

በዚህ ዓመት የመጀመርያዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ መንግሥት ከቱሪዝም ዘርፍ ከ1.8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታውቆ ነበር፡፡ ይሁንና ይህ ገቢ የተሰላበትን መንገድ ውድቅ የሚያደርጉ ትንታኔዎች ከዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ብቅ ብለዋል፡፡

የጥምቀት በዓልን በዩኔስኮ የማስመዝገብ ማመልከቻ ‹‹በመጋቢት›› ይገባል

በወርኃ ጥር የኢትዮጵያ አደባባዮች በበዓላት ደምቀው ይታዩበታል ከሚያሰኘው አንዱ የጥምቀት በዓል የሚከበርበት መሆኑ ነው፡፡ የውጭ ጸሐፍት ‹‹የአፍሪካው ኤጲፋኒያ›› (African Epiphany) በመባል በልዩ ልዩ ድርሳኖች የሚታወቀው የጥምቀት በዓልን በዩኔስኮ (የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት) በሰው ልጅ ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስነት ለማስመዝገብ (Representative List of Intangible Cultural Heritage of Humanity)  የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን በይፋ እንቅስቃሴ ከጀመረ ከርሟል፡፡

ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ቅርሶችን በተሻለ ለማስጠበቅ የሚረዳ ሕግ እያረቀቀ እንደሚገኝ አስታወቀ

በአገሪቱ የሚገኙ ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ የተፈጥሮና ሌሎችም ቅርሶችን በተሻለ ክብካቤና በባለቤትነት ስሜት ለማስጠበቅ ያግዛል ያለውን የሕግ ረቂቅ ማዘጋጀት እንደጀመረ ያስታወቀው ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ በቅርስ መዳረሻዎች አካባቢ የሚኖሩ ማኅበረሰቦች ከሚገኘው ገቢ እስከ 30 በመቶ እንዲደርሳቸው ማቀዱን ይፋ አድርጓል፡፡

የኮከብ ምደባ ከተካሄደባቸው 365 ሆቴሎች ውስጥ አስገዳጅ መሥፈርት ያሟሉት 167 ብቻ መሆናቸው ታወቀ

የፖለቲካ ቀውሱ የቱሪስት ፍሰቱን አልገታም ተብሏል ከሦስት ዓመት በፊት በወጣውና ካቻምና በ365 ሆቴሎች ላይ በተደረገ የኮከብ ደረጃ ምደባ መሠረት ተገቢውን መሥፈርት በማሟላት ደረጃ ያገኙት ሆቴሎች 135 ብቻ እንደሆኑ ታወቀ፡፡ አብዛኞቹ የንፅህና፣ የአደጋ ጊዜ መውጫና ሌሎችም አስገዳጅ መሥፈርቶችን ማሟላት ባለመቻላቸው ነው ተብሏል፡፡

ዮድ አቢሲኒያ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶብኛል የሚል አቤቱታ ለመንግሥት አቀረበ

ጥርጣሬውን ወደ አቶ ሰይፉ ፋንታሁን ማድረጉን ሰነዶች ይጠቁማሉ የብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ እሴቶችን በማስተዋወቅ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ታዋቂ በመሆን ‹‹የኢትዮጵያ የባህል አምባሳደር›› ተብሎ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የተሰየመው ዮድ አቢሲኒያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ‹‹የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶብኛል›› በማለት አቤቱታ ለሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ማቅረቡ ታወቀ፡፡

ላሊበላን ለመጠበቅ የተዘረጋው የብረት ጥላ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስላመዘነ ሊነሳ ነው

የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ከተለያዩ የተፈጥሮ አደጋዎች ለመከላከል በሚል የከባድ የብረት ምሰሶ የተሠራው ጥላ፣ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስላመዘነ ሊነሳ እንደሆነ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ጥላው የተዘረጋው ቅርሱን ከዝናብ፣ ከንፋስና ከመሳሰሉት ተፈጥሯዊ ተፅዕኖዎች ለመከላከል በሚል ቢሆንም፣ ቅርሱን እየተጫነው ነው፡፡ በተለይም ከጊዜ ብዛት ጥላው ያረፈበት የቅርሱ ክፍል እየተሰነጠቀ መምጣቱ በጥናት መረጋገጡ ተገልጿል፡፡